Gondaronline.com

ወደ ቀዉስ አዘቅት የምትንደረደረዉ ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ወደ አዘቅት እየተንደረደረች በመሆንዋ የጉዳዩን አሳሳቢነት መንግሥት ሊያጤነዉ እንደሚገባ  የዶይቼ ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ዛሬ በጀርመንኛ ይፋ ባደረገዉ ኃተታዉ አሳስቦአል።

የኢትዮጵያ ሁኔታ የተዛባ ይመስላል ሲል የሚጀምረዉ የዶቼ ቬለዉ ጋዜጠኛ በኃተታዉ በሀገሪቱ ለብዙ ዘመናት ታምቆ የነበረዉ የሕዝቦች አለመግባባት የፀጥታ ኃይላት በሚወስዱት የጥቃት ርምጃ ችግሮች እየተባባሱ ነገሩ ከቁጥጥር ዉጭ በመዉጣት ላይ እንደሚገኝ ይጠቁማል። የኦሮሞ እና የአማራ ብሔረሰቦች መብታችን ይከበር ብለዉ መነሳታቸዉ፤ ወጣቱ ትዉልድ በበኩሉ ሥራና የሚበላ ዳቦን እፈልጋለሁ ብሎ በአንድነት መቆሙ፤ በሀገሪቱ ከልክ ያለፈ በስልጣን መባለግ በግልፅ መኖሩን ያመለክታል ይላል ጽሑፉ። መንግሥት በሀገሪቱ ለተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ በዉጭ ኃይላት ላይ ከማላከክ ይልቅ የጣለዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቶ በሥራ ላይ እተረጉመዋለሁ ያለዉን ተሐድሶ ገቢራዊ ማድረግ ይገባዋል። የቆለፈዉን የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን መክፈት ይኖርበታል ሲል ጋዜጠኛዉ በኃተታዉ ዘርዝሮአል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል፤ የሉድገር ሻዶምስኪን ኃተታ ተርጉሞ ልኮልናል።Listen from here DW
Exit mobile version