የሰማያዊ ፓርቲ በ ጥር 17 ቀን በፓርቲዉ ጽ/ቤት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ የዉይይት መድረክ አዘጋጅቷል

የሰማያዊ ፓርቲ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ መሰረት፣ ቅዳሜ ጥር 17 ቀን በፓርቲዉ ጽ/ቤት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ የዉይይት መድረክ አዘጋጅቷል። « ድንበራችንን ጉዳይ በተመለከተ በተጨባጭ መረጃ በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ይፈጠር ዘንድ ትምህርታዊ ውይይት መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይም በዘርፉ ለረጅም አመታት በመስራት የሚታወቁት የረጅም ጊዜ የጆግራፊ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ድንበሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርት ይሰጣሉ» ሲል የገለጸው የሰማያዊ መግለጫ፣ ኢትዮጵያዉያን በስፍራዉ ተገኝተዉ በጉዳዩ ላይ ሙሉ ግንዛቤ እንዲያገኙ ጥሩ አቅርቧል።

semayawi_border
የሰማያዊ ፓርቲ ፣ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ለተለያዩ የመንግስት አካላት በጉዳዩ ላይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን እስከአሁን ጉዳዩን በድብቅ ለመያዝ ከፈለጉ የመንግስት አካላት እስከአሁን ማብራሪያ ሊገኝ አልተቻለም።

%d bloggers like this: