የአ.አ ከንቲባ ጽ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ተታኮሱ

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

image

የአዲስ አበባ መስተዳደር ማዘጋጃ ቤት (ከንቲባ ጽ/ቤት) ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች ዛሬ በግምት ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ እርስ በእርሳቸው መታኮሳቸውን አስተዳደሩ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ 

ፖሊሶቹ የተታኮሱት በከንቲባው ጽ/ቤት ውስጥ የሚሰሩ ፖሊሶች በነበራቸው ግምገማ በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ፖሊሶቹ የተታኮሱት ከስብሰባው እንደወጡ እንደሆነም ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

በከንቲባ ጽ/ቤት ፖሊሶች በተታኮሱበት ወቅት የአትክልት ተራን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኘው ማህበረሰብ በድንጋጤ ውስጥ እንደነበርና አብዛኛው ከተኩሱ በኋላ ወደ አስተዳደሩ ቢሮ በማቅናቱ በከንቲባው ጽ/ቤት አካባቢ በርከት ያለ ህዝብ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡ 

ፖሊሶቹ በተታኮሱበት ወቅት ገላጋዮች መሃላቸው በመግባታቸው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለና ይህም በግምገማው ወቅት ለገላጋይ ያበቃ አጨቃጫቂ ጉዳይ እንደነበራቸው ያሳያል ተብሏል፡፡