የማንነት ብዙነትና ወሳኝ ማንነት

22 April 2014

ከስማቸው ተሰማ
Borkena.com

የኤርትራን ነጻ አገር መሆን ተከትሎ በጥቂት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያና የ ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር በብዙ አስር ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ኤርትራ ተባረሩ፤ ከተባረሩት ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ተወልደው ካደጉባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጋር ያላቸው ምስ ስል እና ቅርበት በዘር ሀረግ ከሚዛመዱት ከ ኤርትራ ማህበረሰብ ጋር ካላቸው ምስ ስል የበለጠ እንደነበር ግልጽ ነው። ከ ኢትዮጵያ ለመፈናቀላቸው ኤርትራዊ ማንነታቸው ምክንያት ይሁን እንጅ፣ በሄዱበት ኤርትራ ደግሞ ብዙ ርቀት አቋርጠው ከመሄዳቸው ጋር በሚያያዝ መልኩ “አምቼ” መባላቸው የማንነታቸው አንዱ መገለጫ ሊሆን ችሏል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ ኤርትራዊነታቸው የጎላውን ያህል፣ ኤርትራ ውስጥ ሲኖሩ ከ ኢትዮጵያ መሄዳቸው ወሳኙ የማንነታቸው መገለጫ ሆኗል።

በተመሳሳይ መልኩ ዜግነት ስለሌላቸው ብቻ ተወልደው ካደጉበት አገር በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ወላጆቻቸው አገር እንዲሄዱ የሚጠየቁ ሰዎች ተመሳሳይ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ባደጉበት አገር ከሌላ አገር ከመጡ ወላጆች መወለዳቸው ጎልቶ የሚታይ በመሆኑ ወሳኝ ማንነታቸው እሱ እንደሆነ ተደርጎ ቢቀርብም እውነተኛ አገራቸው ወደተባለው አገር ሲሄዱ ግን ካደጉበት አገር የወረሱት ቋንቋ፣ ባህል ፣ የ አመለካከት እና ሌሎችም ዝንባሌዎች ጎልተው ይወጣሉ። ከልጅነታቸው ጀምሮ አሜሪካ አድገው በወንጀልና በህገወጥነት ምክንያቶች ወደ ሌሎች አገራት እየተባረሩ ያሉ ሰዎችን በዜግነት አሜሪካዊ ባይሆንም ከ አገሪቱ ጋር ባላቸው ቁርኝት የተነሳ ተባረው በሚሄዱበት ቦታ እንደ አሜሪካ ስደተኞች እንደሚኖሩ ለማሳየት Daniel Kantstroom የተባለ ስድተኞችን በተመለከቱ ህጎች ዙሪያ የታወቀ ምሁር እነዚህን ሰዎች “the new American Diaspora” በማለት ይገልጿቸዋል።

ከዚህ ጋር አያይዘን በተለያዩ ጊዚያት ወደ እስራ ኤል የተጓዙ ቤተ እስራኤላውያንንም ማንሳት ይቻላል። ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ጎልቶ የሚታየው የማንነታቸው መልክ ከ እስራ ኤል ጋር ያላቸው ቁርኝት ቢሆንም እስራ ኤል ውስጥ ደግሞ ከቆዳቸው ቀለም ጀምሮ ኢትዮጵያዊ መነሻቸው የማንነታቸው ጉልህ መገለጫ የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚ አለ።

ከላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች ማንነት አንድና ወጥ እንዳልሆነ ከማሳየት አልፈው በተለያዩ ሁኔታዎች ጎልቶ የሚወጣው የ አንድ ሰው የማንነት ገጽታ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል የሚያመላክቱ ይመስለኛል። ማንነት፣ ምስ ስልና ልዩነትን፣ ርቀትና ቅርበትን፣ እንዲሁም መዛመድንና አለመዛመድን መሰረት አድርጎ የሚደረግ ክፍፍልንና መቧደንን የምንረዳበት፣ የምንገልጽበትና የምንተነትንበት ጽንሰ ሃሳብ ነው። የምንመሳሰልባቸው እና የምንለያይባቸው፣ የምንራራቅባቸውና የምንቀራረብባቸው፣ የምንዛመድባቸውና የማንዛመድባቸው ነገሮች በጣም ብዙ ስለሆኑ የተለያዩ ማንነቶች ይፈጥሩልናል። የወላጅ፣ የ አያት፣ ቅድመ አያት ወዘተ መጋራት ቤተሰብነትና ዝምድናን ይፈጥራል፤ በጾታ መመሳሰል የጾታ ማንነትን ይፈጥራል፤ በሃይማኖት መመሳሰል የሃይማኖት ማንነትን ይፈጥራል፤ በቋንቋ መመሳሰል፣ የቋንቋ ማንነትን ይፈጥራል፤ በ አገር መሳሰል፣ የ አገር ማንነትን ይፈጥራል፣ በ አህጉር መመሳሰል አህጉራዊ ማንነትን ይፈጥራል፤ በፖለቲካ አቋም መመሳሰል ፣ የፖለቲካ ማንነትን ይፈጥራል፤ በቆዳ ቀለም መመሳሰል፣ የቀለም ማንነትን ይፈጥራል። አንድ ሰው ልብስ ደራርቦ እንደሚለብሰው ሁሉ ከ እነዚህን የተለያዩ የማንነት መገለጫዎችንም ደራርቦ ይይዛል። ከነዚህ ሁሉ ማንነቶች ጀርባ ሰው በሰውነቱ ከሁሉም ሰዎች ጋር የሚጋራው ሰብ አዊ ማንነት አለው።

ከዚህ በመነሳት ስለ ማንነት የተወሰኑ ምልከታዎችን ማድረግ የምንችል ይመስለኛል። አንድ ሰው ካሉት ተደራራቢ ማንነቶች ውስጥ አስበልጦ የሚያየውን ሊወስን ይችላል። ነገር ግን ይሄ ውሳኔ ከሚኖርበት ከባቢ ተጽእኖ ነጻ መሆን የሚችል አይደለም። ይሄ የሆነበት አንዱ ምክንያት የሚኖርበት ባህላዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ከባቢ አጉልቶ የሚያያቸው የማንነት አይነቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነው። ራሱ አስበልጦ የሚያየው የማንነቱ ቀለም እና ሌሎች ሰዎች አጉልተው የሚያዩት የማንነቱ ቀለም አንድ ላይሆን መቻሉም ሌላው ገዳቢ ነገር ነው። ለምሳሌ ባሁኑ ሰ አት የ አለም ህዝብ በዋነኝነት የተከፋፈለው እና የተቧደነው በ አገራት እንደመሆኑ አንድ ግለሰብ ከሁሉም አስበልጬ የማየው ማንነቴ ሰው መሆኔን ነው በማለት ብቻ በፈለገው አገር ሄዶ የመኖር እድል አያገኝም። ወይም ደግሞ ከ እምነት ከማይመሳሰሉኝ ኢትዮጵያዊያን በእምነት የሚመሳሰሉኝ የሳውዲ ሰዎች ይበልጡብኛል ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ በህገ ወጥነት ወደ አገርህ ሂድ ተብሎ ከመባረር አይድንም፤ከላይ መግቢያው አካባቢ በተጠቀሰው አይነት ሰዎች ጥርስ ነቅለው ካደጉበት አገር ወደ “አገራችሁ” ሂዱ እየተባሉ የሚባረሩበት እውነት ይህ አለም የሰዎች ሳይሆን የ አገሮች ነው እንድንል ያስገድደናል።

ከሁሉም የማስበልጠው የ ትግራይ ማንነቴን ነው፣ በዚህም ከ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ጋር ያለኝ ዝምድና ይበልጥብኛል የሚል ሰው፣ በ ኤርትራ ሲኖር በሌሎች ዘንድ ከትግራይ መምጣቱ የጎላ የማንነቱ መገለጫ ተደርጎ እንዳይታይ መከላከል ይከብደዋል። ከሁሉም የማስበልጠው አማራ መሆኔን ነው የሚል አንድ የጎጃም አካባቢ ሰው፣ ወደ ጎንደር ቢሄድ የጎጃሜነት ማንነቱን ደጋግሞ እንዲያስታውስ የሚያደርግ ከባቢ ውስጥ ሊኖር እንደሚችል መገመት ይቻላል። ከሁሉም የማስበልጠው ማንነቴ ጎጃሜ መሆኔን ነው የሚል ሰው ወደ ኦሮምያ ወይም ደቡብ ክልል ቢሄድ ጎልቶ የሚጠቀስለት ማነነቱ አማራነቱ ሊሆን እንደሚችልም መገመትም ይቻላል።

ከሌላ አገር በስደት ከመጡ ወላጆች ተወልደው የሚያድጉ ህጻናት ከሚገጥማቸው ማንነት ነክ ፈተና አንዱ ባደጉበት አገር ከሌላ አገር ጋር ያላቸው የትውልድ ቁርኝት እነሱ ባይፈልጉት እንኳን በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ጎልቶ የሚታይ መሆኑ ነው። እነሱ ተወልደው ካደጉበት አገርና አካባቢ ያገኙትን ማንነት ማጉላት ቢፈልጉ እንኳን በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ወላጆቻቸው የመጡበትን አካባቢ እና ከዚያም የሚቀዳውን ማንነት ደጋግመው ያስታውሷቸዋል። ማንነት መመሳሰልንና ልዩነትን መሰረት የሚያደርግ እንደመሆኑ በ አንድ አካባቢ ውስጥ አንድን ሰው ወይም ቡድን በ አካባቢው ካሉ ሰዎች ወይም ቡድኖች ለየት የሚያደርገው የማንነቱ ቀለም ጎልቶ ይወጣል። በነጭ ወረቀት ላይ በነጭ ቀለም ቢጻፍ እንደማይታይ ሁሉ፣ በነጭ ወረቀት ላይ ከነጭ በተለየ ቀለም ሲጻፍ ጎልቶ እንደሚወታው ሁሉ በማንነት ውይይት ውስጥ ጎልቶ የሚወጣው የሚያመሳስለው ሳይሆን የሚያለያየው ነገር ነው። እስካሁን ባለው ሀተታ ወሳኝ ሊባል የሚችለው ማንነት በምርጫ እና በሁኔታዎች ሊለያይ እንደሚችል ግልጽ የሆነ ይመስለኛል። ስለዚሁ ነጥብ አንድ ተጨማሪ አስተያየት በመስጠት ይህን ጽሁፍ ላጠቃልል።

ማንነት ተኮር ግጭቶች ስለሚነሱበት እውነት እያሰብን የ አለምን ሁኔታ ብናስተውል በየ አካባቢው ያሉ የተለያዩ አይነት ልዩነቶች፣ ከህዝቦች ታሪካዊ መስተጋብር ጋር ተዳምረው ስር በሰደደ እና በከረረ ፉክክር፣ በጥላቻ እና በግጭት ውስጥ ጎልተው እናስተውላለን። በቋንቋ አንድ በሆኑ እንደ ሱማልያ ባሉ አገራት የጎሳ ልዩነት ጎልቶ ሊወጣ ይችላል። በደቡብና ሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ልዩነት መሰረቱ ርእዮታለማዊ ነው። እስልምናን በመከተል ተመሳሳይ የሆኑ ማህበረሰቦች፣ በተለያዩ ሴክቶች መካከል ባለው ልዩነት እና ፉክክር ተጠምደው ወደ ግጭት ያመራሉ። ቀደም ባለው ጊዜ በሶሻሊዝም አስተሳሰብ የተቃኙ የኢትዮጵያ አንዳንድ ወጣቶች ከብሄር ወይም ከቋንቋ ዝምድና ይልቅ መደባዊና ርእዮተ አለማዊ ወገንተኝነት የበለጠ ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር እንደሆነ መረዳት ይቻላል። የእያንዳንዱ አገር ወይም አካባቢ ሁኔታ ራሱን በቻለ የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊና ሌሎችም ዝርዝር እውነታዎች የሚወሰን አካሄድ ያለው በመሆኑ፣ በቋንቋ ይሁን በርዕዮተ አለም፣ በጎሳ ይሁን ወይም በአካባቢ፣ በሃይማኖት ይሁን ወይም ሌላ ልዩነቶችና በ አንድ አካባቢ ባለ ግጭት ግልጽ የሆነ የምክንያትና የውጤት ግንኙነት መፍጠር ይከብዳል። ቢያንስ ግን በየሁኔታው ከሚያመሳስለው ነገር ይልቅ የሚያለያየው ነገር ጎልቶ እንደሚወጣና ወሳኝ ተደርጎ እንደሚወሰድ መመልከት ይቻላል። በተጨማሪም የሚጎላው ማንነት እያንዳንዱ ግለሰብ ወይም ቡድን ለራሱ በሚመርጠው ብቻ ሳይሆን፣ ከሌሎች ሰዎች ወይም ቡድኖች ጋር በሚያደርገው መስተጋብር ከእነሱ በሚለይበትና እንዲጎላ በሚፈልጉት እንዲሁም በሌሎች ታሪካዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ሊወሰን እንደሚችል መረዳት ይቻላል። በተለያየ ሁኔታ ጎላ ብሎ ስለሚወጡ ወይም ስለሚቀርቡ ማንነቶች በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የተነሱ አንዳንድ ነጥቦችን በቀጣይ ጽሁፎችም በተሻለ ቅርበት ለማየት እሞክራለሁ።
ቸር ይግጠመን።

የማንነት ብዙነትና ወሳኝ ማንነት

22 April 2014 ከስማቸው ተሰማ Borkena.com የኤርትራን ነጻ አገር መሆን ተከትሎ በጥቂት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያና የ ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር በብዙ አስር ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ኤርትራ ተባረሩ፤ ከተባረሩት ውስጥ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ተወልደው ካደጉባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጋር ያላቸው

The post የማንነት ብዙነትና ወሳኝ ማንነት appeared first on 6KILO.com.

Vote for Aster & Teddy for Kora Awards

22 April 2014 DireTube.com Ethiopian Artists Teddy Afro and Aster Aweke in the list of the 20 top nominees for this year’s Kora Awards. The awards ceremony is scheduled to take place on 2nd December in Ivory Coast. Teddy Afro

The post Vote for Aster & Teddy for Kora Awards appeared first on 6KILO.com.

The science of why most marathon winners are from east Africa

22 April 2014 VOX ET@Max_Fisher max@vox.com The lead elite women’s grouping, including first-place Rita Keptoo, arrives in Wellesley during the 118th Boston MarathonSuzanne Kreiter/Boston Globe via Getty Today’s Boston Marathon set a major record: the first-place male runner is an American citizen

The post The science of why most marathon winners are from east Africa appeared first on 6KILO.com.

Ethiopia’s ‘villagisation’ scheme fails to bear fruit

Residents say government has not delivered on resettlement promise of land, clean water and livestock In the village of Elay, people are defying the government and returning home. Photograph: William Davison The Guardian William Davison Tue 22 April 2014 The

The post Ethiopia’s ‘villagisation’ scheme fails to bear fruit appeared first on 6KILO.com.

In Central Ethiopia, a Dankeshön to Germany 

22 April 2014 WFP Ire Galato, here with one of her sons, can now feed her family until the next harvest. Copyright: Lisa Bryant/WFP German funding for WFP-supported relief and safety-net programmes in Ethiopia is helping 1.6 million pastoralists and

The post In Central Ethiopia, a Dankeshön to Germany  appeared first on 6KILO.com.

Colby Grants To Fund Student Researchers in Ethiopian Church Forest

April 22, 2014 Colby.edu Colby student researchers collect insect samples at a church forest site with an Ethiopian student and an Ethiopian Orthodox priest. Below, a herder follows his cattle, which are drawn to the church forest preserves, including the

The post Colby Grants To Fund Student Researchers in Ethiopian Church Forest appeared first on 6KILO.com.

Ethiopian textile & garment exports earn $84mn in 9 months

April 22, 2014 Fibre2fashion News Desk – India Ethiopia exported US$ 84 million worth of textiles and apparel during the first nine months of the ongoing fiscal year 2013-14 that began on July 8, 2013, according to the Textile Industry

The post Ethiopian textile & garment exports earn $84mn in 9 months appeared first on 6KILO.com.

Ethiopia eyes untapped rubber production potential

April 22, 2014 Turkish Press ADDIS ABABA – Ethiopia is currently carrying out a pilot project on more than 700 hectares of land in the southwestern Bench Maji region that officials hope will help turn the country into a major

The post Ethiopia eyes untapped rubber production potential appeared first on 6KILO.com.

Dam! White Elephants in Ethiopia? 

By Alemayehu G Mariam  April 21, 2014 Last week, in a bizarre display of faux outrage and indignation, the regime in Ethiopia unleashed its big “experts” to go afterInternational Rivers, an organization that has been leading the global struggle to

The post Dam! White Elephants in Ethiopia?  appeared first on 6KILO.com.