የኢሬቻ ጨፍጨፋ ና ፋሽስት ወያኔ So far 350+ Murdered by TPLF

By Muluken Tesfaw

ፋሽስት ወያኔ ባዶ ቄጠማ በመያዝ የኢሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ንጹሀን የኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ ልቤን ሰብሮታል። በጭፍጨፋው ከሞቱ መካከል ከኦሮሞ ወንድሞቻቸዉ ጋር በዓሉን ሊታደሚ ወደ ስፍራው የተጓዙ የአማራ ልጆችም እንደሚገኙበት ታዉቋል።

ነጭ ለብሰው፤ ባዶ ቄጠማ ብቻ በእጃቸው ይዘው ፈጣሪን ለአገራቸው ሰላም እንዲሰጥና ዘመኑ እንዲባረክላቸው ሊለምኑ በወጡ ንጹሀን ኦሮሞዎች ላይ የትግራዩ አገዛዝ ባወረደው መቅሰፍት፤ ከላይ የትግራይ ሄሊኮፕተሮች ባዘነቡት ቦንብ፤ ከታች በመርዝ ጭስና በትግራይ አልሞ ተኳሽ አጋዚዎች ጥይት በተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ እስካሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኦሮዎሞች ሰማዕት ሆነዋል።

እነሆ ዛሬ ለሁሉም ግልጽ ሆኗል! ጎንደር ደብረታቦር ሲከበር ነጭ የለበሱ የአማራ ወጣቶች በነፍሰ በላ የትግራይ ወታደሮች ወድቀው ነበር። ዛሬ ደግሞ ቄጠማ ይዘው፤ ነጭ ለብሰው የወጡ የኦሮሞ እምቡጦች በትግራይ ጨካኝ አጋዚዎች ተጨፍጨፈዋል። በወያኔው ኢትዮጵያ ደም ሳይፈስ በፌሽታና በደስታ የሚከበረው የተከዘ ማዶዎቹ አሸንዳ ብቻ ነው።

በዚህ የኦሮሞች የምስጋና ቀን በፋሽስት ወያኔ ጭፍጨፋ የተቀጠፉትን የኦሮሞ ሰማዕታት እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር! ለወደቁ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ። ይህ ወቅት በአካባቢው ለምትገኙ አማሮች የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችንን የድረሱልኝ ጥሪ ተቀብላችሁ ለተጎዱ የኦሮሞ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሞያዊ እርዳታ በመስጠትና ደም በመለገስ ከኦሮሞ ወገኖቻችን ጎን በመቆም የተለመደ አጋርነታችሁን የምታሳዩበት ወሳኝ ጊዜ ነው።

በተባበረ ክንዳችን ወያኔ የግፍ ዋጋውን እንዲያገኝ እናደርገዋለን!