በጎንደር ተኩሱ ቀጥሏል፣ በግጭቱ 6 ሰው ሞቷል

ሰበር ዜና፣ በጎንደር ተኩሱ ቀጥሏል፣ በግጭቱ 6 ሰው ሞቷል
May 1, 2014 
ነገረ-ኢትዮጵያ – ጎንደር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታ አርምጭሆ ሰፈር፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች የከተማው 
አስተዳደር ‹‹ህገ ወጥ ሰፈራ ነው፡፡›› በሚል ቤቶችን ለማፍረስ መዘጋጀቱን ተከትሎ አፍራሾቹ ከህዝብ ጋር በፈጠሩት ግጭት 
ከ6 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ግጭቱ ከሶስት 
ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ ቀጥሎ የነበር ሲሆን ምንጫችን ደውሎ በሚነግረን ወቅት (ከቀኑ 6፡ 43) ተኩስ 
እንደነበር ለመረዳት ችለናል፡፡ 
የአካባቢው ነዋሪዎቹ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ በተላለፈበት ወቅት ህገ ወጥ አለመሆናቸውን፣
ካልሆነም መንግስት ቅያሬ ቦታና ጊዜ መስጠት እንዳለበት በመግለጽ አንለቅም ብለው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዛሬው ቀን
ግጭቱ የተነሳውም አፍራሾቹ እንዲፈርሱ የተወሰነባቸውን ቤቶች ቀለም በመቀባታቸውና ህዝቡም እንዳይቀቡ በመከልከሉ
መሆኑ ታውቋል፡፡
በግጭቱ ፖሊስ፣ ፌደራልና ልዩ ኃይል የተሳተፈበት ሲሆን ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የአካባቢው ወጣቶች ላይ
ድብደባና እስራት እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ‹‹ወጣቶችን እንደ እንሰሳ በአንድ
ገመድ አስረው እየደበደቧቸው ነው፡፡ ህዝብ በጅምላ እየታሰረ ይገኛል፡፡ ግጭቱ ቢያቆምም በአሁኑ ወቅት በሶስቱም ሰፈሮች
ጥይት እየተተኮሰ ነው›› ያሉት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች የተወሰደው እርምጃ የጎንደርን ህዝብ በማስቆጣቱ ከዚህ የባሰ
ግጭት እንዳይፈጠር ያሰጋል ሲሉም ገልጸውልናል፡፡ በግጭቱ ወቅት የመጀመሪያዋ የሞት ሰለባ የሆነችው ልዩ ኃይል ቤቷ
እንዲፈርስ ቀለም ሲቀባ የተቃወመች የልጆች እናት እንደሆነችም ታውቋል፡፡

Zone9 – Compiled Book of Year One

By zone9

የዞን ፱ ጥንካሬ እና ምን ያህል በፅሁፎቻቸው በሳል እንደነበሩ ለማታውቁ አንዳንድ ካድሬዎች እንዲሁም ሰለ ዞን ፱ ግንዛቤ ለሌላቸው አንባቢዎች ይሀው የአንድ አመት ፅሁፎቻቸው በዚህ መልክ አጠናክረው መፅሀፍ መሆን ቢገባውም በነፃ እንኩ ብለውናል።

Zone9 – Compiled Book of Year One

Suit filed after bus driver calls Ethiopian 11-year-old ‘monkey’

By Edna Adato and Efrat Forsher

Israel Hayom

image

“Not even a lawmaker would imagine that a young girl would be so humiliated by a bus driver on a school field trip only because of the color of her skin and ethnic background,” the complaint says.

An 11-year-old Israeli girl of Ethiopian descent has filed a lawsuit against a school bus driver who humiliated her and made disparaging racist remarks during a class field trip to a swimming pool.

The lawsuit, filed at the Jerusalem Municipal Court with assistance from the Justice Ministry’s legal aid department, emphasized the importance of a case highlighting such “extreme” defamation.

The complaint details the bus driver’s offensive actions, saying that at one point he took the microphone and said to the girl, “Hey you, the monkey in the back.”

Later, when she was outside the bus taking her bag from the baggage compartment, the driver called out, “Where is the monkey?”

When she returned to the bus, the driver said: “There you are. You will not behave this way on my bus. You can act like that in your parents house. What difference will it make? They are monkeys anyway, so you can go to that zoo.” The remarks were made in front of the girl’s friends.

“Not even a lawmaker would imagine that a young girl would be so humiliated by a bus driver on a school field trip only because of the color of her skin and ethnic background,” the complaint read.

The complaint also said the fifth-grader also feared that the driver would hit her.

The bus company Pituach Mateh Binyamin released a statement saying that “the claims were brought before all relevant bodies. We were surprised to hear about the lawsuit because we have not been summoned to court.”

Eritrean rebel group based in Ethiopia claim to have killed dozens of intelligence agents

 

By Tesfa-Alem Tekle
Sudan Tribune

April 29, 2014 (ADDIS ABABA) – Eritrean rebel group, the Red Sea Afar Democratic Organization (RSADO), alleged on Monday it had killed and wounded dozens of Eritrean government intelligence agents in an attack inside the reclusive East African nation.

The Ethiopia-based rebel group said that the strike was carried out at the military barracks of an intelligence unit based in the Northern Red Sea region in the vicinity of Alhan.

Ibrahim Haron, the leader of the rebel group, told Sudan Tribune that their “forces in the early hours of Saturday attacked the military camp and killed 27 intelligence agents and wounded many others belonging to the 15th sub-division intelligence unit”.

The rebel leader said his fighters took control of the military base for over eight hours following the attack, destroying the entire camp before leaving the area.

The group also claims to have captured various types of weapons.

There was no immediate comment from the government in Asmara and the claims cannot be independently verified.

He said there were some 70 government intelligence members inside the camp during the assault but he said none of them tried to engage the rebel fighters.

“They preferred to runaway than fight against [us]. This indicates how much the government army is weakening,” the rebels said.

Ibrahim said the latest assault was in retaliation to ethnic killings by Eritrean government agents targeting Afar minorities.

This is the rebel group’s first cross-border attack since 2012 when they killed 30 Eritrean soldiers in an attack at a military base in the Southern Red Sea region.

RSADO which is a member of the Eritrean Democratic Alliance (EDA), a coalition of 11 Eritrean political organisations, renewed its calls for other opposition members to join the armed struggle to topple president Isaias Afwerki’s regime.

After the 1998-2000 bloody border war between Eritrea and Ethiopia, Asmara considers Eritrea’s Afars as being aligned to Ethiopia and having links to fellow Afar tribes in Ethiopia.

Ethiopia’s Jewish community divided

24 April 2014

BBC

As Jewish people around the world marked the festival of Passover, thousands of Jews living in northern Ethiopia, did not have much to celebrate.
Many have been left disappointed by an Israeli government decision to end a 30-year-old programme that saw tens thousands of Ethiopian Jews airlifted to the Holy Land.
And many families are grappling with being separated from their loved ones, as Focus on Africa’s Emmanuel Igunza found out in the north-western city of Gondar.

http://youtu.be/nBaAMm9B9vE

የማንነት ብዙነትና ወሳኝ ማንነት

22 April 2014

ከስማቸው ተሰማ
Borkena.com

የኤርትራን ነጻ አገር መሆን ተከትሎ በጥቂት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያና የ ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር በብዙ አስር ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ኤርትራ ተባረሩ፤ ከተባረሩት ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ተወልደው ካደጉባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጋር ያላቸው ምስ ስል እና ቅርበት በዘር ሀረግ ከሚዛመዱት ከ ኤርትራ ማህበረሰብ ጋር ካላቸው ምስ ስል የበለጠ እንደነበር ግልጽ ነው። ከ ኢትዮጵያ ለመፈናቀላቸው ኤርትራዊ ማንነታቸው ምክንያት ይሁን እንጅ፣ በሄዱበት ኤርትራ ደግሞ ብዙ ርቀት አቋርጠው ከመሄዳቸው ጋር በሚያያዝ መልኩ “አምቼ” መባላቸው የማንነታቸው አንዱ መገለጫ ሊሆን ችሏል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ ኤርትራዊነታቸው የጎላውን ያህል፣ ኤርትራ ውስጥ ሲኖሩ ከ ኢትዮጵያ መሄዳቸው ወሳኙ የማንነታቸው መገለጫ ሆኗል።

በተመሳሳይ መልኩ ዜግነት ስለሌላቸው ብቻ ተወልደው ካደጉበት አገር በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ወላጆቻቸው አገር እንዲሄዱ የሚጠየቁ ሰዎች ተመሳሳይ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ባደጉበት አገር ከሌላ አገር ከመጡ ወላጆች መወለዳቸው ጎልቶ የሚታይ በመሆኑ ወሳኝ ማንነታቸው እሱ እንደሆነ ተደርጎ ቢቀርብም እውነተኛ አገራቸው ወደተባለው አገር ሲሄዱ ግን ካደጉበት አገር የወረሱት ቋንቋ፣ ባህል ፣ የ አመለካከት እና ሌሎችም ዝንባሌዎች ጎልተው ይወጣሉ። ከልጅነታቸው ጀምሮ አሜሪካ አድገው በወንጀልና በህገወጥነት ምክንያቶች ወደ ሌሎች አገራት እየተባረሩ ያሉ ሰዎችን በዜግነት አሜሪካዊ ባይሆንም ከ አገሪቱ ጋር ባላቸው ቁርኝት የተነሳ ተባረው በሚሄዱበት ቦታ እንደ አሜሪካ ስደተኞች እንደሚኖሩ ለማሳየት Daniel Kantstroom የተባለ ስድተኞችን በተመለከቱ ህጎች ዙሪያ የታወቀ ምሁር እነዚህን ሰዎች “the new American Diaspora” በማለት ይገልጿቸዋል።

ከዚህ ጋር አያይዘን በተለያዩ ጊዚያት ወደ እስራ ኤል የተጓዙ ቤተ እስራኤላውያንንም ማንሳት ይቻላል። ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ጎልቶ የሚታየው የማንነታቸው መልክ ከ እስራ ኤል ጋር ያላቸው ቁርኝት ቢሆንም እስራ ኤል ውስጥ ደግሞ ከቆዳቸው ቀለም ጀምሮ ኢትዮጵያዊ መነሻቸው የማንነታቸው ጉልህ መገለጫ የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚ አለ።

ከላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች ማንነት አንድና ወጥ እንዳልሆነ ከማሳየት አልፈው በተለያዩ ሁኔታዎች ጎልቶ የሚወጣው የ አንድ ሰው የማንነት ገጽታ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል የሚያመላክቱ ይመስለኛል። ማንነት፣ ምስ ስልና ልዩነትን፣ ርቀትና ቅርበትን፣ እንዲሁም መዛመድንና አለመዛመድን መሰረት አድርጎ የሚደረግ ክፍፍልንና መቧደንን የምንረዳበት፣ የምንገልጽበትና የምንተነትንበት ጽንሰ ሃሳብ ነው። የምንመሳሰልባቸው እና የምንለያይባቸው፣ የምንራራቅባቸውና የምንቀራረብባቸው፣ የምንዛመድባቸውና የማንዛመድባቸው ነገሮች በጣም ብዙ ስለሆኑ የተለያዩ ማንነቶች ይፈጥሩልናል። የወላጅ፣ የ አያት፣ ቅድመ አያት ወዘተ መጋራት ቤተሰብነትና ዝምድናን ይፈጥራል፤ በጾታ መመሳሰል የጾታ ማንነትን ይፈጥራል፤ በሃይማኖት መመሳሰል የሃይማኖት ማንነትን ይፈጥራል፤ በቋንቋ መመሳሰል፣ የቋንቋ ማንነትን ይፈጥራል፤ በ አገር መሳሰል፣ የ አገር ማንነትን ይፈጥራል፣ በ አህጉር መመሳሰል አህጉራዊ ማንነትን ይፈጥራል፤ በፖለቲካ አቋም መመሳሰል ፣ የፖለቲካ ማንነትን ይፈጥራል፤ በቆዳ ቀለም መመሳሰል፣ የቀለም ማንነትን ይፈጥራል። አንድ ሰው ልብስ ደራርቦ እንደሚለብሰው ሁሉ ከ እነዚህን የተለያዩ የማንነት መገለጫዎችንም ደራርቦ ይይዛል። ከነዚህ ሁሉ ማንነቶች ጀርባ ሰው በሰውነቱ ከሁሉም ሰዎች ጋር የሚጋራው ሰብ አዊ ማንነት አለው።

ከዚህ በመነሳት ስለ ማንነት የተወሰኑ ምልከታዎችን ማድረግ የምንችል ይመስለኛል። አንድ ሰው ካሉት ተደራራቢ ማንነቶች ውስጥ አስበልጦ የሚያየውን ሊወስን ይችላል። ነገር ግን ይሄ ውሳኔ ከሚኖርበት ከባቢ ተጽእኖ ነጻ መሆን የሚችል አይደለም። ይሄ የሆነበት አንዱ ምክንያት የሚኖርበት ባህላዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ከባቢ አጉልቶ የሚያያቸው የማንነት አይነቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነው። ራሱ አስበልጦ የሚያየው የማንነቱ ቀለም እና ሌሎች ሰዎች አጉልተው የሚያዩት የማንነቱ ቀለም አንድ ላይሆን መቻሉም ሌላው ገዳቢ ነገር ነው። ለምሳሌ ባሁኑ ሰ አት የ አለም ህዝብ በዋነኝነት የተከፋፈለው እና የተቧደነው በ አገራት እንደመሆኑ አንድ ግለሰብ ከሁሉም አስበልጬ የማየው ማንነቴ ሰው መሆኔን ነው በማለት ብቻ በፈለገው አገር ሄዶ የመኖር እድል አያገኝም። ወይም ደግሞ ከ እምነት ከማይመሳሰሉኝ ኢትዮጵያዊያን በእምነት የሚመሳሰሉኝ የሳውዲ ሰዎች ይበልጡብኛል ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ በህገ ወጥነት ወደ አገርህ ሂድ ተብሎ ከመባረር አይድንም፤ከላይ መግቢያው አካባቢ በተጠቀሰው አይነት ሰዎች ጥርስ ነቅለው ካደጉበት አገር ወደ “አገራችሁ” ሂዱ እየተባሉ የሚባረሩበት እውነት ይህ አለም የሰዎች ሳይሆን የ አገሮች ነው እንድንል ያስገድደናል።

ከሁሉም የማስበልጠው የ ትግራይ ማንነቴን ነው፣ በዚህም ከ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ጋር ያለኝ ዝምድና ይበልጥብኛል የሚል ሰው፣ በ ኤርትራ ሲኖር በሌሎች ዘንድ ከትግራይ መምጣቱ የጎላ የማንነቱ መገለጫ ተደርጎ እንዳይታይ መከላከል ይከብደዋል። ከሁሉም የማስበልጠው አማራ መሆኔን ነው የሚል አንድ የጎጃም አካባቢ ሰው፣ ወደ ጎንደር ቢሄድ የጎጃሜነት ማንነቱን ደጋግሞ እንዲያስታውስ የሚያደርግ ከባቢ ውስጥ ሊኖር እንደሚችል መገመት ይቻላል። ከሁሉም የማስበልጠው ማንነቴ ጎጃሜ መሆኔን ነው የሚል ሰው ወደ ኦሮምያ ወይም ደቡብ ክልል ቢሄድ ጎልቶ የሚጠቀስለት ማነነቱ አማራነቱ ሊሆን እንደሚችልም መገመትም ይቻላል።

ከሌላ አገር በስደት ከመጡ ወላጆች ተወልደው የሚያድጉ ህጻናት ከሚገጥማቸው ማንነት ነክ ፈተና አንዱ ባደጉበት አገር ከሌላ አገር ጋር ያላቸው የትውልድ ቁርኝት እነሱ ባይፈልጉት እንኳን በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ጎልቶ የሚታይ መሆኑ ነው። እነሱ ተወልደው ካደጉበት አገርና አካባቢ ያገኙትን ማንነት ማጉላት ቢፈልጉ እንኳን በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ወላጆቻቸው የመጡበትን አካባቢ እና ከዚያም የሚቀዳውን ማንነት ደጋግመው ያስታውሷቸዋል። ማንነት መመሳሰልንና ልዩነትን መሰረት የሚያደርግ እንደመሆኑ በ አንድ አካባቢ ውስጥ አንድን ሰው ወይም ቡድን በ አካባቢው ካሉ ሰዎች ወይም ቡድኖች ለየት የሚያደርገው የማንነቱ ቀለም ጎልቶ ይወጣል። በነጭ ወረቀት ላይ በነጭ ቀለም ቢጻፍ እንደማይታይ ሁሉ፣ በነጭ ወረቀት ላይ ከነጭ በተለየ ቀለም ሲጻፍ ጎልቶ እንደሚወታው ሁሉ በማንነት ውይይት ውስጥ ጎልቶ የሚወጣው የሚያመሳስለው ሳይሆን የሚያለያየው ነገር ነው። እስካሁን ባለው ሀተታ ወሳኝ ሊባል የሚችለው ማንነት በምርጫ እና በሁኔታዎች ሊለያይ እንደሚችል ግልጽ የሆነ ይመስለኛል። ስለዚሁ ነጥብ አንድ ተጨማሪ አስተያየት በመስጠት ይህን ጽሁፍ ላጠቃልል።

ማንነት ተኮር ግጭቶች ስለሚነሱበት እውነት እያሰብን የ አለምን ሁኔታ ብናስተውል በየ አካባቢው ያሉ የተለያዩ አይነት ልዩነቶች፣ ከህዝቦች ታሪካዊ መስተጋብር ጋር ተዳምረው ስር በሰደደ እና በከረረ ፉክክር፣ በጥላቻ እና በግጭት ውስጥ ጎልተው እናስተውላለን። በቋንቋ አንድ በሆኑ እንደ ሱማልያ ባሉ አገራት የጎሳ ልዩነት ጎልቶ ሊወጣ ይችላል። በደቡብና ሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ልዩነት መሰረቱ ርእዮታለማዊ ነው። እስልምናን በመከተል ተመሳሳይ የሆኑ ማህበረሰቦች፣ በተለያዩ ሴክቶች መካከል ባለው ልዩነት እና ፉክክር ተጠምደው ወደ ግጭት ያመራሉ። ቀደም ባለው ጊዜ በሶሻሊዝም አስተሳሰብ የተቃኙ የኢትዮጵያ አንዳንድ ወጣቶች ከብሄር ወይም ከቋንቋ ዝምድና ይልቅ መደባዊና ርእዮተ አለማዊ ወገንተኝነት የበለጠ ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር እንደሆነ መረዳት ይቻላል። የእያንዳንዱ አገር ወይም አካባቢ ሁኔታ ራሱን በቻለ የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊና ሌሎችም ዝርዝር እውነታዎች የሚወሰን አካሄድ ያለው በመሆኑ፣ በቋንቋ ይሁን በርዕዮተ አለም፣ በጎሳ ይሁን ወይም በአካባቢ፣ በሃይማኖት ይሁን ወይም ሌላ ልዩነቶችና በ አንድ አካባቢ ባለ ግጭት ግልጽ የሆነ የምክንያትና የውጤት ግንኙነት መፍጠር ይከብዳል። ቢያንስ ግን በየሁኔታው ከሚያመሳስለው ነገር ይልቅ የሚያለያየው ነገር ጎልቶ እንደሚወጣና ወሳኝ ተደርጎ እንደሚወሰድ መመልከት ይቻላል። በተጨማሪም የሚጎላው ማንነት እያንዳንዱ ግለሰብ ወይም ቡድን ለራሱ በሚመርጠው ብቻ ሳይሆን፣ ከሌሎች ሰዎች ወይም ቡድኖች ጋር በሚያደርገው መስተጋብር ከእነሱ በሚለይበትና እንዲጎላ በሚፈልጉት እንዲሁም በሌሎች ታሪካዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ሊወሰን እንደሚችል መረዳት ይቻላል። በተለያየ ሁኔታ ጎላ ብሎ ስለሚወጡ ወይም ስለሚቀርቡ ማንነቶች በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የተነሱ አንዳንድ ነጥቦችን በቀጣይ ጽሁፎችም በተሻለ ቅርበት ለማየት እሞክራለሁ።
ቸር ይግጠመን።