ብአዴን ማን ነው?

የስትራተጂ ስህተት ለከባድ ወድቀት ይዳርጋል

ኢህአፓ ትግሉን የጀመረው ገና በ1960 መጀመሪያ ነበር። አብዮቱ እየተቀጣጠለ ሃገር አቀፍ ሆነ። ዘውዳዊ ስርዓት ወድቆ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ርእዮተ ዓለም የሚመራ ሶሻሊዝም የኢትዮጵያ ስርአት እንዲሆን ነበር። ይህ ግራ አክራሪ ስታሊኒዝም በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ ይማሩ በነበሩ የተሰባሰበ ቡድን፣ የወቅቱ አብዮተኞች ተገቢውን መልክ የያዘ አደረጃጀት ያልነበረው፣ አብዮተኛ የሚል ስም በማግኘታቸው ብቻ “ዲሞክራሲያ” ተብሎ የሚታወቀውን የኢህአፓ ልሳን በየሳምንቱ በመበተን አሁን ኢትዮጵያ የደረሰባትና እየደረሰባት ያለው ከባድ ችግር የከፈተው እነ ዋለልኝ መኮንን እና የኢህአፓ ግብረአበሮቹ የስታሊን ደቀ መዛሙርት ኢትዮጵያን አደጋ ወስጥ ጣሏት። በዚህ ወቅት ሰፊውን ትኩረት የሰጡት፤

  1. በኤርትራ ጥቅያቄ ላይ ኢህአፓ ያለው አቋም ኤርትራ ከዚህ ቅኝ አገዛዝ ነፃ በመሆን ተገንጥላ ነፃ መንግሥት ማቋቋም ሙሉ መብቷ መሆኑን ያምናል፤
  2. ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ወህኒ ቤት እንደመሆኗ የኢህአፓ አቋም በዚሁ ጥያቄ ላይ ርቱእና ግልጽ ሲሆን፣ ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸውን እድል በራሳቸው በመወሰን እስከ መገንጠል መብታቸው ያልተገደበ ነው ይላል።

ይህ ትንታኔ ማንም ኢትዮጵያዊ በተጨማሪ ለማረጋገጥ ክፈለገ “ዲሞክራሲያ” ቅጽ 8 ቁጥር 1፣ የካቲት 23 ቀን 1973 የታተመውን ሙሉ ሃሳቡን በድጋሚ ጽፎታል፣ የቃላት ለውጥ በትንሹ ቢኖርበትም። ይህንን ጽሑፍ ለማግኘት EPRP በሚለው ድረገጽ በመግባት የዲሞክራሲያን እትም ከ1961 እስከ ዛሬ የሚለውን ፈልጋችሁ አንብቡ። ይህ ጽሑፍ የሚያሳዝነው ኢህአፓ አሲምባ እንደገባ ታጋዮቹ በፈጠሩት ጫና በሻእቢያ 1ኛ ጉባኤ 1969 መጨረሻ የአቋም ለውጥ በማድረግ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ናት፤ የኤርትራ ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ በመሆኑ ትግሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ስለሆነ ኤርትራም የዚሁ አካል እንጂ ቅኝ ተገዢ አይደለችም በማለት በጉባኤው የሰጠው ውሳኔ ቅጥረኛው ህወሓት ታህሳስ 1972 የኢህአፓ ተዋጊ ክንፍ ሰራዊት ከባድ መስዋእትነት ክፍሎ በወያኔ ተደመሰሰ። በውጭ ሃገር የሚኖሩ የኢህአፓ አመራር በየካቲ 1973 በዲሞክራሲያ ልሳን ያወጡት ጽሑፍ የኢህአፓው ተዋጊ ክንፍ ኢህአሠ ታጋይ ለናት ሃገሩ ኢትዮጵያ የከፈለውን መስዋእትነት ውድቅ ለማድረግ የታቀደ ነው፤ ለምን?

ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ነጥቦች የኢህፓ አመራር በዲሞክራሲያ ልሳኑ ደጋግሞ በመዘርዘር ጠባቦችና ጸረ ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ሃይሎች እንዲፈጠሩ አደረገ።

ጠባብና ዘረኛው ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት፣ ጸረ-ሕዝብና አንድነት ማገብት – ማህበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ – ተሓህት የዛሬው ህወሓት ሊፈጠር ቻለ። ይህ የኢህአፓ ርእዮተ ዓለምና አቋም ኢትዮጵያና ሕዝቧን ለዛሬው ክፉ አደጋ ዳርጓት አልፏል።

የሻእብያው የበህር ልጅና በአምሳያው የተፈጠረው ህወሓት አረጋዊ በርሄ በዋና ፈላጭ ቆራጭነት እስክ 1977 መጨረሻ ሲመራው የነበረ ቡድን ተሰብስቦ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሳ፣ በቋንቋ እስከ መገንጠል ሃገርና ሕዝብን ለመበታተን ፕሮግራሙን አስተካክሎና ጽፎ በማዘጋጀት ደደቢት በረሃ ወረደ። ተሓህት፤ የዛሬው ህወሓት – ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ – ባረቀቀውና ባዘጋጀው ፕሮግራም እነሆ ዛሬ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት መከራና ችግር፤ ፈርሳ፤ ሕዝብ ተበታትኖ እየተገደለ ለስቃይና መከራ ተዳረገ። ኢትዮጵያን በህወሓት ፋሽስት ስርዓት ደም እያለቀሰች ትገኛለች። የወላድ መሃን። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽኑ ኢትዮጵያዊነቱን ህወሓት በሃይል ነጥቆ በጎሳህ እመን ብሎታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓትን ዓላማ አንቀበልም፣ በኢትዮጵያዊነታችን እናምናለን በማለት በግለጽ እየተናገረ ይገኛል።

የኢህአፓ አመራር በኢትዮጵያ ፈጥሮት ያለፈው ግዙፍ ስህተቶች በርካታ ስለሆኑ ከላይ የጠቀስኩት መሰረታዊ ስህተት ሆኖ በራሱም ላይ ድክመቶቹ ለጥቃት ሊዳርገው ቻለ። በወቅቱ የተሰባሰቡት አመራር ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ በቅጡ ያልተገነዙቡ ጭፍን በሆነ አመለካከትበማርክሲዝም ሌሊኒኒዝም አብዮተኝነት ደንዝዘው መጥፎውን እና ደጉን ማየት የተሳናቸው ነበሩ። ከስህተታቸው መሃከል ሁለቱን አስፈላጊ ነገሮች እንመልከት።

  1. ማእከላዊ አመራር (central leadership) የዚህ አይነት የአመራር ስርአት ለአንድ ድርጅት ወሳኝ ነው። በወቅቱ ኢህአፓ ሙሉ እንቅስቃሴው በከተማ ውስጥ ስለነበር በምስጢር ቦታ አባላቱን አሰባስቦ በኮንፈረንስ ደረጃ ጊዜያዊ ማእከላዊ  አመራር ለመስጠት ይችሉ ነበር። በዚሁ ጊዜ በአባላቱ የተመረጠው ማእከላዊ ኮሚቴም ተሰብስበው ድርጅቱን በሙሉ ሃላፊነት የሚመሩ ብቃት ያላቸው ሥራ አስፈዳሚ “ፖሊት ቢሮ” ይመርጣሉ። ከነዚህ ብቁ ናቸው የተባሉትን፣ የድርጅቱ ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር፤ ካስፈለገም በሶስተኛ ዋና ጸሃፊ መርጠው የቀሩትም ማ/ኮሚቴ በሥራ አስፈፋሚው በየቦታው መድቦ ያሰራቸው ነበር። ግን በወቅሩ የነበሩት የኢህአፓ አመራር የዚህ አይነት የትግል ጉዞ አይፈልጉም፤ አልተቀበሉትም። ይህ ኢህአፓን ለውድቀት ዳረገው።
  2. የተመረጡት የሥራ አሰፈጻሚ አባላት የድርጅቱ መሰሶ የሆኑትን ክፍሎች ይቆጣጠራል፣ ይመራል። እነዚህም፤ ወታደራዊ፣ ፕሮፓጋንዳ ቢሮ፣ ኢኮኖሚ ቢሮ፣ የገጠር የሕዝብ ግንኙነት፣ የከተማ ግንኙነት፣ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሲሆኑ፣ እነዚህን በበላይነት የሚመራው የሥራ አስፈጻሚው ነው። እንደ አስፈላጊነቱም ከማ/ኮምቴው ብቃት ያላቸው ታጋዮች በየዘርፉ ይመደባል። ትእዛዝ ከላይ ወደ ታች ሲተላለፍ ተግባራዊነቱን በመከታተል ከታች ወደ ላይ ይላካሉ። ይህ የድረጅቱ ጥንካሬና ብቃት ሆኖ ያድጋል። በጉባኤው ያልተመረጡት የኢህአፖ አመራር ይህን አይቀበሉትም። ይህን ባለመቀበሉ ኢህአፓ ለውድቀት ተዳረገ።
  3. ወታደራዊ እስትራተጂን በተመለከተ ሥራው ሁሉ የሚጠናቀቀው በሥራ አስፈጻሚው በኩል ነው። ወታደራዊ ተግባራት የሳይንስ ጥበብና እውቀት ይጠይቃል። በውስጡ ብዙ ዘርፎች በስትራተጂ ደራጃ፣ በታክቲክ ወይም ስልት ደራጃ ያቀፈ አሰራርና አጠቃቀሙ ብልህነትና አስተዋይነትን ይፈልጋል። ስለሆነም የአንድ ድርጅት እንቅስቃሴ ተግባራዊ ይሆናል። ይህን የማይቀበል ድርጅት ደግሞ በቀጥታ ለሞትና ለውድቀት አሳልፎ የሚሰጥ ነው። ይህን በወቅቱ የነበሩ የኢህአፓ አመራር ወታደራዊ ጥበብን በንቀት ይመለከቱት ስለነበር፣ የኢህአፓ ተዋጊ ክንፉ ኢህአሠ በቀላሉ በህወሓት እንዲጠቃ አደረገው። የኢህአፓ አመራር ከብቃት አነስተኛነት አልፎ በወታደራዊ ስትራቴጂ እምነቱ ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ ውድቀት አስከተለለት።

ሌላው ቀርቶ ኢህአፓ ከተማን ለቆ ለትጥቅ ትግል ኤርትራ በረሃ ገብቶ ከሻእቢያ እንደተጥጋ ጉባኤ ጠርቶ የነበሩትን ደካማ አመራር አሰወግዶ ብቃት ባላቸው ታግዮች መለወጥ ሲገባው አላደረገውም። በወቅቱ የነበሩ የኢህአፓ አመራር ጉባኤ መጥራትን አይፈልጉትም፣ የፈሩታል። ምክንያቱም፣

  1. የነበረው ደካማ አመራር ተወግዶ በብቁ ታጋዮች ስለሚተካ፣
  2. ኢህአፓ ሃብታም ድርጅት እንድመሆኑ እያላገጡ መብላትና መዝረፍ የለመዱ በመሆናቸው ጥቅማችው እንዳይነካ ስለፈለጉ ነው።

ኢህአፓ እንደ ዲሞክራሲ አብይ ጉዳይ የሚከተለው የክልል ነፃ አስተዳደር “Regional autonomy” ነበር። ይህ ደግሞ ማእከላዊ አመራርን የሚጻረር፣ ትእዛዝ ተቀባይ የሌለው፣ ደፈጣ ተዋጊ ሰራዊቱን ለክፉ አደጋ አሳልፎ የሚሰጥ አደገኛ መንገድ ነው። ድርጅቱም ስርዓት የለሽ “anarchy” እንቅስቃሴ በቀጥታ የሚዳርገው ነው።

ህወሓት፣ ኢህአፓን ለማጥቃት ሃይሉን ማጠናከር የጀመረበት ወቅት

 ኢህአፓ በትግሉ ወቅት ህወሓት ጠላቴ ነው ብሎ አልፈረጀውም። ይልቁንስ በአንድ ግንባር ተስልፈን ሃገራችን ኢትዮጵያን አሁን ካለው የደርግ ስርዓት ነፃ አውጥተን ሕዝባዊ መንግሥት እንድንመሰረት በአንድነት እንሰለፍ ከማለት በስተቀር። ደጋግም ኢህአፓ ለህወሓት አመራር በመቅረብ ቢጠይቅም በህወሓት አመራር የተሰጠው ምላሽ “ከአባይ ኢትዮጵያ” ተስፋፊዋ ኢትዮጵያ ታጋይ የሆንከው ኢህአፓ ግንባር አንፈጥርም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አደረጉት። ትንሽ ቆየት ብሎም ኢህአፓ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ በስብሃት ነጋ የተፈረመ ደብዳቤ ተላከለት። ኢህአፓም ትግራይ ኢትዮጵያ ስለሆነች አንወጣም፤ እናንተም ሸዋ፣ ጎጃም ወዘተ ቤታችሁ ነው፤ በምትፈልጉበት ቦታ ለመንቀሳቀስ መብታችሁ ነው የሚል መልስ ሰጠ። ይህ በኢህአፓ የተሰጠው ምላሽ ትክክል ነው።

ኢህአፓ በህወሓት ላይ ምንም የመተናኮስ ሥራ አልሠራም። የህወሓት አመራር ግን በኢህአፓ ላይ ብዙ መተናኮልና በተናጠል ግደያ ጀምረዋል። ቀስ በቀስም ኢህአፓን ለመደመሰስ ዝግጅቱ እየተጠናከረ መጣ። ይህ ሲሆን የኢህአፓ አመራር በተለያዩ መንገዶች መረጃ ሲደርሳቸው መደረግ የነበረበትን ሥራ አልሠሩም። አሲምባ የነበሩ አመራር በየቀኑ የሚደርሳቸውን መረጃ በንቀት ይሁን ወይም በትእቢት ግምት አይሰጡትም ነበር።

የኢህአፓ ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠ የከፈለው ከባድ መስዋእትነት

የኢህአፓ ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠ “የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ሠራዊት” ተብሎ የሚታወቀው ነው። ኢህአሠ በተለያዩ የሃይል ምድብ ተመድቦ አንድ ሃይል ከ150 ታጋዮች በላይ እንደሆነም የህወሓት አመራር ሲናገሩ ነበር። ከ12-14 ሀይሎች ብዛት እንዳለውም ተናግረዋል። በወቅቱ የነበረው ትጥቁ  ዘመናዊ ክላሽንኮፍ የታጠቀ በአንድ ሃይል፤ ሶስት ዘመናዊ መትረየስም የታጠቀ በመሆኑ የህወሓት አመራር አረጋግጠው ተናግረዋል።

ኢህአፓ ከተለያዩ ግዛቶች የተሰባሰበ ኢትዮጵያዊ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችውን አጠናቅቀው በኢትዮጵያ ወስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመማር ላይ የነበሩ ስለሆኑ ንቁና የተማረ ታጋይ ነበር። ብቁ የኢህአፓ አመራር ግን አላገኘም።

ህወሓት ኢህአፓን እና ተዋጊ ክንፉ ኢህአሠን ለማጥቃት ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ አሲምባ የነበሩ የኢህአፓ አመራር አስተማማኝ መረጃ ቢደርሳቸውም ተገቢውን ጥንቃቄ ባለመፈጸማቸው በታሪክና በሕግ የሚይስጠይቃቸው ስህተት ፈጽመዋል።

  1. ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ኢህአፓ በማእከላዊ አመራር ያልተጀመረ፣ በወቅቱ የነበሩ አመራር በመሰላችው መንገድ የሚጓዙ፣ ስርዓት የለሽ ነበሩ። እያንዣበበ ያለውን አደጋ ለመከላከል አመራሩ ተሰብስቦ ጊዜያዊ አመራር መርጦ ቢሰይም ሁሉንም እየተቆጣጠረ ድርጅቱን እና ታጋዩን ከጥቃት ያድኑት ነበር። አልተደረገም።
  2. ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚው ድርጀቱ በነፃ ክልል አስተዳደር የተበታተነው ታጋይ ነፃ ክልሉን አፍርሶ ሁሉንም የድርጅቱን እንቅስቃሴ በአንድ ማእከላዊ አመራር ይመራው ነበር።

ሀ. ኢትዮጵያ ሰፊ ሃገር እንደመሆኗ የድርጅቱን ሃብትና ንብረት ወደማይታወቅ ቦታ ወስዶ ከዘራፊውና ወንጀለኛው ህወሓት ይድን ነበር፤

ለ. ኢህአሠና ቀሪው የኢህአፓ ታጋይ ከሚከፍለው መስዋእትነት ለማዳን ጊዜያዊ አመራር፣ በጥናት የተመረኮዘ፣ ወደ ሚተማመንበት ቦታዎች በተለያየ አቅጣጫዎች ማፈግፈግ ይችል ነበር። ትግራይን ለቆ በመውጣት የታጋዩን ህይወት በማዳን እንደገና ተደራጅቶ በህወሓት ላይ ጥቃት የመሰንዘር ሰፊ እድል በመፍጠር ኢህአሠ ወያኔንም ሆነ ሻእቢያን ይደመስሳቸው ነበር። ምክንያቱም አሁን ስልታዊ ወታደራዊ ማፈግፈግ በሰፊዋ ኢትዮጵያ ስለሚንቀሳቀስ ብዙውን ወጣት ዜጋ ወደ ትግሉ ስለሚቀላቀሉ ሃይልና ግልበቱ ተጠናክሮ ስለሚወጣ ነው። ይህ መሆንና መደረግ ሲኖርበት፣ ደካማውና ብቃት አልባው የኢህአፓ አመራር    አላደረጉትም።

ሀወሓት የኢህአፓውን ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠን ሌሎች ታጋዮችን ለማጥቃት ቀናት እንደቀሩት አሲምባ ውስጥ የነበርው የኢህአፓ  አመራር ጓዛቸውን ተሸክመው ሶቦያ ወረዱ። መነኩሳይቶ ለነበሩ ጀብሃ – ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ – ጨለማን ተገን በማድረግ እጃቸውን ሰጡ። በነጋታው ደቀመሃሪ፣ ኤርትራ ወረዳ “ደርሆ ማይ” ወደ ተባለው ቦታ በሌሊት ወሰደው በመኪና ጭነው ሱዳን፣ ካርቱም አደረሷቸው።

የህወሓት አመራር የኢህአፓ ደካማ ጎኑን ለረጅም ጊዜ ያጠናው ስለነበር በተለያዩ የኢህአፓ ነፃ ክልል የተመደቡ ኢህአሠና ታጋዩ አመራሩ ቦታውን ለቆ ሌላውን መርዳት እንደማይፈቅድ ያውቃሉ።

የኢህአፓን ተዋጊ ክንፍ ኢህአሠን ለመደመሰስ የወጣው ፕላን

ጥቃቱ የተጀመረው ታህሳስ 1972 ሆኖ፣ የውጊያው ሁኔታ ከፋፍለው ያስቀመጡትን የህወሓት አመራር፣ ማለትም፣ አረጋዊ በርሄ ወታደራዊ አዛዥ፤ ስብሃት ነጋ የህወሓት ሊቀመንበር፤ መለስ ዜናዊ፤ አባይ ፀሃየ፤ ሥዩም መስፈን፤ አርከበ አቁባይ፤ አዋውአሎም ወልዱ፤ ጻድቃን ገብረተንሳይ፤ ስየ አብርሃ በዋናነት፤ ከህወሓት ተዋጊ አመራር፣ ሃየሎም አርአያ፣ ሳሞራ የኑስ ወዘተ ጋር በመሆን ጥቃቱ ተጀመረ።

የመጀመሪያው የጥቃት ኢላማ አጋሜ አውራጃ የሚንቀሳቀስ የኢህአሠ አሲምባ ሶቦያ አካባቢ በነበረው ላይ ጦርነቱ ተጀመረ። ረዳትና አስተባባሪ አመራር ሰጪ በማጣቱ፣ ለሶስት ቀን በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት እንደቆየ ተጠቃ፣ ሊከፍለል የማይገባውን ከባድ የህይወት መስዋእትነት ከፈለ። ህወሓት የቆሰልውን ኢህአሠን ድገመው (አዳግመው) እያሉ ጨረሱት። የታጠቀውን ትጥቅ፣ ጥይት፣ ቦምብ፣ ራዲዎ መገናኛ የሞተውን እያገላበጡ ዘርፈው የኢህአሠን ትጥቅ ታጥቀው ፊታቸውን ወደ ሌላ ቦታ አዞሩ።

ለቀጣዩ ጦርነት በፍጥነት ፊታቸውን ያዞሩት ወደ መሃል ትግራይ ወደነበረው ኢህአሠ ገሰገሱ። በድንገት ገብተው የጥቃት እርምጃ መውሰድ ሲጀምሩ እንዳሰቡት በቀላሉ የሚጠቃ ባለመሆኑ ኢህአሠ የመከላከል ጥቃቱን ከፋፍሎ በሃውዜን፣ በነበለት፣ በፈረሰማይ ወዘተ ስለነበር፤ የህአሠ ተዋጊ ቦታውን በሚገባ ስለሚያውቀውና ከአካባቢው ህዝብም ጥሩ መተበባር ስለነበረው አስቀድሞ የውጊያ ቦታውን በመያዝ እንዳለ የህወሓት ሃይሎች ጥቃት ቢከፍቱም በኢህአሠ አጸፋዊ ጥቃትና መልሶ ማጥቃት ወያኔዎች ሊቋቋሙት አልቻሉም። የህወሓት ታጋዮች ሙትና ቁስለኛ ሆነ። ውጊያውን ይመራ የነበርው አመራር ከአቅሙ በላይ ስለሆንበት ሌላ ተጨማሪ ሃይሎች በማስመጣት እንደ አዲስ ጥቃት ከፍቶ ኢህአሠን አዳከመው። በኢህአሠ በኩልም ወልቃይት ፀገዴ ያለው የኢህአፓ አመራር እዛ ያለው የኢህአሠ ሰራዊት ለእርዳታ እንዲመጣለት ሲጠይቅ የተሰጠው መልስ ክልላችንን ትተን እናንተን ለመርዳት አንመጣም የሚል ነበር። ጥቂት ታጋዮች በረሃው ወደመራቸው አፈግፍገው ህይወታቸውን አዳኑ። ኢህአሠ በዚሁ ውጊያ በጀግንነት ተዋግተው ከባድ መስዋእትነት ከፍለዋል። ህወሓት ኢህአሠን አጥፍቶ በዘረፈው ትጥቅና ጥይት ትምበሸበሸ፣ ሙሉ ሰራዊቱን ክላሺንኮፍ አስታጠቀ።

ቀጥሎም ፊቱን ያዞረው ወደ ወልቃይት ጸገዴ ነበር። በዛ ክልል የነበሩ አመራር አስቀድመው ደብዳቤ ወደ ህወሓት በመላክ እጃችንን እንሰጣለን፣ ተቀበሉን በማለት ገና ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እጃቸውን ሰጡ። በአጠቃላይ ወደ 35 የሚሆኑ በቀጥታ በህወሓት ታጋዮች እየተመሩ ተምቤን ገቡ። ወያኔ ተቀበላቸው። የተቀበላቸው የድርጅቱ የስለላ ሃላፊ የነበረው ተክሉ ሃዋዝ ነበር። ሽሉም እምኒ በተባለችው ጎጥ እንዲያርፉ ተደረገ። በህወሓት ታጋዮች ጥብቅ ቁጥጥር እንደ ግዞተኛ ይጠበቁ ነበር።

ወልቃይት ጸገዴ አካባቢ የነበረው ኢህአሠ አምስት ሃይሎች ሲሆኑ ወያኔ ያለውን የሌለውን ሃይል ወየንቲ/ምልሻም/ ተጨምረው ጥቃት ጀመረ። ኢህአሠ አካባቢውን ስለሚያውቀው ካባድ መከላከል በማድረግ ቀላል የማይባል የህወሓት ታጋዮች ገድለዋል። ይህንን ጦርነት ሲመራው የነበረው ስብሃት ነጋ ለትንሽ ከእጃቸው አመለጣቸው። ብዙ የወያኔ ሃይል አመራር ተገድለዋል። ጦርነቱ ወያኔን ለከባድ ሽንፈት አድርሶት ነበር። ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ሌላ ተጨማሪ ሃይል መጥቶ ውጊያው በክፉ መልኩ ቀጠለ። አርከበ እቁባይ የቀኝ እግሩ ቋንጃው ተመትቶ ስለቆሰለ በቃሬዛ ተሸክመውት ሸሹ። አሁንም ሌላ ተጨማሪ ሁለት ሃይሎች በበርሄ ሻእቢያና በታደሰ ወረደ የሚመሩ ተጨምረው ኢህአሠ የያዘው ጥይትና ቦምብ እያለቀ በመሄዱ ከባድ መስዋእትነት ከፍሎ በመጨረሻ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የተወሰኑት ታጋዮች ከጦርነቱ ጉዳት ደህና የነበሩ ኢህአሠ ተመከካረው ወደ መተማ አቅጣጫ አፈገፈጉ። የወሰዱት እርምጃ ትክክለኛ ነበር። ህዝቡም በየሄዱበት በመተባበር አስፈላጊውን እርዳታም በማቅረብ ወደሚፈልጉት ቦታ ሸኛቸው።

ባጭሩ ለኢህአፓ የተሰለፈው ተዋጊ ሰራዊት ኢህአሠ ኢትዮጵያዊ ራእይ ያለው፣ የነቃና ብቃት የነበረው ቢሆንም “የአሳ ግማቱ ከአናቱ” እንዲሉ የኢህአፓ አመራር ደካማና ብቃት የሌለው ስለነበር ሠራዊቱን እንደ ወያኔ ላለ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ህዝብ ሃይል አጋልጦ ለውድቀት ዳርጎታል።

በኢትዮጵያ አርበኝነት ከሚወሱት የኢህአሠ ተዋጊዎች በተቃራኒ ደግሞ፣ ሰራዊቱ ሲፈርስ እጃቸውን ለወያኔ የሰጡትና ዛሬ እራሳቸውን ብአዴን ብለው የሚጠሩት ግንባር ቀደም የወያኔ ስርአት አስፈጻሚዎች፣ ዋናዎቹ የኢህአፓ ጥፋትና ወድቀት ማስታወሻዎች ሆነው ይገኛሉ።

ኢህአፓ ጠንካራ ጎኖችም የነበሩት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም። ዘውዳዊው ስርዓት ተንኮታኩቶ እንዲወድቅ ማድረጉና መሬት ላራሹ የመጀመሪያ መፈክሩ ተግባራዊ መሆኑና ሌሎችም አሉት።

የብአዴን አፈጣጠርና አመጣጥ!! መሪዎቹስ እነማን ከየትስ ናቸው?

ሽብርተኛው “terrorist” ቅጥረኛ “mercenary” ህወሓት፣ ኢህአሠን ካጠፋ በኋላ ፊቱን ያዞረው እጃቸውን የሰጡት ወዶ ገቦችን አስልጥነን በፕሮግራማቸው ብሄረ አማራ የመሰሉ ነገር ግን ፀረ-አማራ ሆነው ኢንዲቆሙ ማድረግ አለብን ተብሎ በወቅቱ የነበሩ የህወሓት አመራር፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አረጋዊ በርሄ፣ አባይ ፀሃይ፣ ስዩም መስፍን፤ አውአሎም ወልዱ፤ አርከበ እቁባይ፣ ስየ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ ዘርአይ አስገዶም፣ አስፍሃ ሃጎስና የህወሓቱ ም/ሊቀመንበርና የድርጅቱ ዋና አስተዳዳሪ ግደይ ዘርአጽዮን በዚህ አርእስት ላይ አጀንዳ ቀርቦ ሲወያዩ ም/ሊቀመንበሩ ግደይ ዘርአጽዮን ይህንን ሃሳብ አልቀበልም በማለት ራሱን አገለለ። የተቀሩት ውይይቱን ቀጥለው ስምምነት ላይ ደረሱ። የግደይን ስም ለማጥፋት በዚህ ጉዳይ ላይ የታሰፉ አመራር፣ ግደይ የድርጅቱን ሃሳብ በመቃወም ችግር እየፈጠረብን ነው በማለት በደፈናው የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፈቱበት።

ከላይ ከተዘረዘሩት የመጀመሪያዎቹ 12ቱ የህወሓት አመራር ተሰባስበው፣ ተወያይተው ስምምነት የደረሱበት አማራ ጠላት እንደመሆኑ በራሳችን ትእዛዝና እንቅስቃሴ የሚታዘዝ ድርጅት ከፈጠርን አማራው ህልውናው የሚጠፋበት አማራጭ መንገድ ከዚህ የበለጠ ስለሌለን ፕሮግራሞቹን ጽፈን ሙሉ ቁጥጥር እያደረግን እነዚህን የኢህአፓ ወዶ ገቦች እናደራጅ ተብሎ ውሳኔ ተላለፈ።

በዚህ ውሳኔ መሰረትም መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ ለሚመሰረተው የአማራ ድርጅት ፕሮግራምና የቅድመ ሁኔታ ውይይት እንዲያዘጋጁ ሃላፊነቱ ተሰጣቸው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት አመራር ያዘጋጁት ለህወሓት ፖሊት ቢሮ ስብሰባ ቀርቦ፣ እነ አረጋዊ በርሄና ስዩም መስፍን አንድ ላይ ሆነው የቀረበውን ጽሁፍ አንብበው ፕሮግራሙ ላይ ተስማሙበት። ይህም በዋናነት እጃቸውን የሰጡ የኢህአፓ አባላት ውይይቱን የሚመሩ ሶስት ሆነው ወዶ ገቦቹን አሳምነው መስራች ጉባኤ ተካሂዶ ፕሮግራሙን አምነው ተቀብለው በህወሓት እርዳታ የአማራ ብሄር ድርጅት ተመስርቶ እንዲቋቋም ተብሎ ተወሰነ።

በፕሮግራሙ መሰረት የመወያያ አርእስቶች

ውይይቱ የተጀመረው ግንቦት መጨረሻ 1972 ሲሆን፣ የውይይቱ መሪዎች መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፤ ሲሆኑ ተጠባባቂ ረዳቶች ደግሞ አውአሎም ወልዱና አርከበ እቁባይ ሆኑ። የመወያያው ር ዕስ፣

  1. ነፃ ሃገር የነበረችው ኤርትራ ዛሬ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ስር ወድቃ ህዝብ ለመከራና ለችግር ተዳርጓል። ከህዝባዊ ሓርነት ኤርትራ ጋር በመተባባር ኤርትራን ነፃ እናወጣለን፣
  2. ነፃ ሃገር የነበረችው ትግራይ፤ የራሷ መንግሥትና መስተዳድር የነበራት ሃገር፣ ከአፄ ዮሐንስ ሞት በኋል በምኒልክ ተወራ በአማራው ቅኝ አገዛዝ ቀንበር መውደቋ፣
  3. የአሁኗ ኢትዮጵያ የታሪክ ድሃና ታሪክ የሌላት ሃገር፣ በአፄ ምኒልክ የተመሰረተችና ከ100 ዓመታት ያነሰ ታሪክ ያላት ሃገር መሆኗን አምኖ መቀበል፣
  4. ምኒልክ ግዛቱን ለማስፋፋት በመነሳት ሳይወድ በግድ ኢትዮጵያዊነትህን ተቀበል ተብሎ በአማራው የመንግሥት ስርዓት በስቃይና በችግር የሚገኙት ብሄር በሄረሰቦች የራስን እድል በራስ በመወሰን እስከ መገንጠል አምኖ መቀበል። በዚህም ላይ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ወህኒ ቤት መሆኗን አምኖ መቀበል፣
  5. አማራ የሚባለው ጨቋኝ ፀረ-ሕዝብ መሆኑን አምኖ መቀበል።

እነዚህ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱት ዋናውና የሚፈጠረው የአማራ ድርጅት የሚመራበት ፕሮግራም ሆነው ለውይይት ቀረቡ።

ይህንን ውይይት የህወሓት አመራር አባይ ፀሃየ፣ ሊቀመንበር፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ ሆነው በመቅረብ ከሰኔ ወር መጀመሪያ 1972 እስከ ህዳር መጨረሻ 1973 ለ6 ወር ተከታታይ ውይይት ሲካሄድበት፣ በዚህ ጊዜም አዳዲስ የኢህአፓ አባላትም ሲቀላቀሉ ነበር። አብዛኛዎቹ ይህ ፕሮግራም ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሉአላዊነትና ፀረ-ሕዝብ ነው ይሉ ነበር።

የኢትዮጵያ ህዝብ በብዙ ሺህ ዘመናት የዳበረ ወንድማማችነት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ በጋብቻ፣ በባህል፣ በእምነት በአንድነት ሆኖ ሃገሩን ኢትዮጵያን ከባእዳን ወራሪዎች ተከላክሎ ለኛ አስረክቦናል። በህዝባችን ያልነበረና ያልታየ ፕሮግራም ተሸክመን አንታገልም ሲሉ፣ ከፈቀዳችሁ ፕሮግራሙን ራሳችን ጽፈን ለአንዲት ኢትዮጵያ፣ ለአንድ ህዝብ እንዲታገል ፍቀዱ። አማራ የህዝብ ጠላት ነው የምትሉት እኛም አማራ ነን፡፡ ኩሩውን አማራ የኢትዮጵያ የህዝብ ጠላት ነው ብላችሁ አትፈርጁት፣ በማለት እልህና ንዴት እንዲሁም ብስጭት በተቀላቀለበት ለወራት ከተወያዩ በኋላ ተሰብሳቢው በሶስት ተከፈለ።

  1. በህወሓት ፖሊት ቢሮ ተረቆና ተዘጋጅቶ የቀረበውን ተቀብላችሁ ታገሉ የምትሉንን አንቀበለውም። በአማራው ህዝብ እውቅናም ውክልናም አልተሰጠንም። አማራውን ብቻ መነጠል ጠባብ አስተሳሰብነው፣ በዚህም ላይ አማራ ጠላት ነው እያላችሁን አማራውን ለክፉ ስቃይ አንዳርገውም። አማራ ኢትዮጵያዊ ነው፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ይታገል፣
  2. ጊዜ ስጡን፣ በረጋ መንፈስ አንብበን እና ተረድተን መልስ እንስጥበት የሚሉ፤
  3. በህወሓት የቀረበልን ፕሮግራም ለብዙ ወራት ገንቢ ውይይት ያካሄድንበት ትክክለኛ የአቋም ፕሮግራም መሆኑን ስለአመንበት ካለምንም ተቃውሞና ጥርጣሬ ተቀብለነዋል ያሉ ናቸው።

ከዚህ ተከትሎ ምን ተፈጠረ የሚለውን ባጭሩ እንመልከት። እንደሁኔታው ተራ ቁጥሩ ይለዋወጣል።

  1. ጊዜ ስጡን፣ በረጋ መንፈስ አንብበን መልስ እንሰጥበታለን ያሉት፣ ትንሽ ጊዜ ለማግኘትና ሕይወታቸውን ለማዳን የሚጠፉበትን እቅድ ማውጣት ላይ ተሰማሩ። ጋሻው ከበደ፤ አያሌው ከበደ፣ ምትኩ አሸብር ከማስታውሳቸውና ሌሎችንም ጨምሮ፣ የተወሰኑት ወደ ሱዳን፣ የተወሰኑት ደግሞ ለኢትዮጵያ መንግሥት እጃቸውን በመስጠት ሕይወታቸን አዳኑ። አሁንም በሕይወት አሉ።
  2. በህወሓት ፖሊት ቢሮ ተረቆ የተዘጋጀውን ፕሮግራም አንቀበልም ያሉት በህወሓት አመራር ላይ ጭንቀት ስለፈጠረበት የተወሰኑ አመራር ተሰብስበው፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስየ አብርሃ፣ መለስ ዜናዊ፣ አውአሎም ወልዱ፣ አርከበ አቁባይ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይና ስዩም መስፈን ተሰብስበው እነዚህን የህወሓት ሃሳብ ያልተቀበሉትንአፈንጋጭ በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ሰጡ። በውሳኔው መሰረት በስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሃላፊነት እንዲፈጸም ተወሰነ። በዚህ ጊዜ ሃለዋ ወያነ (06) በዙ እስረኞች ሞትን የሚጠባበቁ ስለነበሩ፣ የቦታው ርቀትን ጨምሮ ሃሳቡ ቀርቦ ከህዝብ ግንኙነት አባላትም ተጨምረው ግድያው እንዲፈጸም ተደረገ።

ግደያውን የሚያስፈጽሙት፣ ብስራት አማረና ሃሰን ሹፋ እንዲሆኑ ፖሊት ቢሮው ወሰነ።

1. ከወርዲ ሃለዋ ወያነ በአበበ ዘሚካኤልና ዘርአይ ይህደጎ የሚመሩ ተጨማሪ 5 ታጋዮች

2. ፃኢ ሃለዋ ወያነ በወልደሥላሴ ወልደሚካኤልና በተስፋየ መረሳ (ጡሩራ) የሚመሩ 5 ታጋዮች

3. ከህዝብ ግንኙነት

ለኡል በርሄ፣ አብያ ወልዱ፣ ሃይሉ በርሄ፤ ቢተው በላይና ወልደ ገብርኤል ሞደርን። ሁሉም ተሰብሰበው ተምቤን ውስጥ አምበራ መጡና ገቡ። ግደያውን የሚፈጽሙት ብስራት አማረና ሃሰን ሹፋም መጥተው ከእነ ታምራት ላይኔ ጋር ቆዩ። ስብሃት ነጋም መጣና ከነብስራት አማረ ጋር ተነጋገረ። እነታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን ወዘተ ከነበሩበት ቤት ራቅ ባለ ቦታ የመረሸኛ ጉድጓድ ተቆፍሮ ተዘጋጅቷል። እነዚህ በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አንቀበለም ያሉት ቁጥራቸው በርካታ ነው። ስብሃት ነጋ ለልዩ ስብሰባ ብሎ በሃለዋ ወያነ አባላት ታጅበው ሄዱ። አባላቱ እጃቸውን በገመድ ጠፍረው በማሰር ወደ ተዘጋጀው መግደያ ጉድጓድ ወስደው በጥይት ደብድበው ገደሏቸው። ሁሉም አማራ ሲሆኑ፣ ሃይላይ የሚባል አንድ የትግራይ ልጅ ከነሱ ጋር ነበር።

ይህ ፋሽስታዊ ተግባር እንደተፈጸመ በሶስተኛው ቀን በጣም አሳዛኝና አስደንጋጭ ወሬ በህወሓት ታጋይ ተናፈሰ። ወሬውን የበተኑት በግድያው የተሳተፉት የሃለዋ ወያነ አባላት እነ ሃሰን ሹፋ፣ አበበ ዘሚካኤል፣ ተስፈየ መረሳ ወዘተ ከህዝብ ግንኙነት ተመርጠው የመጡ ልኡል በርሄ፣ ቢተው በላይ በህወሓት ውስጥ ኦቦራ አስነሱ። የህወሓት ታጋይ ሁሉም ማለት ይቻላል፣ ተናደደ፣ አበደ። በዚህ ጊዜ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ፈርተው ተደበቁ። እነብስራት አማረም ፈርተው ባኽላ ሄደው ተደበቁ።

በዚህ በተሰራጨው ወሬ ጠንከር ያሉ አመራር ስለነበሯቸው በተረጋገጠው ዜና የእንቅስቃሴው መሪዎች የነበሩ፣ ከልካይ ጎበና፣ አስራደው ዘውዴ፣ ዳኛቸው ታደሰና ሃይላይ፣ አክራሪ አማሮች፣ የነፍጠኛ ልጆች የተባሉ በነበሩበት ወቅት በፋሽስት ህወሓት አመራር ለህልፈት በቅተዋል።

በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አምነን ተወያይተን ገምቢ ፖሊሲውን ተቀብለናል ያሉት እነዚህ ናቸው፣

  1. ሙሉአለም አበበ፣ አማራ                                    7. ህላዊ ዮሴፍ፣ ኤርትራ
  2. ሃይለ ጥላሁን፣ ትግራይ፣ እድገቱ ጎጃም            8. ተፈራ ዋልዋ፣ ሲዳማ
  3. ታምራት ላይኔ፣ ከንባታ                                     9. ታደሰ ካሳ፣ ትግራይ
  4. ዮሴፍ ረታ፣ ትግራይ፣ ኤርትራ                         10. መለሰ ጥላሁን፣ አማራ፣ ትግራይ
  5. በረከት ስምኦን፣ ኤርትራ                                   11. ሲሳይ አሰፋ፣ ትግራይ
  6. አዲሱ ለገሰ፣ ሂርና ሃረር                                      12. ኢያሱ በላቸው፣ ትግራይ፣ አማራ

ማሳሰቢያ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ትወልድ ቦታቸውን ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖብኝ ለዓመታት ብቆይም፣ ዛሬ ግን ከሚያውቋቸው ሰዎች ጠይቄና አፈላልጌ ትክክለኛውን የትውልድ ቦታቸውን በማያያዝ ይህን ጽሑፍ አቅርቤአለሁ።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ናቸው የአማራ ህዝብ ድርጅትን ለመመስረት ህወሓት ያዘጋጀው። ህዋሓት ሲፈጠር በሻእቢያ ነበር። ያደረገው ነገር ድርጅቱ በኤርትራውያን እና ከትግራይ የተፈጠሩ ባንዶች በማቀናጀት ህወሓትን ፈጠረ። ለምን ይህ ነገር ተደረገ የሚል ጥየቄ ከተነሳ፣ ሻእቢያ የትግራይና አማራውን ህዝብ ስለሚጠላ ህወሓት በህዝቡ ላይ ጥቃት ይፈጽማል በሚለው ፖሊሲ መሰረት ነው። ህወሓት በወቅቱ ተሓህት ገና ከመፈጠሪያ ትግሉ መነሻ ጀምሮ በትግራይና በአማራው ህዝብ ላይ የፈጸመው ግድያና እልቂት የአማራውን እና የትግራይ ህዝብ ያውቀዋል። ከዚህ በመነሳት ህወሓት የፈጸመውና እየፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል የዓለም ህዝብ ያወቀው እውነት ነው። አሁን ደግሞ ብአዴን በአማራው ላይ የሚፈጽመው ወንጀል አደባባይ የወጣ ሃቅ በተግባር እየታየ ነው።

ከዚህ ከአፈጣጠሩ ተነስተን ብአዴን ማን ነው? እውነትስ የአማራውን ህዝብ ይወክላል? ለሚሉት መልስ ለመስጠት እነማን ናቸው የአማራ መሪ ድርጅት ብለው የሰየሙት? ከየትስ መጡ? ብዙ ጥያቄ ሊነሳ ይገባል። ለዚህ ሁሉ መልስ ግን ይህ ጽሑፍ ሙሉ መልስ የሚሰጥ ነው። በእርጋታና በጥሞና አንብቡት። የአማራው ህዝብም ብአዴን አማራን አትወክልም፣ አናውቃትም በማለት እምቢ አልገዛም ማለቱ ትክክለኛ የትግል መስመር ነው። ቀሪው ኢትዮጵያዊም ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ደቡብ ህዝብ፣ የሁላችንም መልስ አንድ ነው። ህወሓት ዘረኛና ፋሽስት ነው፣ አጋር ድርጅቶችም የህወሓት ተግባር አስፈጻሚ ናቸው።

ህወሓት ምን መብትና ሃላፊነት አለው ለአማራ፣ ለኦሮም፣ ለደቡብ፣ ለአፋር ወዘተ? ድርጅት የሚመሰርተውስ ህወሓት ራሱ ማን ነው? በቅጥረኝነት የተፈጠረ የባንዳ ስብስብ የተለያዩ ድርጅቶች መስርቶ ኢትዮጵያን ሊበትን የመጣ መብቱን ማን ሰጠው? ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ከነዚህ የቀን ጅቦች የሚገላግለው ራሱ ነው።

ሐምሌ 1973 የህወሓት ፖሊት ቢሮ ያዘጋጀው የኢህዴንን ፕሮግራም በመያዝ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አርከበ እቁባይ አምቦራ መጡ ልዩ ስሙ ሸሉም እምኒ ቁሽት በመሄድ ቀኑም የተቆረጠ ስለነበር ከኢህዴን አባላት ጋር ተገናኙ። በፕሮግራሙ ላይ ለአጭር ጊዜ ከተወያዩ በኋላ የብአዴን ፕሮግራም መሆኑን በድጋሚ ባማረጋገጥ ተቀበለው። የኢህዴን መስራች ጉባኤ እንዲመሰረት ተደረገ። በዚህ መስራች ጉባኤ አምስት ሰዎች ብቻ ስለሚፈለጉ በእቅዱ መሰረት ምርጫው ተካሄደ። በምርጫውም ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ህላዊ ዮሴፍና ተፈራ ዋለዋ ሲመረጡ፣ ሊቀመንበሩ ታምራት ላይኔ ሆነ።

መስራች ጉባኤ እየተባለም እስከ 1975 ቆየ። ለዚህ ምክንያት ካለ 12ቱ የኢህዴን ሰዎች ማንም ከትግሉ የሚቀላቀል አልተገኘም። ኢህዴን ወይም የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እየተባለ የመጣው ዋና ዓላማው የኢትዮጵያ ታጋይ እየተባለ ድጋፍና ታጋይ ወጣቶች ከአማራውና ከሌላውም ለማግኘት ህወሓት ያቀደው ዓላማ ነበር። ቢሆንም፣ አንድም አልተገኘም፣ ድጋፍም አላገኘም።

ህወሓት በኢህዴን ተስፋ በመቁረጥ ከራሱ 50 የህወሓት ታጋይ ጨመረለት። እነዚህ ደግሞ 12ቱን ግዞተኞች የሚከታተሉና የህወሓት ታጋዮች በሚሉት ስለሚመሩ መብት አልነበራቸውም።

የህወሓት አመራር የኢህዴን 1ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የት ይደረግ የሚለው ሃሳብ ከተወያየ በኋላ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ሐምሌ 1975 ዋግ አካባቢ እንዲሆን ሲወሰን ህወሓት ደግሞ ሙሉውን የጉባኤ ወጪ ሸፍኖ እንዲዘጋጅ ተደረገ። በዚሁ ጉባኤ የህወሓት አመራር ትኩረት የሰጠው እነማን ጉባኤውን ይምሩት በሚለው ላይ ነበር። በህወሓት ውሳኔ መሰረት በሊቀመንበርነት ጉባኤውን የሚመሩ መለስ ዜናዊ፣ ሊቀመንበር፣ አባይ ፀሃየ፣ ከህወሃት፣ ህላዊ ዮሰፍ፣ ብአዴን ተብሎ ተወሰነ።

በፕሮግራሙ መሰረት በመለስ ዜናዊ ሊቀመንበርነት የኢህዴን ጉባኤ ተጀመረ። ለአንድ ቀን በተለያዩ ጉዳዮች ከተወያዩ  በኋላ በሁለተኛው ቀን 1ኛው የብአዴን አማራውን የሚወክል አርማና ባንዲራ ማጽደቅ፣ 2ኛ የብአዴን አመራር መምረጥ ሲሆን በአንደኝነት የተጠበቀው አልተዘጋጀም ተብሎ ለ2ኛ ጉባኤው ሲተላለፍ፣ መረጣው ግን ቀጠለ። ከዚህ በታች የሚታየው ስም ዝርዝር የአማራ ህዝብ አመራር ናቸው። ከአማራው ህዝብ አብራክ የተወለዱት አማሮች እንደመሆናቸው አማራውን ይመሩታል በማለት በህወሓት የማጭበርበር ዘዴ መለስና አባይ እየተቀባበሉ ተናግረው ምርጫው ቀጠለ።

ተ.ቁ

ስም ከነ አባት

የትውልድ ቦታ

ሃላፊነቱ

1 ታምራት ላይኔ (ጌታቸው ማሞ) ከንባታ የብአዴን ሊቀመንበር
2 በረከት ስምኦን ኤርትራ ም/ሊቀመንበር
3 አዲሱ ለገሰ ሂርና፣ ሐራር
4 ተፈራ ዋለዋ ሲዳማ ፕሮፓጋንዳ ቢሮ
5 ዮሴፍ ረታ ኤርትራ
6 መለሰ ጥላሁን አማራ፣ ትግሬ
7 ህላዊ ዮሴፍ ኤርትራ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
ተ.ቁ

ተለዋጭ ማ/ኮሚቴ ስም ከነአባት

የትውልድ ቦታ

1 ታደሰ ካሳ ትግራይ
2 ሙሉአለም አበበ አማራ

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በጉባኤው ተመረጡ። ኢህዴን የሚለው ስም ተለውጦ ብአዴን (ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ተብሎ ተሰየመ። የአማራ መሪ ድርጅት ሆነ። ቀደም ብለው የተነሱ ጥያቄዎች ብአዴን ማን ነው? ከየትስ መጡ? እነማንስ ናቸው? ወዘተ ለሚሉትጥያቄዎች መልሱ ይህ ነው። እውነትስ ብአዴን የአማራውን ሕዝብ ይወክላል? መልሱ ፈጽሞ አማራውን የሚወክል ድርጅት አይደለም ነው።

ህወሓት ለራሱ ትግል የተነሳው ኤርትራን አስገንጥሎ የትግራይ መንግሥት እናቋቁማለን ብሎ ነው ፕሮግራሙን አዘጋጅቶ የካቲት 1967 ደደቢት በረሃ የወረደው። በምን መልኩ ነው ደመኛ ጠላቴ ለሚለው አማራ ድርጅት ብአዴንን ሊፈጠርለት የቻለው? ህወሓት ምን መብትና ሃላፊነት አለው? ማንስ ሰጠው? ህወሓት ይህን ሁሉ የፈጠረው የአማራውን ህዝብ ከዘር ማንዘሩ ሊያጠፋልኝ ይችላል ብሎ ነው የብአዴንን ቅጥረኞች “mercenary” የፈጠረው። ሌላውም ህወሓት ለአማራ ድርጅት መፈጠር ቅንጣት የምታክል መብት ፈጽሞ የለውም። ስለዚህ ብአዴን ፀረ- አማራ ቅጥረኛ ድርጅት ነው።

እነዚህ ወዶ ገቦች ብአዴን ከህወሓት እንደተቀላቀሉ በተግባር ያሳዩትን ግፍ ባይናችን አይተናል። የኢህአፓ አባላትና ደጋፊዎች እያሉ በወልቃይት፣ በፀገዴ፣ በጸለምት መሪ ሆነው ለህወሓት በመጠቆም ስላማዊ ዜጋውን አማራ አስጨርሰዋል። ንብረቱ በህወሓት እየተወረሰ ተገድሏል። ህፃን፣ ሽማግሌ፣ ሴት ሳይለይ እነበረከት ስምኦን በነስብሃት ነጋና አርከበ እቁባይ ትብብር ሙሉ ቤተሰቦች በሚኖሩበት የሳር ቤት እያስገቡ በላያቸው ላይ እሳት ለኩሰው አቃጥለው አስገድለዋል። በተመሳሳይ መንገድ ታምራት ላይኔ፣ ታደሰ ካሳ፣ መለሰ ጥላሁን እና ህላዊ ዮሴፍ ህዝቡን ቤት ውስጥ በማስገባት በእሳት በማቃጠል ጨርሰዋል። የወልቃይት ከሞት የተረፈው የፀገዴና ጸለምት ህዝብ ላይ የተፈጸመበትን ግፍ ይውጣና ራሱ ይመስክር። ምስክርነትህን ጮክ ብለህ አሰማ።

ብአዴን ከ1972 መጨረሻ ጀምሮ በአማራው ላይ አሰቃቂ ግፍ እየፈጸመ የመጣ ፀረ-አማራ የሆነ ቅጥረኛ “mercenary” ድርጅት ነው።

አዲሱ ለገሰ ወያኔ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በተወለድኩበት ለዘመናት የቆዩትን አማሮች ዘር እየለየ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎችን አልገድልክም? አፈናቅለህ አላባረርክም? በምን መልኩ ነው አንተ ወንጀለኛና ፋሽስት አማራውን የምትወክለው? ብአዴን ሁላችሁም ግፍ የፈጸማችሁና በደም የታጠባችሁ ናችሁ።

ብአዴን የአማራውን ህዝብ ባህልና ወግ የማያውቅ ስለሆነ የአማራ መሪ ድርጅት የመሆን መብትና ሕጋዊነት የለውም። በአንጻሩ ብአዴን ፀረ-አማራና አማራውን ለማጥፋት በህወሓት የተፈጠረ ነው።

የብአዴን 2ኛው ጉባኤ በ1981 ዋግ አውራጃ አውሰን ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲካሄድ፣ ብአዴን ያሳየው እድገት አልታየም። ሐምሌ 1975 የተመረጠው አመራር በድጋሚ ተመረጡ። አሁንም 12 ሰዎች ናቸው።

በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ሀገራችን ወደ ጨለማ ጉዞ እያዘገመች ነበረች። ትናንትና ደህና የነበረው፣ ዛሬ አስደንጋጭ ሁኔታ ይዞ ብቅ ይላል። ደርግ ትግራይን ለቆ በመውጣቱ ህወሓት ትግራይን የመቆጣጠር እድል ስላገኘ፣ የአሜሪካ የስለላው ማእከል CIA ባለሥልጣናት መቀሌ ድረስ በመሄድ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስተካከል ተባበሩት። ህወሓት ትግራይን ነፃ ለማውጣት በተላበሰው አልባሳት ላይ ሌላ ካባ ደረበበት። መስከረም 1982 እንደርታ አውራጃ ሰምረ ወረዳ ባኽላ ቁሽት ግዞተኛ የነበረው ብአዴን አመራሩ በሙሉ ተጠርተው መቀሌ ገቡ። የመጡበት ምክንያት ለስብሰባ መሆኑ ተነገራችው።

ስብሰባው ሁሉም የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባላት፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ስየ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ አርከበ እቁባይ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ክንፈ ገ/መድህን እና ጻድቃን ገ/ተንሳይ ሲሆኑ፤ በብአዴን በኩል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ዮሴፍ ረታ፣ መለሰ ጥላሁን፣ ህላዌ ዮሴፍና ተደሰ ካሳ ናቸው። በዋናው አጀንዳ ከተነጋገሩ በኋላ በመጨረሻ ብአዴን የህወሓት አጋር ደርጅት መሆኑ ተገለጸላቸው። በዚህ መሰረትም ህወሓትና ብአዴን በመሆን ኢህአዴግ (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር) ተብለው እንደሚጠሩ ተወሰነ። የቀኑ ውሎ ሁኔታ እንደመግቢያ ተደርጎ “ድምፂ ወያነ” ልክ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ታወጀ፣ በጽሑፍም ተበተነ።

እኔ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በወቅቱ የነበርኩት አዲስ አበባ ስለሆነ በጊዜው የነበረውን የኢትዮጵያ መንግሥት ህወሓት በትግራይ ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በየሰዓቱ በሚስጥራዊ ሥራው ይከታተለው ስለነበር ከላይ ያስቀመጥኩት ሁሉ በተገኘው የስለላ መስመር ሁሉም በዝርዝር ተነገረኝ። ዛሬ ማታ በ12 ሰዓት በድምፂ ወያነ እንድከታተለው ተነገረኝ። ጠቅላላ የመረጃውን ጽሑፍ እንዳነበው ተሰጠኝ። አንብቤም አንዳንድ ነጥብ በማስታወሻ እንድጽፈው ፈቃድ ስጠይቅ ይቻላል፣ ምንም ችግር የለውም ተባልኩ። አስፈላጊውን ወሰድኩ። ቤቴ ሂጄ ልክ በ12 ሰዓት ድምፂ ወያነን ከፍቼ አዳመጥኩ። የደህንነቱ የመረጃ ክፍል ያነበብኩትና የነገሩኝ ሁሉ በትክክል ቃሉ ሳይዛነፍ ድምፂ ወያነ ሴኮ በሚባል ሰው አዋጁን አስነበበ።

የደርግ መንግሥት የደህንነትና የመረጃ ሥራ በጣም ረቂቅና የተደራጀ መሆኑን ያደነቅሁት በዚህ ጊዜ ነበር። ለነገሩ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት የተማሩ ምሁራን መሆናቸውን አውቃለሁ።

የህወሓት ፋሽስት አመራር ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለማጥፋትና ለመበታተን በፕሮግራሙ ያስቀመጠው ኢህአዴግ በሚል ስም ግንቦት 20 ቀን 1983 ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ስርዓቱ እንደተቆጣጠረ 12ቱም ብአዴን “ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ”ን  አጋር ድርጅት ብሎ የሰየመው ህወሓት አቅፎት አብረው አዲስ አበባ ሲገቡ፣ ህወሓት የኢትዮጵያን ህዝብ አደናግሮ ፋሽስትና ሽብርተኛ ስርዓቱን በመላ ሃገሪቷ ዘረጋ።

ፋሽስቱ ህወሓት በሽግግር መንግሥት ስም ስርዓቱን እንደ ዘረጋ፣ ቀዳሚ ትኩረቱ ያደረገው የአማራውን ህዝብ ዘሩን ለማጥፋት ተግባራዊ እርምጃ በቅጥረኛው “mercenary” ብአዴን ታምራት ላይኔ ጠ/ሚኒስትር ሆነ። የብአዴኑ መሪ የከንባታው ተወላጅ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፀረ-አማራ ንግግር በተደጋጋሚ በመናገር ተስፋፊ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ አማራን ማጥፋት አለብን በማለት የዘር ማጥፋት ወንጀሉን ተግባራዊ ለማድረግ ተዘጋጀ።

በ1983 ከሰኔ ወር ጀምሮ በህወሓት ፋሽስቱ መሪና የህወሓት አመራር በሙሉ በሚያምኑበትና በተሰጠው ቀጭን መመሪያ በአማራውን ህዝብ በየአለበት በታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ በተፈራ ዋለዋ፣ በመለሰ ጥላሁን ወዘተ የብአዴን አመራር መሪነት የህወሓት የታጠቁ ሃይሎች በማሰለፍ በየቦታው ዘምተው በአማራ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግድያ በመፈጸም ዘሩን ለማጥፋት ዘግናኝ እርምጃ ወስደዋል። በአርባ ጉጉ፣ በደኖ፣ ቦረና፤ ጉጂ፤ ጋምቤላ ወዘተ የነበረውን አማራ ሙሉ በሙሉ ገድለው አጠፉት። ከሞት እንደ ምንም ብሎ የዳነውን፣ ውጣ አንተ ተስፋፊ፣ ትምክህተኛ ተብሎ በመፈናቀል በረሃ ላይ ወደቀ። ከህፃናት እስከ ሽማግሌ፣ ወንድና ሴት ሳይለይ፣ እርጉዝ ሴቶችን ጨምሮ በረሃ ተጥለው ለአራዊት ምግብ የተዳረገው፣ ለመጥፎና አሰቃቂ መከራ የተዳረገው፣ በህወሓትና ብአዴን የአማራው ህዝብ ነው።

በረከት ስምኦን ባደገበት ወሎ አካባቢ በሱ የሚመራው የህወሓት ታጣቂ ገዳዮች በመያዝ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግድያ የፈጸመው የብአዴን መሪ ቅጥረኛ ኤርትራዊ ነው።

አዲሱ ለገሰ በተወለደበት አካባቢ ይኖሩ የነበሩትን አማሮች በአሰቃቂ ግደያ አጥፍቷቸዋል። ከንብረታቸው አፈናቅሎ ለመከራና ችግር የዳረጋቸው የብአዴን መሪ ነው።

መለሰ ጥላሁን ባደገበት የአማራው ቦታ በህወሓት የታጠቁ ሃይሎችን በመምራት በአማራው ላይ አሰቃቂ ግፍ የፈጸመ የብአዴን መሪ ነው። የብአዴን መሪዎች ሁሉም በአማራው ህዝብ ላይ ፋሽስታዊ ግፍ  ፈጽመዋል። ታድያ እነዚህ የብአዴን አምራር ፀረ-አማራ ሆነው ተፈጥረው አንተን በምርኮኛነት እየተቆጣጠሩህ የአማራ ህዝብ መሪዎች ናቸው? መልሱ፣ አይደለም ነው።

በኢሳት ሚዲያ የተሰራጨውን ዘገባ የሰማነው በትክክል ኤርትራዊው ቅጥረኛ በረከት ስምኦን የብአዴን ሥራ አስፈጻሚና መሪ የአማራ ሕዝብ ተነስ ስንለው ይነሳል፣ ተኛ ስንለው ይተኛል፣ አድርግ ስንለው ያደርጋል በማለት የተናገረው የአማራው ህዝብ ለ23 ዓመታት እንደ ባርያ እየገዙት፣ መብቱ እየተረገጠ፣ እንዴት በእነዚህ የብአዴን ቅጥረኞች ዘሩ እየጠፋ፣ ከየቦታው እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ ሊኖር ነው? መልስ የሚሰጠው የነፃነት ግዴታው የሆነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው።

አለምነው መኮንን የተባለው ቅጥረኛ ባንዳ ህወሓት በአማራው ላይ የሚከተለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፖሊሲ ፈጻሚና አስፈጻሚ በመሆን የሚሰራው የብአዴን መሪና ሥራ አስፈጻሚ በብአዴን የካድሬዎች ስብሰባ በአማራው ህዝብ ላይ ያወረደው አስጸያፊ ስደብ በጣም ያሚያሳዝን ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን በሚገባ የተከታተልው ስለሆነ ይህንን ዘግናኝና አጸያፊ ስድብ እዚህ ባላነሳው ይሻላል። አለምነው መኮንን የተፋው ስድብ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነው የሰደበው። ሲናገርም፣ ይህ የተናገርኩት ጉዳይ የድርጅቴ ብአዴን/ኢህአዴግ አቋምና እምነትም ነው፣ በማለት በድጋሚ አረጋግጦታል።

ደመቀ መኮንን የብአዴን ሥራ አስፈጻሚ መሪ ነው። ቅጥረኛው ባንዳ በጸረ አማራነቱ የተሰለፈ በመሆኑ በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኝ ነው። በአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመነሻ ጀምሮ ከነበረከት ስምኦን፣ ህላዌ ዮሴፍ፣ ታደሰ ካሳ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ታምራት ላይኔ ወዘተ በመተባበር አማራውን ከየቦታው በማፈናቀል ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ተስፋፊ በማለት ግፍ የፈጸመ ወንጀለኛ ሲሆን፣ በተጨማሪም ክህወሓቱ መሪ መለስ ዜናዊ ጎን በመቆም የሱዳን መንግሥት መሬቴን ባለፉት መንግሥታት የኢትዮጵያ መሪዎች ስለተቀማሁ መልሱልኝ በማለታቸው በአማራው ክልል ያለው የሱዳን መሬት ነው ብለህ ፈርም ተብሎ ካለምንም ማቅማማት ፈርሞ የሰጠ ፀረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ባንዳ ነው።

ብአዴን የህወሓት ተግባር ፈጻሚ ባንዳና ቅጥረኛ በመሆኑ በአማራው ላይ ያደረሰው ጥቃትና መፈናቀል ባጭሩ እንመልከት፤

  1. በቀጥታ በህወሓት የሚፈጸሙት ግድያዎች ዘር ማጥፋት ብአዴን በዋናነት በመሰማራት ግፍ የፈጸመ፣
  2. ከህፃናት ጀምሮ እስከ 45 ዓመት ክልል ወስጥ የሚገኙትን አማራዎች የዓይን ትራኮማ መድሃኒት ነው በማለትና ሽፋን በመስጠት የማምከኛ መርፌና ኪኒኒ  ለወንዱም ለሴቱም በመስጠት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙና እያስፈጸሙ የሚገኙት የብአዴን አመራር በሙሉ ናቸው፣
  3. ከመሬቱ የተፈናቀለው አማራ ተፈናቅሎና ተበታትኖ በየቦታው እያለቀ፣ ረሃብና በሽታ በላዩ ላይ ወርዶ የሚፈጸምበት ያለ ህዝብ ነው። ይህንን ሁሉ በሰው ልጅ ላይ እየፈጸመ ያለው ቅጥረኛው ባንዳ ብአዴን ነው። ለምሳሌ ደመቀ መኮንን እና ግብረአበሮቹ እነ በረከት ስምኦን ሁሉ የብአዴን መሪዎች ከየአካባቢው ክልሎች አመራር ውስጥ ልወስጥ በምስጢር ተነጋግረው ከቤኒሻንጉል፣ ጉራ ፈርዳ፣ ወዘተ ትምክህተኛውና ተስፋፊው አማራን ከየክልላቸሁ ባሃይል አስወጡት በማለት የአማራው ህዝብ ተፈናቅሎ እንዲበታተን ያደረጉ፣ በአማራው ህዝብ ጉያ መሽጎ ያለው ብአዴን ነው። ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ሚና ተጫውተዋል። አማራው ለዚህ አስከፊ ሰቃይ የዳረገው የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ነው። ባነተ ስም ግን ይነግዳል፣ ይሾማል፣ የተንደላቀቀ ኑሮ ይኖራል። ይህንን የሰጠው ህወሓት አንተን ድርሻህን አጥፍቶ ለስደትና ለክፉ ሞት ስለዳረገህ ህወሓት ከመደሰቱ የተነሳ ነው። ታዲያስ አሁን በቃኝ ብለህ አትነሳም? ለማኝና ባሪያ ሆነህ እስከመቼ ትኖራለህ?

በአማራው እየደረሰ ያለው ሰቆቃ፣ ግድያና  ማፈናቀል በአማራ ብቻ አልተወሰነም። የህወሓት ፋሽስት ሰርዓት በሌሎች ኢትዮጵያውያንም ላይ እየፈጸመው ነው። የኦሮሞ ህዝብ በኦህዴድ፣ የደቡብ ህዝብ፣ በደህዴን፣ በትግራይ ወዘተ ከባድ ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል። የዚህ ወጀል ፈጻሚዎች ቅጥረኛ ባንዳዎች ኦህዴድ፣ ደህዴን በሌላ ቦታዎች፣ ራሱ ህወሓት በቀጥታ በመግባት ግድያ፣ ዘር ማጥፋት፣ ማፈናቀል ከግብረአበሮቹ ጋር ሆኖ እየፈጸመው ይገኛል። ይህም የሚያበቃው ኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ የተባበረ ክንዱን ሲያሳርፍበት ብቻ ነው!! የኢትዮጵያ ህዝብ ተነሳ! ፍርሃትህን አስወግድ!!

1ኛ. የህወሓት ሽብርተኛው ስርዓት በምንም ተአምር በሰላማዊ መንገድ ከስልጣኑ አይወርድም። ይወርዳል የሚል ካለ በጭልምተኝነት ማእበል የሚንሳፈፍ ኢትዮጵያዊ ፍጡር ነው። ህዋሓት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የመጣ ሳይሆን ወራሪና ቅኝ ገዢ ነው። ይህን አምባገነን ፋሽስት ቅጥረኛ የሚወርደው በህዝባዊ አመጽ በተባበረ ክንድ ተደምስሶ መቃብር ውስጥ ሲገባ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ብቻ የወያኔ ስርዓት ያከትማል።

2ኛ. አንድ አንባገነን ፋሽስት ስርዓት እውነተኛ ምርጫ የሚባል ነገር አያውቅም። ፀረ-ዲሞክራሲ ስርዓት ያለበት ሃገር ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ቦታ የለውም። ይህም በ1997፣ በ2002 ያየነው ነው። በህወሓት የተዘረፈው ምርጫ አስተምሮናል። በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች የኢትዮጵያ ህዝብ አልመረጠውም። አሁንም የምርጫ ኮሚሽኑ ህወሓት፣ አስመራጭ ህወሓት፣ የምርጫ ሳጥን አቅራቢና ተቆጣጣሪ ህወሓት ነው። ተቃዋሚ ሃይሎች ከነተመራጮቻቸው በአካባቢው እንዳይደርሱ ተደርጎ እውነተኛ ምርጫ ሊከናወን አይችልም።

ጌዱ

ለሚመጣው 2007 ምርጫ ምን መተማመኛ አለን? በሚቀጥለው ምርጫ አንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) አሸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም። ይህ ቢሆንም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር የላቸውም። በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ እየተከተለው ያለውን መንገድ፣ የፋኖ ጉዞውን፣ አቁሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መተባበር አለበት። ካላደረገ የወያኔን እድሜ እያራዘመ ነው። በትግራይ አረና ሙሉ በሙሉ አሸናፊ ነው። የትግራይ ህዝብ ወያንኔ ህወሓትን አይመርጥም። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም ይመረጣሉ። ይህንን ድል ለመቀናጀት ግን ምን ዓይነት የምርጫ አካሄድና ዘዴ “Mechanism” ተዘጋጅቷል? ጥያቄው ይህ ሆኖ፣ ገለልተኛ ወይም ነፃ የምርጫ ኮሚሽን፣ ከውጭ የሚመጡ ገለልተኛ ታዛቢዎች፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ሃገር ኤምባሲዎች ምርጫውን በታዛቢነት እንዲከታተሉ መገኘት፤ የወያኔም ሆነ የወያኔ አጋር ደርጅቶች ወይም ተለጣፊ የጎሳ ፓርቲዎች፣ ድህንነቶች፣ ፖሊሶች፣ የወያኔ ደጋፊዎች በምርጫ ቦታዎች እንዳይታዩ ማሳገድ ወዘተ የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ለማቀነባበር ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጊዜው አሁን ነው። ወያኔ ህወሓት ደግሞ ግርግር ፈጥሮ እንደማይቀበል የታወቀ ቢሆንም በስፋት ደግሞ እንደገና ይጋለጣ፣ እድሜው ግን ይራዘማል።

ለማጠቃለል፣ ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሰጠው በአማራው ህዝብ ላይ ብአዴን “ብሄረ አማራ ዴሞራሲያዊ እንቅስቃሴ” ከመነሻውና ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ፀረ-አማራ ሕዝብ ሆኖ የተፈጠረ፤ ትወልዳቸው ከአማራ ውጭ የሆኑ ብአዴን እና ህወሓት ሃገር እንደተቆጣጠሩ በገንዘብ የተገዙ ባንዳዎች ለመሆናቸው ምስክርነቴን ለመስጠት ነው። የብአዴን አመራር ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮቹና ባንዳዎቹ እነ ደመቀ መኮንን፣ አለምነው መኮንን፣ ጌዱ አንዳርጋቸው፣ አያሌው ጎበዜ፣ ተፈራ ደርቤ፣ ብናልፈው አንዱአለም፣ አህመድ አብተው፣ አምባቸው መኮንን ወዘተ ከነ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ታደሰ ካሳ፣ ህላዌ ዮሴፍ፣ በህወሓት መሪነት በአማራው ላይ የከፋ ግፍና ሰቆቃ ፈጽመዋል። አማራው ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር ሆኖ፣ ለካስ እነዚህ ናቸው የኔ መሪዎች ብሎ በማሰብ፣ የገደሉትን፣ ዘሩን ያጠፉትን ሆዳሞች ሁሉ በጠንካራው ክንዱ ተባብሮ የማያዳግመውን ክንዱን እንዲዘረጋባቸው ነው። ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራው ላይ ብቻ ሳይወሰን ኦሮሞ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ድቡብ ህዝቦችም ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። ተገድለዋል፣ ዘራቸውን ለማጥፋት በየወህኒ ቤቱ ታስረው በውስር እየተገደሉ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ በግፍ እያለቀ ነው። ከመሬቱ ተሰዶ፣ ካደገበት ተፈናቅሎ ፋሽስታዊ ጭፍጨፋ እየደረሰበት ነው። ተባብሮ በመነሳት ህወሓት ወያኔን በህዝባዊ አመጽ ካልደመሰሰው ኢትዮጵያኝ ህዝቧ በህወሓት ሴራ ለክፉ አደጋ ይዳረጋሉ። በህዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል በከፋ መንገድ ከመቀጠሉ በፊት በህዝባዊ አመጽ ህወሓትን ማንበርከኪያ ጊዜው አሁን ነው

ከተራ ምንድን ነው?

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

ጥያቄ

በየዓመቱ የጥምቀት በዓል በድመቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ፋይዳውን ብታብራሩልን

ዮስቲና ከአዲስ አበባ

መልሱ

ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡

ketera 2 2“ከተራ” በመባል የሚታወቀው – ዋዜማው” ሠርግው /1981፣8/ እንደገለጹት “ከተራ” የሚለው ቃል “ከተረ ከበበ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ነው፡፡ ከተራ ፍቺውም ውኃ መከተር፣ ወይም መገደብ ማለት ነው፡፡” ብለው ሲፈቱ፣ ደስታ ተከለ ወልድ /1962፣ 694/ ደግሞ የጥምቀት ዋዜማ፣ ጥር 10 የጠራ ወራጅ ውኃ የሚከተርበት ታቦትና ሰው ወደ ዠማ ወንዝ የሚወርዱበት ጊዜ” ነው በማለት ይፈቱታል፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም /1948፣ 555/ ከተረ የሚለውን ቃል በቁሙ፣ “ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ፡፡” ማለት ነው ብለው ይፈቱታል፡፡ በየዓመቱ ጥር 10 ቀን የምእመናኑ አብዛኛው ሥራ ውኃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው፡፡ በየሰበካው ቦታ ተለይቶና ተከልሎ ታቦታቱ በዳስ ወይም በድንኳን የሚያድሩበት፣ የተለያዩ የውኃ አካላት ተጠርገው የሚከተሩበት ወይም ሰው ሠራሽ የግድብ ውኃ የሚበጅበት ስፍራ ‹‹ባሕረ ጥምቀት››፣ ‹‹የታቦት ማደርያ›› እየተባለ ይጠራል፡ ባሕር፡- የውኃ መሰብሰቢያ (ምእላደ ማይ፣ የውኃ መከማቻ (ምቋመ ማይ) ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ‹‹የውኃ አገር›› /መካነ ማይ፣ ዓለመ ማይ/ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና ክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል፡፡ የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ፡፡ ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ(1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት በዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡

ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።/ሐመር ጥር/የካቲት 1998 ዓ.ም/ ketera 3ታቦታት ከአንድ በላይ ሆነው ወደ ከተራው ስለሚሄዱ እግዚአብሔር አምላክ ለነብዩ ሙሴ “የታቦት መኖር ከእናንተ ጋር የመኖሬ ምልክት ነው” ዘፀ 25÷1 እንዳለው ታቦተ ሕጉን ተሸክመው ዮርዳኖስን እንደ ተሻገሩት ካህናተ ኦሪት፤ ካህናቱ የማይለወጠውን ታቦተ ሕጉን በራሳቸው ተሸክመው የብሉዩን ሥርዓት ከሐዲስ ኪዳን ጋር አንድ አድርገው የሐዲስ ኪዳን መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰቡ፤ ካህናተ ሐዲስም ወደ ከተራ (ዮርዳኖስ) ይጓዛሉ፡፡ ሊቃውንቱም እንዲሁ ለበዓሉ የሚስማማውን ቃለ እግዚአብሔር እያደረሱ እንደሚያድሩ ሊቀ ጠበብት ሐረገወይን አገዘ ያስረዳሉ። ሊቀ ጠበብት አያይዘውም የከተራ ዕለት ጥር 10 ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሄደበትን ለማዘከር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን የሚለውን ዋዜማ ይቆማሉ፡፡ የዋዜማው ቀለም ከቀኑ በአራት ሰዓት በመላው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይጀመራል ከዚያም የዋዜማው ሥርዐት ቅዱስ ተብሎ እስከ ሰላም ያለው ቀለም ይደርሳል፡፡

በዕለቱም ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ ታቦተ ሕጉን የሚያነሡት ሰሞነኛ ካህን ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ለዕለቱ የሚገባውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡ በከተራው ዕለት ድንኳን ተተክሎ፣ ዳሱ ተጥሎና ውኃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ታቦተ ሕጉ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት ሲደርስ የየቤተ መቅደሱ ታቦታት በወርቅና በብር መጎናጸፊያ እየተሸፈኑ በተለያየ ኅብር በተሸለሙ የክህነት አልባሳት በደመቁ ካህናትና የመጾር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ከብረው፣ ከቤተ መቅደስ ወደ አብሕርት /ምጥማቃት/ ለመሄድ ሲነሡ መላው አብያተ ክርስቲያናት የደወል ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ምእመናን ከልጅ እስከ ዐዋቂ በዐጸደ ቤተ ክርስቲንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ‘’ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ …’’ እንደሚባለው ያማረ ልብሳቸውን ለብሰው በዓሉን ያደምቃሉ፡፡ ሊቀ ጠበብት የበዓሉን ሂደት ሲገልጹ ታቦቱ ከመንበረ ክብሩ ሲነœ ‹‹ዮም ፍስሀ ኮነ›› ተብሎ ከተጸነጸለ በኋላ ታቦቱ ወጥቶ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት የሚለው ሰላም በሊቃውንቱ ይዘመራል፣ ይጸነጸላል፣ ይመላለሳል፡፡

የወርቅ ካባና ላንቃ የለበሱ ቀሳውስት፣ መነኮሳት ጥላ የያዙት ከታቦቱ ጎን መስቀልና ጽና የያዙት ከታቦቱ ፊት ይሄዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብሰ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ ፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ከነዚህም ሌላ ካባ፣ ላንቃ ጥንግ ድርብ የለበሱ መዘምራን የብር፣ የነሐስ መቋሚያና ጸናጽል ይዘው ‹‹ወረደ ወልድ›› የሚለውን አመላለስ እያሸበሸቡ ዲያቆናቱን ቀድመው ይሄዳሉ፡፡ የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችም በተለያዩ ቀለማት ባሸበረቁ አልባሳት ተውበው ትርዒት እያሳዩ “ወረደ ወልድ፣ እግዚኡ መርሐ፣ ሆረ ኢየሱስ” እና ሌሎችንም የአማርኛ መዝሙራትን እየዘመሩ፣ እናቶች “ነይ ነይ እምዬ ማርያም” እያሉ ሌሎችም ምስጋናዎችም እየቀረቡ ጉዞ በዝግታ ወደ ጥምቀተ ባሕር ይሆናል፡፡ የከተራ በዓል ማክበሪያ ቦታ እንደደረሱ ታቦታቱ በድንኳኑ አጠገብ ቆመው ‹‹ወረደ ወልድ›› የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተደርጎ የዕለቱ ትምህርተ ወንጌልና ዝማሬ ከቀረበ በኋላ ውዳሴ ማርያም፣ መልክዐ ኢየሱስ ተደግሞ ታቦታ ሕጉ ወደ ተዘጋጀላቸው ድንኳን ይገባሉ /ሠርግው፤ 1981፣ 9/፡፡

በሁለተኛ የአገልግሎት ክፍል ካህናቱ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ያድራሉ፡፡ በመንፈቀ ሌሊትም ሥርዐተ ቅዳሴው ተጀምሮ ከሌሊቱ በ9፡00 ሠርሆተ ሕዝብ ይሆናል፡፡ በነጋታው የሥርዐተ ጥምቀቱ መርሐ ግብር ይቀጥላል፡፡ የከተራ በዓል ምሳሌያት በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀቱ መዘጋጀት ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው፡፡የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብሮ መጓዝና ወደ ወንዝ መወረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ከሁለት ይከፈልና ወራጁም ይቆም/ይከተር/ ነበር፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ወደ ምድረ ርስት ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ሲሻገሩ፡- ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳኑን ታቦት በድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ በዙሪያው፣ ካህናቱ ደግሞ በውስጥ ኾነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል /ኢያሱ 3÷8-9/፡፡ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብረው የወንዙን ዳርቻ በረገጡት ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ውኃ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ወደ ላይ ቆሟል፡፡ ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ጽዮንን ያከበሩት ካህናት ከወንዙ መሀል ይቆሙ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ‹‹ወተጠምቃ እገሪሆሙ ለካህናት›› ይህም ‹‹የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስን ውኃ በመርገጣቸው እንደ ጥምቀት ሆናቸው›› በሐዲስ ኪዳነ ጌታችን ለመሠረተው ሥርዐተ ጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራችው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው፡፡ ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ፡፡›› /ኪ.ወ.ክ ፤517/፡፡

ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው፡፡ ከወንዝ ዳር ያለ መጠለያ መዋልና ማደር አይቻልም፡፡ በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ፡፡ በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በላስታ የላሊበላ መዋኛን፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እኒህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ፡፡እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡

“ኢትዮጵያ ምን ትመስላለች?” ብላ ትጠይቀኝ ነበር እናቴ

Hiwot Emishaw

  1. ጩኸቱ ሁሉ ‹‹በአውሎ ንፋስ ውስጥ የነበረ ፉጨት›› ሆነ ቀረ እንጂ፤ በዚያ ሰሞን ‹‹ኡ ኡ!›› ሲባልበት የነበረውን በድንበር ማካለል ሽፋን ለሱዳን መሬት አሳልፎ የመስጠት ጉዳይን መቼም ታስታውሱታላችሁ፡፡

    ወዳጄ አንተነህ ይግዛው ፤ ይህንኑ ጉዳይ በራሱ መንገድ አይቶት እንዲህ አድርጎ ፅፎታል፡፡
    ስለወደድኩት ለእናንተ አመጣሁት፡፡

    ‹‹የሶስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ፤
    “ኢትዮጵያ ምን ትመስላለች?” ብላ ትጠይቀኝ ነበር እናቴ፡፡
    “ጀበና!” ስል እመልስላት ነበር እኔ፡፡
    እንደማስታውሰው ይህ ጥያቄ፣ ያኔ የጂኦግራፊ ጥያቄ ነበር ፡፡ መልሱም የጂኦግራፊ፡፡
    .
    ዩኒቨርስቲ የሶስተኛ አመት ተማሪ እያለሁ፤
    “ኢትዮጵያ ምን ትመስላለች?” ብላ ብትጠይቀኝ እናቴ…
    “አንገት የሌላት ጀበና” እላት ነበር እኔ፡፡
    አሁንም ጥያቄው የጂኦግራፊ ሊሆን ይችላል፡፡ መልሱ ግን የፖለቲካ፡፡
    .
    ነገስ?…
    ነገም፤ “ኢትዮጵያ ምን ትመስላለች?” ትለኝ ይሆናል እናቴ ፡፡
    እኔስ ምን ብዬ እመልስላት ይሆን?
    “እጀታ የሌላት ጀበና”?…
    ነገም ጥያቄው የጂኦግራፊ ሊሆን ይችላል፡፡

    መልሱስ?

የህወሓት መፈክር፡ ‘የአማራ የበላይነት ይውደም!’

  • ———————————————————-

    ግርማይ ገብሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የአሁን የቪኦኤ (VOA) ዘጋቢና ደራሲ ነው። ዓላማዬ ስለ ግርማይ ገብሩ ለመፃፍ አይደለም፤ ግርማይ በፌስቡክ ገፁ ስላሰፈረው መረጃ ለመዋስ እንጂ። መረጃው ከዚህ በፊትም አውቀው ነበር። ግን ለማስረጃ ያህል ግርማይን ልጥቀስ: ምክንያቱም ግርማይ የህወሓት ታጋይ ነበርና።

    ግርማይ በ1969 ዓም የህወሓት (ተሓህት) ሦስቱ መፈክሮች ሲጠቅስ የመጀመርያውና ዋነኛው አድርጎ የፃፈው “አፄነት፣ መስፍንነትና የአማራ የበላይነት ይወድማሉ” ይላል።
    በትግርኛ “ካብ ጭርሖታት ህወሓት 1969 ዓም: ሃፀይነት፣ መስፍንነትን ናይ አምሓራ ዕብለላን ዓነውቲ እዮም!” ይላል። ግርማይ ገብሩ አልተሳሳተም። ከህወሓቶች ጋር የማልስማማበት ግን ነጥብ አለኝ።

    እርግጥ ነው። እኔም አፄነትና መስፍንነትን እንደ ስርዓት አልቀበልም። ምክንያቱም አፄነትና መስፍንነት (እንደ ስርዓት) ላሁኗ ኢትዮጵያ አይመጥኑም። የአፄነትና መስፍንነት ስርዓት በኢትዮጵያ ታሪክ እዚ ግባ የሚባል ለውጥ አላመጣም። ስለዚህ እኛ የሚያስፈልገን ዘመናዊ (ከዘመኑ ንቃተ ህሊናችን ጋር አብሮ የሚሄድ) የህዝብ አስተዳደር (ዴሞክራሲ) እንጂ ንጉስነት (የሰው ገዢነት) አይደለም። የምንፈልገው የሕግ የበላይነት እንጂ የንጉስ የበላይነት አይደለም።

    ግን አፄነትና መስፍንነት እንደ ስርዓት ባልቀበለውም የንጉሳውያን ቤተሰቦችና መሳፍንቶች መጥፋት አለባቸው ብዬ ግን አላምንም። እኔ ብሆን እነኚህ የንጉስ ቤተሰቦችና መሳፍንት ቁልፍ የመንግስት ስልጣን አልሰጣቸውም ነበር። በሀገራቸው በሰላም እንዲኖሩ ግን እፈቅድላቸው ነበር። ምክንያቱም እንደማንኛውም ሰው ዜጎች ናቸው፤ ለሀገራቸው በተቻላቸው መጠን አስትዋፅዖ አድርገዋል። ስለዚህ ንጉሳዊ ቤተሰብና መሳፍንት ስለሆኑ ብቻ መጥፋት አለባቸው ብዬ አልፈርድም። እንደ ጠላትም አላያቸውም፣ እንደ ዜጎች እንጂ።

    ህወሓት ግን በመፈክር ደረጃ በጠላትነት ፈረጃቸው። በተግባርም አጠፋቸው፣ ገደላቸው። በንጉሳዊ ቤተሰብና መስፍንነት ዝንባሌዎች ሰበብ ብዙ የተምቤን፣ ዓጋመ፣ እንደርታ፣ ዓድዋ፣ ሽረ፣ አክሱም ወዘተ መሳፍንቶች እንዲጠፉ ተደረገ። ‘ትግራይ ከመሳፍንቶች ነፃ ወጣች’ ተባለ። እውነታው ግን ‘ትግራይ ተገደለች’ መባል ነበረበት። መሳፍንቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ምን አመጣው (ህወሓቶች ከስልጣን ማውረድ እየተቻለ መግደል ለምን ያስፈልጋል)?

    ባጠቃላይ መሳፍንቶቹ ሲወድሙ ትግራይ ወደመች። አሁን በትግራይ የተቃውሞ መንፈሱ የተዳከመው በመስፍንነት ሰበብ ብዙ ብቁ ሰው ስለተፈጀብን ነው የሚል እምነት አለኝ። በህወሓት የተገደሉብንን ያህን በሌላ ስርዓት አልተገደሉብንም። ስለዚህ መሳፍንቶች ከስልጣን በማውረድ (መሳፍንቶችን ሳይሆን መስፍናዊ ስርዓቱ) ከህወሓቶች ጋር እስማማለሁ። መስፍናዊ ስርዓቱ ለማጥፋት መሳፍንቶቹ ማጥፋት ከሚል የህወሓት መፈክር ወይ መርህ ግን አልስማማም።

    ሌላውና መሰረታዊ የህወሓት ችግር “የአማራ የበላይነት ይውደም!” የሚል መፈክር ነው። እኔም ብሆን የማንም ሰው ወይ ብሄር ወይ ሌላ አካል የበላይነት አልቀበለም። የቴድሮስ ወይ ዮሃንስ ወይ ምኒሊክ ወይ ኃይለስላሴ ወይ መንግስቱ ወይ መለስ ወይ ኃይለማርያም ወይ አማራ ህዝብ ወይ ትግራይ ህዝብ ወይ ኦሮሞ ህዝብ ወይ ሌላ … የበላይነት አልቀበልም። እኔ የምቀበለው የበላይነት ‘የሕግ የበላይነት’ ብቻ ነው። የሌላ የማንም የበላይነት አልቀበልም።

    እንደ ፖለቲካ ድርጅት አንድን ህዝብ ዒላማ አድርጎ መነሳት ግን ስህተት ብቻ ሳይሆን በሽታ ነው። ህወሓት (ተሓህት) የአማራን ህዝብ ዒላማ አድርጎ ሲነሳ፣ ሌሎች የህወሓት ተቃዋሚዎች ደግሞ በህወሓት ምክንያት የትግራይን ህዝብ ዒላማ ሲያደርጉ ዉጤቱ ምን ይሆናል? አንድን ህዝብ ከሌላ ህዝብ ጋር የማጣላት ስትራተጂ የፖለቲካ ዕብደት ነው። ህዝብና ገዢው መደብ አለመለያየት (አንድ እንደሆኑ አድርጎ ማሰብ) የፖለቲካ እውቀት ማነስ ዉጤት ነው። ስርዓቱ መቃወምና መታገል እየተቻለ ህዝብን ዒላማ አድርጎ በህዝቦች ላይ መተማመን እንዳይኖር መትጋትና በህዝቦች መካከል ጥላቻ እንዲነግስ መስራት ጠባብነት ነው።

    አንድን ህዝብ የበላይነት ሊይዝ አይችልም። አንድን ቡድን ግን በአንድን ህዝብ ስም በመነገድ ሌሎችን ሊበድል ይችላል። የሰው የበላይነት (በህዝቦች ላይ) ሊተገብር ይችላል። ህዝብ እንደ ህዝብ ግን ሌላውን ህዝብ ሊበድል አይችልም። ህወሓት የትግራይን ህዝብ እንደሚወክል ይነግረናል። የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ እያለ ሌሎች ህዝቦች (የትግራይን ጨምሮ) ይበድላል። ሌሎች ህዝቦች (የትግራይ ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን) ደግሞ በህወሓት ስርዓት ሲበደሉ በትግራይ ህዝብ የተበደሉ አድርገው ያስባሉ። ግን ስህተት ነው። መታረም አለበት። የትግራይ ህዝብ ለራሱ በህወሓት አገዛዝ የሚበደል ነውና።

    “የአማራ የበላይነት” የሚባለው የህወሓት በሽታ እስካሁን ፈውስ አላገኘም። በመርህ ደረጃ ህዝብን ዒላማ አድርጎ ህዝብን ለመታገል መነሳት ስህተት ነው ብያለሁ። በፖለቲካ ህዝብን ዒላማ አይደረግም። ምክንያቱም የፖለቲካ ዓላማ ህዝብን ማገልገል እንጂ ህዝብን መጨቆን አይደለም። ስለዚህ ህዝብን የመበደል ዓላማ መያዝም መተግበርም የህሊና ወንጀል ነው። ህወሓቶች ይህን በሽታ (“የአማራ የበላይነት” መፈክር) አልተዋቸውም። አሁንም “ፀረ አማራ” እንቅስቃሴዎች አሉ። የህወሓት የአሁኑ ስትራተጂ “እኛ ከስልጣን የምንወርድ ከሆነ ከአማራ ጋር አብረን አንቀጥልም” የሚል ገንጣይ አስተሳሰብ እያራመዱ ይገኛሉ። “እኔ ከሌለሁ ሠርዶ አይብቀል …” ዓይነት ስትራተጂ መሆኑ ነው። በጣም የሚገርመው ነገር ፀረ ብአዴንም መነሳታቸው ነው። ለነሱ ከስልጣን ከሚወርዱ ኢትዮጵያ ብትበታተንና ትግራይን አስገንጥለው ትግራይን እየጨቆኑ ቢገዙ ይመርጣሉ።

    ግን ይህን “አማራ” የሚባል ህዝብ መቼ ይሆን የበላይነት ይዞ ሌሎች ህዝቦችን የበደለው? አንድን ህዝብ እንዴት ሌላውን ህዝብ ይበድላል? ህዝብ ህዝብን ሊበድል አይችልም። ምክንያቱም አንድን ህዝብ ሌላውን ህዝብ መበደል ከጀመረ (ከቻለ) ህዝብ መሆኑ ቀርቶ ገዢ መደብ (elite) ሁነዋል ማለት ነው። ገዢ መደብ ከሆነ ደግሞ ህዝብ አይደለም። ገዢ መደብ ስርዓት ነው። ህዝብና ስርዓት ደግሞ ይለያያሉ።

    ምናልባት የህዝብ የበላይነት አለ የምንለው ህዝብን የሚያስተዳደር (የሚገዛ) ስርዓት ከህዝቡ የወጣ ሲሆን ይሆን? ይህም አሳማኝ አይደለም። ምክንያቱም ገዢ ሁሌ ከህዝቡ ነው የሚወጣው (የቅኝ ግዛት ካልሆነ በስተቀየር)፤ ገዢ ከህዝቡ እንጂ ከማርስ አይመጣም። የኢትዮጵያ መሪ ከኢትዮጵያ ህዝብ ይወጣል። በኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሉ። ስርዓቱ ከሁሉም ህዝቦች ሰዎች ይኖሩታል። መሪ ግን አንድ ነው የሚሆነው። ያ አንድ ሰው (መሪው) ከአንድ ብሄር ሊሆን ይችላል። ያ አንድ ሰው ስልጣኑ ተጠቅሞ ሌሎች ህዝቦችን ሊበደል (ወይ ሊጠቅም) ይችላል። ሰውየው የፈጠረው ስርዓት ለህዝቡ ቢጎዳም ቢጠምም ከስርዓቱ ይገናኛል እንጂ መሪው ከመጣበት ብሄር ጋር አይገናኝም። ስለዚህ ገዢዎች የሚወክሉት የፈጠሩትን ስርዓት እንጂ የመጡበትን ብሄር አይደለም።

    የደርግ ስርዓት ሲበድለን፣ “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የኃይለስላሴ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” ይሉናል። የምኒሊክ ስርዓት ሲበድለን “አማራ በድሎናል” አሉን። የህወሓት ስርዓት ሲበድለንስ ማን በደለን ሊሉን ነው? የትግራይ ህዝብ? አይሆንም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ይበድላል? አንድን ህዝብ ራሱን ይበድላል? በደል ሁሉ ወደ አማራ ህዝብ ለምን? ስርዓትና ህዝብ ማገናኘት የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል።

    ግን እስቲ ይሁን፤ መሪዎች የመጡበትን ብሄር ይወክላሉ እንበል (ስህተት ቢሆንም)። እነሱ (መሪዎቹ) ሲበድሉ የመጡበት ብሄር በበዳይነት ተፈርጆ እንደ ጠላት ይቆጠር እንበል። የአማራ ህዝብ መቼ ይሆን በመሪዎቹ አድርጎ ሌሎች ህዝቦችን የገዛ (የበደለ)? ያለፉ ጨቋኝ ስርዓቶች አማራ ነበሩ ያለው ማነው? አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። እስቲ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መሪዎች እንመልከት።

    ብዙ ግዜ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከአፄ ቴድሮስ ነው (ወይም ከዚሁ እንጀምር! ምክንያቱም ከአፄ ቴድሮስ በፊት ኢትዮጵያ በመሳፍንቶች ነበር የምትተዳደረው። በዘመነ መሳፍንት መሳፍንቶች የራሳቸውን ህዝብ (ብሄር) ይገዙና ይበድሉ ነበር)። “አማራ” ተብሎ ከተሰየመው አከባቢ የሚወለድ ገዢ ቴድሮስ ነው። አፄ ቴድሮስ ኢትዮጵያ አንድ ለማድረግ በዛን ግዜ የነበሩ መሳፍንቶች ተዋጉ። አፄ ቴድሮስ ዉግያው የጀመሩት በአማራ መሳፍንቶች (የጎጃም፣ ወሎና ጎንደር) ነበር። ቴድሮስ “ከአማራ ስለመጣሁ፣ አማራ ስለምወክል፣ የአማራ መሳፍንቶች ማጥፋት የለብኝም” አላሉም። (ህወሓት ለትግራይ መሳፍንቶች እንዳደረገው ሁሉ)። ስለዚህ አፄ ቴድሮስ አማራን ወክለው ሌላው ኢትዮጵያዊ አልበደሉም (ከበደሉም ለሁሉም ነው)። ስለዚህ “በአማራ ህዝብ ተገዛን” የሚለው ክስ “በአፄ ቴድሮስ ተገዛን” የሚል እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

    የአማራ ተወላጅ የሆነ የኢትዮጵያ ገዢ ቴድሮስ ብቻ ነው ብዬ አስባለሁ (ጉዳዩ ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተወው እንዳልሳሳት፤ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ)። ዮሃንስ አማራ አልነበረም፣ ምኒሊክ አማራ አልነበረም፣ ኃይለስላሴ አማራ አልነበረም፣ መንግስቱ አማራ አልነበረም፣ መለስ አማራ አልነበረም፣ ኃይለማርያም አማራ አይደለም። ማነው አማራ?

    ምናልባት “የአማራ ገዢዎች” የምንለው ግለሰቦቹ (ንጉሶቹና መሪዎቹ) ሳይሆን ስርዓቱ ነው ካልን ያው ስርዓቱማ ከሁሉም ህዝቦች ተወካዮች አሉበት። አማራ ለብቻው ገዥ ነበር ማለት አንችልም። ምናልባት ገዢዎቹ አማርኛ ስለሚናገሩ ነው ካልን ደግሞ አማርኛ የተናገረ ሁሉ አማራ አይደለም። አቶ መለስም አማርኛ ይናገር ነበር። አፄ ዮሃንስም አማርኛ ይናገሩ ነበር (አማርኛ የኢትዮጵያ ኦፊሽየላዊ የስራ ቋንቋ እንዲሆን የወሰኑት አፄ ዮሃንስ ናቸው የሚል መረጃ አለኝ፤ ‘መረጃ’ እንጂ ‘ማስረጃ’ አላልኩም)።

    የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያ ገዢዎች ሲሰቃይ የነበረ ነው። ባልበላበት በልተሃል፣ ባልገዛበት ገዝተሃል ሲባል ይገርማል፤ ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ። የትግራይ ህዝብ ሳይበላ በልተሃል፣ ሳይገዛ ገዝተሃል ይባላል፤ ህወሓት በበላው፣ ህወሓት በገዛው። ህወሓት ትግርኛ ተናጋሪ ስለሆነ ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም (በፖለቲካ መልኩ)። ያለፉ ገዢዎች አማርኛ ስለሚናገሩ ከአማራ ህዝብ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም። ህዝብ ሌላ ገዢ ሌላ።

    ባጭሩ ፀረ ህዝብ አቋም መያዝ ተገቢ አይደለም (ለማንኛውም ህዝብ)። ሰው የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት መያዝ ይችላል። “የቀድሞ ስርዓት አባላት …” ምናምን እያልን አንፈርጅ። የህወሓት አባላት ለሌሎች ሰዎች የቀድሞ ስርዓት አባላት፣ ናፋቂዎች ወዘተ እያላቹ ስትፈርጁ እናንተም ራሳችሁ ከህወሓት ስርዓት በኋላ “የቀድሞ ስርዓት አባላት ..” ምናምን እየተባላቹ ስማቹ ይጠፋል፣ የፈለጋችሁን የፖለቲካ ፓርቲ አባል የመሆን መብታቹ ይገደባል። አሁን በሌሎች ላይ የምትፈፅሙትን ስም የማጥፋት ተግባር በናንተ (በራሳቹ) ይፈፀማል።

    ስለዚህ እናስተውል። ከጥላቻ ፍቅር ይሻለናል። ጥላቻ ይውደም። አሜን!

    It is so!!!

ዳር ድንበራቸው ለሱዳን ሊሰጥ መዘጋጀቱን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

(ዘ-ሐበሻ) 1200 ኪሎ ሜትር የሚገመትን የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ጠዋት በዋሽንግተን ዲሲ የሱዳን ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ።

DC-ethiopian-sudan

“የወያኔ መንግስት ሃገርን በመሸጥና በመክዳት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ በመስጠትና ነዋሪዎችንም በማባረር እየፈጸመ ያለው ወንጀል ዝም ሊባል” አይገባም የሚሉት እነዚሁ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሱዳን መንግስት ከዚህ ወንጀል ጋር ተባባሪ እንዳይሆን በተቃውሞ ሰልፋቸው ጠይቀዋል። በሰልፉ ላይ ከተሰሙ መፈክሮች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል።

EDUCATING DEMEKE MEKONEN AND COMPANY

ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ !!!:::
ለኢትዮጵያውያን በሙላ ! የሟች ጠ/ሚኒስትሩን ሊጋሲ ለማስፈፀም አሻንጉሊቱ ጠ/ሚ ሀይለማርያም እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቴዎድሮስ : ሀገር በማሻሻጥ ስራ ላይ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር በሱዳን ካርቱም ስምምነት ላይ ደርሰዋል ::
ማፊያው የህውሐት መንግስት በካርታው ላይ የሚታየውን መሬት ለሱዳን መንግስት አሳልፎ በመስጠት እጅግ በርካታ ሕዝብ ለማፈናቀልና የሐገሪትዋን ለም መሬት ለመሸጥ ጫፍ ላይ ደርሰዋልና ኢትዮጵያውያን በአንድነት ተነስተን በቃቹ ልንላቸው ይገባል ::
ከህዝብ ተደብቆ በተደረሰው ስምምነት መሰረት መሬቱ ሲካለል የኢትዮጵያን ካርታ እንደሚቀየርና ሀገሪትዋ ታሪክዋ እና ክብርዋ ተደፍሮ ከማየት ወያኔን በቃ ማለት ግዴታ ነውና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምሁራንና መላ ኢትዮጵያውያን ጥሪውን ተቀብለን ሀገሪችንን እናድን
ሼር በማድረግ መረጃውን እናድርስ::

አገር አትሸጥም አትለወጥም” በማለት
የወያኔን ለሱዳን መሬት መስጠት ከተቃወሙት
የአትላንታ ኢትዮጵያውያን መካከል
በልማት ስም ለመጣው ልዑክ
ከታሪክ ትምሕርት ሲሰጡ።

Demeke Kebede: አገርና ፊደል ( ከደሃ ህዝብ ችግር ይልቅ ቃል በመሰንጠቅ ለሚዳክሩ )

አገርና ፊደል
//ደመቀ ከበደ – አዲስ አበባ//( ከደሃ ህዝብ ችግር ይልቅ ቃል በመሰንጠቅ ለሚዳክሩ )ዝናብ ባጣ መሬት – ስንጥቅጥቅ ባለ – ውሃ በተጠማ
ዘር አበቅል ብሎ – ሁሌ እጁ ለሚላጥ – ሰርክ ለሚደማ
አንደዜ ለእግዜሩ
አንደዜ ለአውጋሩ
ጎንበስ ቀና ለሚል – አንገት ለሚደፋ
በሽህ ዘመን ሞፈር – አፈር ለሚገፋ
‹‹ሀ›› ማለት ምንድን ነው?
‹‹ለ›› ማለትስ ምንድን?
በፊደል ላይጠግብ – ጎኑ ላይደነድን፤ፊደልን በለየ – ፊደል በቆጠረ
ከፊደል ጋር ውሎ – ፊደል ጋር ባደረ
በፊደል ‹‹ልህቀት›› ላይ – ‹‹ዕውቀት›› ባደደረ
ምስኪን የአገር ድሃ
ሲሻ ‹‹የተማረ›› – ‹‹የተመራመረ››
ከችግሩ ጋራ – አለ እየዳከረ፤

ከ‹‹ሀ›› እና ‹‹ሁ›› በላይ
ለእኛነት ሾተላይ
‹‹ችጋር›› ሆኖ ሳለ – የህልማችን ሰማይ – የህዝባችን ስቃይ
መንጋ ‹‹እኔ ልብላ›› ባይ
መንጋ ‹‹እኔ አውቃለሁ›› ባይ
የፊደል አድርባይ
ፊደል አቀባብሎ – ፊደል ይተኩሳል – ይኸው በአደባባይ፤

በቁራጭ አጎዛ – ጥቀርሻ ጎጆው ውስጥ
ታጥፎ ለሚተኛ – ገበሬው አባቴ
ካለቀ ጫካ ውስጥ – ቅጠል በጀርባ አዝላ
ዳቦ ለምትጋግር – መከረኛ እናቴ፤
ነገን የኔ ብለው – በሰለለች ተስፋ – ለሚውተረተሩ
ከ‹‹አዋቂ ነን›› ባዮች
ከ‹‹ምሁር ነን›› ባዮች
ከነ ‹‹ፊደል ጭንቁ›› – መፍትሄ አለ ብለው – ለሚያጨነቁሩ
ለደሃ አገር ህዝቦች – ‹‹ምን ልሁን›› ለሚሉ……
ሶፋ ተደግፎ – ‹‹ላፕቶፕ›› ተንተርሶ
መለኪያ ጨብጦ – ወፍራም ፒፓ ጎርሶ
ቃል እየመተሩ – እየለዩ ጎራ
‹‹የለም ‹ሀ› ነው›› ማለት
‹‹አይ ‹ፐ› ነውንጅ›› – ማለት በየተራ
ይህ የ‹‹ቃል›› ስንጠቃ – የ‹‹ፊደል›› ድርደራ
ከቶ ምን ማለት ነው?
ካልሆነ በስተቀር – እውነቱን ስወራ!!

እንጂማ ….
ለኔ ብጤ ደሃ
‹‹ሀ›› ቢሉት ምኑ ነው? – ‹‹ለ›› ማለትስ ምንድን?
ፊደል እህል ሆኖ – ጎኑ ላይደነድን፤

ደግሜ ደግሜ – አሁንም እላለሁ
ለአንዲት ደሃ አገር ህዝብ
‹‹ሀ›› ማለት ምንድን ነው? – ስል እጠይቃለሁ፤
የምሬን እኮ ነው
‹‹ሀ›› ማለት ምንድን ነው? – ‹‹ለ›› ማለትስ ምንድን?
ፊደል እህል ሆኖ
ከችጋር ላይፈውስ – ከጠኔ ላያድን!!

እዚህ ገና ሳትናገር ሃሳብህን በረዶ የሚያደርጉ አፍጣጭና ገልማጮች…

ከሰው ፊት የተፈጥሮ ፊት
(አሌክስ አብርሃም )ወዳጃችን Yona Bir እንዲህ ሲል መልእክቱን ልኮብናል
<<እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አልፈልግም፤ በዐልም አልወድም>> የሚል ሃበሻ እንኳን ቢኖር ዛሬ አገሩን መናፈቁ አይቀርም።ለምን መሰላቹ?

አየሩ!!!

ወይኔ አየሩ፤ ወይኔ ብርዱ፤ ወይኔ ቅዝቃዜው (በእናታቹ ሌላ ቃል ፈልጉልኝ)

ዛሬ አንዳንድ ቦታዎች ቅዝቃዜው ከዜሮ በታች እስከ 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ (-40 °C ወይም -40.0 °F ሁለቱም እኩል ናቸው) ደርሷል። -40 °C ሲባል ቁጥር ብቻ ስለሆነ ስሜቱን አትረዱት ይሆናል። ቆይ በሌላ ዘዴ ላስረዳቹ

ከብርዱ የተነሳ ኡ… ኡ…. ኡ… ብላችሁ መጮህ ያምራቹና ገና ኡ.. ለማለት አፋቹን ስትከፍቱ አፋችሁ ውስጥ ያለው ምራቅ ወደ በረዶነት ስለሚቀየር አፋችሁ እንደተከፈተ ይቀራል። በዚህ ምክኒያት ዛሬ ዎክ ማድረግ ተከልክሏል። ››
.
.
እንግዲህ በዚህ የገና ወቅት … አገር ውስጥ የምትኖሩ (በነሮዛ ቋንቋ ሎካሎች) ያንን ውብ አየር እየማጋችሁ ደስ ይበላችሁ!!

አሌክስ አብርሃም የቤት ክራይ በየቀኑ ማሻቀቡ አብሽቆህ ይሆናል። ግን በምድር ላይ (ከገነት ቀጥሎ) ምርጥ አየር ባላት አዱ ገነት ላይ ገናን በማክበርህ ደስ ይበልህ። ››

Yona Bir ያልከው ሁሉ ገብቶናል !! ግን አልተግባባንም ! ምክንያት ብትለኝ ….

እዚህም ኑሮ ቀዝቅዞ ከዜሮ በታች (-40 °C ወይም -40.0 °F ሁለቱም እኩል ናቸው) ደርሷል። እንዳይመስልህ ወዳጀ እናተስ ጋር ልትናገር አፍህን ስትከፍት ምራቅህ በረዶ ይሆናል እዚህ ገና ሳትናገር ሃሳብህን በረዶ የሚያደርጉ አፍጣጭና ገልማጮች ብዙ ናቸው ! ወዳጀ በእኔ ይሁንብህ ከሰው ፊት የተፈጥሮ ፊት ቢገለምጥህ ይሻላል ! አርፈህ ዶላሬህን ሰራ ሰራ አድርግና ደህና ማሞቂያ ሸምት !

የሰው ልጅ ንፁህ አየር ወደውስጥ በመሳብ ብቻ አይኖርም የተቃጠለውን አየርም ወደውጭ ሲተነፍስ እንጅ ! እና መተንፈስህ በሚደብራቸው ሰወች መሃል ከሆንክ እንኳን ከገነት ቀጥሎ ያለ አገር ገነትም ራሱ ከሲኦል እኩል ነው ፡፡ ዮኒ የቤት ኪራይ መጨመር አያምም ….የቤት ኪራይ ጨምር መባል ነው የሚያመመው …..አለመተንፈስ አያምም አትተንፍስ መባል ግን ያማል …..ስለነፃነት የሚያወሩህ ሰወች ምርኮኞች ናቸው ምርኮኛ ጋር ደግሞ ማራኪ አይጋጭም ! በሃሳብ የተለየ ግን ዎዮለት !

ያው እንዳየኸው በተያያዘ ዜናህ እንደታዘብከው …..እች አገር ሳትቀመጥ እግሯን እየዘረጋች መፈንገል ሆኗል እጣ ፋንታዋ ሃሳብ እየተገመደለ እና እየታፈነ ለአንዲት ፊደል ፊርማ ሰብስቡ ይሉናል ! ከደቡብ እስከሰሜን የተዘረጋ ችግር ሳይቆረቁራቸው ከጉሮሮ እስከምላስ ያለች ድምፅ የእግር እሳት የሆነችባቸው ወዳጆቻችን ዘመቻ ላይ ናቸው !

እና ልድገምልህ ከሰው ፊት የተፈጥሮ ፊት ቢገለምጥህ ይሻላል ! በረዶ ለዘላለም ይኑር ! በረዶ ላይ ገናን በማክበርህ ደስ ይበልህ ! እኛም ቃላችን ሳይሆን ምራቃችን በረዶ የሚሆንበት ዘመን ይናፍቀናል ንግግር የሚከለክል ሃሳብን በነፃነት እንዳትገልፅ የሚያግድ በረዶ በፀሃይ ይቀልጣልና !!

አቶ አያሌው ጎበዜ ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነታቸው ለምን ተነሱ?

Zehabesha

ከአቡዛብር ተገኝ

ፋክት መፅሄት (በታህሳስ 2006፣ ቁጥር 26 እትሙ) የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ አያሌው ጎበዜ በምን ምክንያት ከስልጣን እንደ ተነሱ ያሰፈራቸውን መላምቶች አንብቤያለሁ፡፡ ብዙዎቹ በግምትና በይሆናል ላይ የተመሰረቱ ከመሆናቸውም በላይ ለግለሰቡ ከፕሬዝዳንትነት መነሳት በዋና ምክንያትነት ሊመደቡ የሚችሉ አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ለመፃፍ መነሳቴ፡፡

አቶ አያሌው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነት የተነሱበት ዋና ምክንያት ምንድነው?

ከዜናው ሀሳብ በመነሳት በአንድምታ የምንረዳው እውነታ ስላለ፣ በኢቲቪ ከቀረበው የአቶ አያሌው ዱላ የማቀበል ዜና ልጀምር፡- በኢቲቪ ዜና መሰረት አቶ አያሌው ጎበዜ ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸው የተነሱት በፍቃዳቸው ነው፤ “በቃኝ፣ ዱላውን ላቀብል” ብለው፡፡ እንኳንስ ከክልል ፕሬዝዳንትነት ስልጣን ላይ ይቅርና ከተራው የሹመት ስልጣን (ለምሳሌ ምክትል ቢሮ ሀላፊ፣ ከዚያም ዝቅ ሲል “ፕሮሰስ ኦውነር”) ላይ በራሱ ፈቃድ “ልውረድ” ያለን የፖለቲካ ተሿሚ፣ ኢህአዴግ “‘በቃኝ’ ካልክማ እሰዬ” ብሎ ቶሎ የመልቀቅ ልምድ የለውም፤ ኢህአዴግ እንደ ገብስ ቆሎ ሳያሽ የማውረድ ባህል የለውም፡፡ ኢህአዴግ፣ አፍ አውጥቶ “ሹሙኝ-ሹሙኝ” ያለን ወይም በጣም “በሚያስበላ” ሁኔታ እንዲሾም የቋመጠን ሰው የስልጣን መንበሩ የማያቀምሰውን ያህል፣ “ስልጣን በቃኝ” ያለን አባል፣ ተንደርድሮ አያወርድም – ለዚያውም የክልል ፕሬዝዳንት ያህልን ሰው፣ ለዚያውም አስቸኳይ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ጠርቶ፡፡

አያሌው ጎበዜ
ስለሆነም ኢቲቪ አቶ አያሌው ጎበዜ በራሳቸው ፈቃድ “የመተካካት መርሁ በ’ኔም ላይ ይተግበርልኝ” ብለው ከፕሬዝዳንትነታቸው ስለመልቀቃቸው የነገረን ዜና ታእማኒነት የሌለው፣ የተለመደ የኢህአዴግ ድራማ ለመሆኑ አንድ ማሳያ ነው፡፡ ሌላው ማሳያ ግለሰቡ አስቸኳይ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ ከስልጣን በለለቁበት እለት፣ ሙሉ አምባሳደር ሆነው የመሾማቸው “ትንግርት” ነው፡፡ የአማራው ክልል የምክር ቤት አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ የተጠራው፣ በአቶ አያሌው የቀረበውን “የመተካካት መርሁ በ’ኔም ላይ ይተግበርልኝ” ጥያቄ አዳምጦ ካመነበት ከፕሬዝዳንትነታቸው ሊያነሳቸው፣ ካላመነበት ደግሞ ጥያቄውን ውድቅ ሊያደርግ ነው፡፡ ወይም ደግሞ ጥያቄያቸውን በመሰረታዊ ሀሳብነት ተቀብሎ ከፕሬዝዳንትነታቸው የሚያነሳበትን ወቅት ግን የተወሰነ ጊዜ ሊያራዝም ይችላል፡፡ 

ከአምባሳደርነት ሹመታቸው የምንረዳው ግን ሁሉም ነገር ቀድሞ ያለቀ መሆኑን ነው፡፡ ግለሰቡ መነሳታቸውም፣ መሾማቸውም ያለቀ ነገር ነበር፡፡ መቼም ምክር ቤት ተብዬው የመወሰን ሙሉ ቀርቶ እንጥፍጣፊ ስልጣን እንኳን ቢኖረው፣ በአምባሳደርነት የተሾመን ግለሰብ ከፕሬዝዳንትነት ስለማውረድ፣ አለማውረድ ጉዳይ እንዲወያይ ባልተደረገ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር አቶ አያሌ ጎበዜ ከፕሬዝዳንትነታቸው እንዲነሱ ለምክር ቤቱ ሀሳባቸውን ካቀረቡበት እለት በፊት አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ስለሆነም ቢያንስ በዚያች እለት ግለሰቡ ሁለት ጥምር ስልጣን በትከሻቸው ላይ ነበር – የአማራ ክልል ፕሬዝዳንትም፣ በቱርክ የኢትዮጵያ ሙሉ አምባሳደርም ነበሩ፡፡ ስለዚህም የአማራው ክልል ም/ቤት አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ ተጠርቶ ሲወያይ የነበረው፣ ቀድሞውኑ ከፕሬዝዳንትነቱ በተነሳና አምባሳደር ሆኖ በተሸመ ግለሰብ (አቶ አያሌው) ጉዳይ ላይ ነበር፡፡ (የኢህአዴግ ድራማ እንዴት ደስ ይላል¡)
ድራማው ግን በዚህ አያበቃም፡፡ አቶ አያሌው ለምን ከፕሬዝዳንትነታቸው እንዲነሱ ተደረገ? ፋክት መፅሄት ከተወሰኑ መላምቶች አንፃር በማየት ስለግለሰቡ አነሳስ ምክንያት ለማቅረብ ሞክራለች፡፡ ሆኖም አንዳንዶቹ መላምቶች የተሳሳቱና እጅግ የተጋነኑ ስለሆነ፣ እኔ ለክልሉ ባለስልጣናት ካለኝ ቅርበት አንፃር የተወሰኑት ላይ ማስተካካያ ለመስጠትና ለግለሰቡ ከስልጣን መነሳት ዋናውን ምክንያት ለመጠቆም እፈልጋለሁ፡፡

አቶ አያሌው ከስልጣን የተነሱት ለሱዳን ከተሰጠ የወሰን አካባቢ ቦታ ጋር የተያያዘ መሆኑን አንዳንድ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በፊትም አቶ አያሌው “አልፈርምም አለ” ተብሎ መናፈሱ ይታወቃል፡፡ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡ አቶ አያሌ በዙሪያቸው ያሰባሰቧቸው የወንዝ ልጆች በስፋት የለቀቁት ተራ ፕሮፓጋናዳ ነው፡፡ አንደኛ መለስን እንኳንስ “የቁርጥ ቀን ልጅ” በሚፈለግበት እንዲህ ባለው ሁኔታ ቀርቶ፣ ቀላል በሚባሉት ጉዳዮችም “ይህን እኔ አልሰራም” የሚል ባለስልጣን ኢትዮጵያ አልነበራትም (ያማ ቢሆን ኖሮ፣ የተሸከምነው መከራ በግማሽ እንኳን በቀነሰልን ነበር)፡፡ እንዲያውም አቶ መለስ በአንድ ወቅት አቶ አያሌውን “አንተ የማትጠቅም፣ የማትጎዳም ነህ” ብለው በመተቸታቸው በድርጅቱ ትልልቆቹ አባላት ውስጥ ዜናው በስፋት ተናፍሶ ነበር፡፡ ባጭሩ አቶ አያሌው “እምቢ” የማለት ወኔው የላቸውም፡፡ (በሱዳኑ ፊርማ ላይ አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሳተፉ የተደረገው፣ ሙስሊም ስለሆኑ/ኢስላማዊ ዳራ ስላላቸው የሱዳኖችን ስነልቦና “ለመግዛት” ኢህአዴግ የቀየሰው ስልት ከመሆን አይዘልም፣ ወደ አንዳንድ አረብ አገራት ዲፕሎማቶችን ሲመድብ ተመሳሳይ መንገድ ስለሚከተል፡፡)

እና አቶ አያሌው ለምን ከፕሬዝዳንትነታቸው እንዲነሱ ተደረገ? የአቶ አያሌው ከፕሬዝዳንትነት መነሳት ለብዙዎች ድንገታዊ ሊመስል ይችላል፤ አንደኛ አቶ አያሌው “የመተካካት መርሁ በ’ኔም ላይ ይተግበርልኝ” ብለው እንዲጠይቁና ይቺው ቃላቸውም ሳትጨመር-ሳትቀነስ በኢቲቪ እንድትተላለፍ ተደርጓል፡፡ ሁለተኛ “ከስልጣን አውርዱኝ” ጥያቆያቸውን ያየው ም/ቤት ጉዳዩን የተወያየበት በ“አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ” ነው፡፡ ሆኖም ግን ሀቁ ሌላነው፡፡ (እነዚህ ግርግሮች ሌላው የድራማው አካል ናቸው)፡፡

አቶ አያሌውን ከፕሬዝዳንትነት የስልጣን ኮርቻ የማንሳቱ እቅድ የተዘረጋው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር (አቶ መለስ) በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ አቶ መለስ በመሩትና ባህር ዳር ላይ በተካሄደ የኢህአዴግ ስብሰባ ላይ አቶ አያሌ ተገምግመዋል፡፡ በዋናነት የቀረበባቸውና የተቀበሉት ክስም በክልሉ ባሉ የተለያዩ የስልጣን/የሹመት እርከኖች ላይ የራሳቸውን አካባቢ ሰዎች እጅግ በተደራጀ መንገድ ማሰባሰባቸው ነው፡፡ አንዳንዶች ሂደቱን “ጎጃማይዜሽን” ይሉታል፤ ሌሎች ደግሞ “ማርቆሳይዜሽን” በማለት ይጠሩታል፡፡

አቶ አያሌው ሹመት የሚሰጡበት ቀመር በጣም ግልፅ ነው፡፡ እሳቸው ከመጡበት ከደብረ ማርቆስና አካባቢው የተማረ ከተገኘ ያለ ምንም ጥርጥር ይሾማል፡፡ ማርቆሴ እያለ ሌላ ሰው በምንም ሁኔታ አይሾምም፡፡ ማርቆሴ ከጠፋ፣ የአቶ አያሌው ሁለተኛው የሹመት ቀመር ስራ ላይ ይውላል፤ ጎጃሜ የሆነ ሰው ተፈልጎ ይሾማል፡፡ ማርቆሴ ሁሉ ጎጃሜ ቢሆንም፣ ጎጃሜ ሁሉ ግን ማርቆሴ አይደለም፡፡ ሆኖም ማርቆሴ ያልሆነ ጎጃሜን መሾም፣ ጎንደሬን፣ ወሎዬን ወይም የሰሜን ሸዋ ሰው ከመሾም እጅግ የተሻለ ነው፤ ምክንያቱም ጎንደሬም፣ የሸዋ ሰውም ሆነ ወሎዬ መቼም ቢሆን ጎጃሜ አይደለምና፡፡ ይህ የአቶ አያሌው የሹመት ቀመር ከስልጣን በሚወርዲት ላይም ስራ ላይ ይውላል፤ ባብዛኛው ከስልጣን የሚወርድ ተሿሚ ማርቆሴ ወይም ጎጃሜ አይደለም፤ ባጋጣሚ ነገሩ ከፍቶ ከስልጣን ከተነሳም ወይ የተሻለ ቦታ ይሰጠዋል፤ ካልሆነም በያዘው ደረጃና ደመወዝ የአቶ አያሌው አማካሪ ሆኖ ይሾማል (ፉገራ በሚወዱ ካድሬዎች አነጋገር Recycle Bin ውስጥ ይገባል፡፡ ይህ ማለት እንደ ገና የሚሾምበት ጊዜ አለ ማለት ነው፤ አቶ አያሌው ማዘናጋት የሚገባቸውን ካዘናጉ በኋላ፡፡ የቀመሩን ዘረኝነት (racist) ልብ ይሏል፡፡)

ይህም በመሆኑ አሁን በአማራ ክልል ርእሰ ከተማ -በባህር ዳር- ብዙዎቹን የመንግስት ተቋማት የሚመሩት ባለስልጣኖችና ምክትሎቻቸው፣ ዝቅ ሲልም የምክትሎቹ ምክትሎች (ፕሮሰስ ኦውነር፣ መምሪያ ሀላፊ፣ ወዘተ) በዚህ የአቶ አያሌው የሹመት አሰጣጥ ቀመር ወደ ስልጣን የመጡ ናቸው፡፡ ይህ የአቶ አያሌ የሹመት ቀመር በቀጥታ በማይመሩት በባህር ዩኒቨርስቲ ጭምር ስራ ላይ እየዋለ እንደ ሆነ ይነገራል፤ ዩኒቨርስቲው በፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር የሚመራና ያሉት መምህራንም ከአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገኙ ሆነው እያለ፤ የፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ዲን ስልጣን (ወረድ ሲልም ከፕሮግራም ሀላፊ) በአብዛኛው በመጀመሪያ ደረጃ በማርቆሴዎች፣ ከዚያም በጎጃሜዎች “ቡድን” እንዲያዝ ተደርጓል፡፡ የአቶ አያሌው የጎጠኝነትና የዘረኝነት እጅ ይሄን ያህል ረጅም ነው፡፡

ይህ ድርጊታቸው ማለትም ክልሉን የጎጠኞች አምባ ማድረጋቸው አቶ አያሌውን ክፉኛ አስገምግሟቸዋል – በአቶ መለስና በሌሎቹም የኢህአዴግ ቁንጮ አባላት፡፡ ሆኖም አቶ መለስ በሀይል የወቀሷቸውን፣ የሰደቧቸውን፣ ያንቋሸሿቸውን ያህል አቶ አያሌውን ሮጥ ብለው ከስልጥን ማንሳት አልሆነላቸውም፡፡ በአቶ አያሌው ድርጊት “የበገኑትን” ያህል የይስሙላውን የአማራ ክልል ም/ቤት አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባ አስጠርተው ግለሰቡን ከፕሬዝዳንትነታቸው በማስወረድ “የትምህን ግባ” ማለት አልቻሉም፡፡ ያን የመሰለ ባለ ራእይ መሪ ይህን ማድረግ ለምን ተሳነው?
ምክንያቱ ግልፅ ነው፡፡ አቶ አያሌው ዙሪያቸውን ያሰለፉት የጎጥ ሀይል ቀላል አይደለም፡፡ ከላይኛው የክልል ካቢኔ ጀምሮ፣ የቢሮ ሀላፊዎች፣ ምክትሎቻቸው፣ ከምክትሎቹ ስር ያሉ ሌሎች ሀላፊዎች ከ95 በመቶ በላይ ከፍ ሲል የተገለፀውን የአቶ አያሌውን የሹመት ቀመር ተከትለው የመጡ ናቸው፡፡ (እዚህ ላይ ከምክትል ቢሮ ሀላፊዎች በታች ባለ የስልጣን ሹመት ላይ አቶ አያሌ ቀጥተኛ ሚና የላቸውም፡፡ ሆኖም በሹመት ቀመራቸው ያመጧቸውን የራሳቸውን የወንዝ ልጆች በሳቸው ቀመር እንዲመሩ ማድረግ አይሳናቸውም፤ አድርገውታልም፤ ተገምግመውበታልም፡፡)
ስለሆነም አቶ አያሌውን በድንገት እንደ ሙጀሌ ፍንቅል ማድረግ አደጋ እንዳለው ኢህአዴግ አመነበት፡፡ እዚያ ክልል ላይ የሰፈረውን አብዛኛውን ባለስልጣን አስኮርፎ ክልሉን መምራት (እንደፈለጉ ማሽከርከር) እንደማይቻል ኢህአዴግ ልብ አለ፡፡ ምናልባት ቅሬታው ስር ሰዶ በተለይም ደብረ ማርቆስ ወደሚገኘው ህዝብ ሊደርስና ያልተፈለገ መነሳነሳት/ብጥብጥ ሊያስከትል እንደሚችል እነመለስ ሰጉ፡፡ ስለሆነም ግለሰቡን በረጅም ጊዜ ለማውረድ መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆነ፡፡

እናም በክልሉ መስተዳድር መዋቅር ውስጥ የሌለ አደረጃጀት ኢህአዴግ ፈጠረና ከፕሬዝዳንቱ ሰር ሁለት ምክትሎች እንዲኖሩ ተደረገ፡፡ ሁለቱ ምክትሎችም በአቶ አያሌው ዙሪያ ካሰፈሰፉት የጎጥ ቡድኖች ውጭ እንዲሆኑ ተደረገ፤ አቶ አህመድ አብተውና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሆነው ተሸሙ፤ ሁለቱም ከወሎ፡፡ ስለሆነም አቶ አያሌው የነበራቸው ያሹትን የማድረግ ስልጣን በእጅጉ ተገድበ፤ ባጭሩ ተንሳፈፉ፡፡

የተዘረጋውን ጠንካራ የማርቆሴ መዋቅርና የአቶ አያሌውን ተፅእኖ የማዳከሙ ስራ እንደ ተሳካ ሲታወቅ የይስሙላው የአማራ ክልል ም/ቤት ተጠራ፤ የይስሙላውን የአቶ አያሌው ዱላ ላቀብል የሚል ምክንያት አዳመጠ፤ አፅድቅ የተባለውን አፀደቀ፡፡ በቃ- የሆነው ይኼው ነው፡፡
በነገራችን ላይ ኢቲቪ በአንድ የዜና ስርጭት ላይ፣ የአቶ አያሌውን ከስልጣን መውረድ “ካረዳ” በኋላ፣ ወዲያው በማስከተል በሙሉ አምባሳደርነት መሾማቸውን “ማብሰሩ” ሰውዬው ከፕሬዝዳንትነት በመነሳቱ ቅር የሚላቸውን መገኖች (የማርቆሴ ቡድን) ስሜት ለማከም መሆኑን ልብ ይሏል፤ ኢህአዴግ እንዲህ ነው መፍራት ሲጀምር ልክ የለውም፣ መድፈር ሲያበዛ ልክ እንደሌለው ሁሉ፡፡

ሌላው ለአቶ አያሌው ከስልጣን መሳነት እንደ ተጨማሪ ምክንያት ሊቀርብ የሚችለው፣ የምስራቅ ጎጃም በተለይም በሞጣ የአዲስ አበባ መንገድ አቅጣጫ ያለው ህዝብ ተደጋጋሚ ቅሬታና አቤቱታ ነው፡፡ የአዲስአበባ-ሞጣ-ባህር ዳር የጠጠር መንገድ በአስፋልት እንዲሰራ የአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠያቄ ሲያቅርብ ኖሯል፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር – አቶ መለስ – ለህዝቡ ቃል የገቡ ቢሆነም እስካሁን ድረስ የመንገድ ስራው ሊጀመር አልቻለም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው ተጠያቂ፣ የአካባቢው ህዝብ እንደሚናገረው፣ አቶ አያሌው ናቸው፤ “አቶ አያሌው በስልጣን እያለ የኛ መንገድ አይሰራም” በማለት ቅሬታቸውን በምሬት ይናገራሉ፡፡ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉ ወጥተዋል፡፡ ግን አቶ አያሌው ለምን ችክ ብለው መንገድ ግንባታውን ያሰናክላሉ?

የአካባቢው ተወላጅ ምሁራን እንደሚሉት የሞጣው መንገድ መሰራት ከአዲስ አበባ-ባህር ዳር ያለውን ርቀት ቢያንስ በ70 ኪሎ ሜትር ስለሚያሳጥረው፣ በነባሩ መስመር ማለትም በቡሬ በኩል ባሉት ከተሞች ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅኖ ይኖረዋል፤ ያለ ጥርጥር ብዙዎቹ ተሸከርካሪዎች በሞጣው መስመር ስለሚሄዱ የቡሬ መስመር ነጋዴዎች በተለይም ሆቴሎች ገቢ ትርጉም ባለው ሁኔታ ማሽቆልቆሉ አይቀሬ ነው፡፡ ደብረ ማርቆስ ያለችው ደግሞ በዚሁ የቡሬ መስመር ነው፡፡ አቶ አያሌው ደግሞ ከዚህች አካባቢ ምሁራን ብቻ ሳይሆን ከከተማዋ ጋር ያላቸው ፍቅር ወደር የለውም፡፡ እናም ለጎጣቸው ሲሉ የጎረቤታቸውን ጎጥ መልማት ሲከላከሉ ነው የኖሩት፡፡
እና ኢህአዴግ እኒህን ሰው ከስልጣን ማንሳት ይነሰው?