የጎንደር ከተማ የጎብኝዎች ካርታ ተዘጋጀ

Thursday, 06 February 2014

የጎንደር ከተማ የጎብኝዎች ካርታው ለጎብኝዎች የተሟላ መረጃ ለማቅረብና የጎብኝዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንደሚያግዝ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

በጎንደር ከተማ የሚገኙ መስህቦችንና በዙሪያዋ ያሉ የመስህብ ስፍራዎችን የሚመለከት ሙሉ መረጃ የሚሰጥ የጎብኝዎች ካርታ በስፔን መንግስትና በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትብብር ተዘጋጅቶ ይፋ ሆኗል፡፡

የጎንደር ከተማን የጎበኝዎች ካርታ በዋናነት ያዘጋጁት ፕሮፌሰር ኤድዋርደ ማርቲን በክልሉ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን የሚገልጽ ካርታ ለመስራት ያሰበው የቅርስ ጥናት ስራውን በጎንደር ሲያካሂድ እንደነበር ገልጿል፡፡

‹‹ የጎንደርን የጎብኝዎች ካርታ ለመስራት ያስብኩት የቅርስ ጥናት ስራ እየሰራሁ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ሁሉንም ታሪካዊ ቦታዎችና የአማራ ክልልን የተፈጥሮና የታሪክ ስብጥር ለመለካት እነዚህን መረጃዎች ለጎብኝዎች በሚሰጥ ካርታ ቢዘጋጅ ጥሩ እንደሆነ አሰብኩ፡፡ ሁሉንም መረጃዎች በተመሳሳይ ይዘት እና ካርታ ላይ ለጎብኝዎች ለማካተትም ቻልኩ፡፡››

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ታደለች ዳሌቾ  የተዘጋጀው ካርታ ታሪካዊ ስፍራዎችን ለሚጎበኙ ሰዎች ሙሉ መረጃ ከመስጠት ባለፈ የጎብኚዎችን ቁጥር ለማሳደግና የጊዜ ቆይታ ለማራዘም ያግዛል ብለዋል፡፡

በ27 ሺህ ዩሮ የተዘጋጀው የጎንደር ከተማ የጎብኝዎች ካርታ በናሽናል ጅኦግራፊ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

የጎንደር ከተማ እንደ በጎርጎሮሳውያኑ ዘመን ቀመር በ1979 በአለም የቅርስ መዝገብ የታሪካዊ ቅርሶች መገኛ በሚል መመዝገቡ ይታወሳል፡፡

ሪፖርተር፡-የልቤ ማዘንጊያ

Source.ertagov.com

%d bloggers like this: