የዐማራ ህዝብ ቁጥር 50.57 ሚሊዮን

By  Ethio Tikdem

አንዳንድ እንሽላሊቶች በቴሌቪዥን፣ ጥቂቶች ደግሞ በጥራዝ ነጠቅነት በየድህረ ገጹ እንደሚያራግቡት ሳይሆን የዐማራ ህዝብ ትክክለኛውን ቁጥርና በመንግስቱ ሊካተቱ የሚችሉትን ከብዙ ጥናትና መረጃ ማሰባሰብ በኋላ ዛሬ ይፋ ታደጋለች – ቤተ አማራ። ይፋ ለማድረግ የተገደድነው በህዝባችንና በአለም ማህበረሰብ ዘንድ የተዛባና እጅግ የተንሸዋረረ አመለካከት ሲፈጥሩ የቆዩትንና ወደፊትም ሊፈጥሩ የሚያሰፈስፉትን ጠላቶች ወደ ሰውነት ደረጃ ተመልሰው ቆም ብለው እንዲያስቡ ለማስገንዘብ ሲሆን የዐማራ ህዝብም ወገኑን፣ አኗኗሩንና ጥንካሬውን አይቶና መዝኖ እንዲተሳሰብና ራሱን እንዲያስከብር ይረዳን ዘንድ ነው።

አጠቃላይ ቁጥር የዐማራ ቁጥር:-

ሀ) #በኢትዮጵያ:
1. ሀገረ ዐማራ 19.4 ሚሊዮን
2. ኦሮሚያ 9.7 ሚሊዮን
3. አዲስ አበባ መስተ. 3.2 ሚሊዮን
4. ደቡብ ብሄረሰቦች ክ. 1.6 ሚሊዮን
5. ቤኒ. ጉምዝ ክልል 0.27 ሚሊዮን
6. ድሬዳዋ መስተዳድር 0.18 ሚሊዮን
7. ትግራይ ክልል 0.116 ሚሊዮን
8. አፋር ክልል 0.130 ሚሊዮን
9. ጋምቤላ ክልል 0.080 ሚሊዮን
10. ሶማሊ ክልል 0.075 ሚሊዮን
11. ሀረሪ ክልል 0.019 ሚሊዮን

12. ቅይጥ አማሮች 8.21 ሚሊዮን

#ኢትዮጵያ ውጭ:
1. አማራ 1.9 ሚሊዮን
2. ቅይጥ አማሮች 0.4 ሚሊዮን

ሐ) #በዐማራ_መንግስት
የሚካተቱ
(በአርበኝነት፣ በታሪክ
በስነልቦና በባህልና
በመሳሰሉት ከአማራ
ህዝብ ጋር የማይለያዩና 3.19 ሚሊዮን
ከአማራ ጋር ለመኖር
እጅግ ልባዊ ፍቅር ያላቸው)

#ድምር 50.57 ሚሊዮን
****^*********
50, 570,000 ህዝብ ያላት ፍትሀዊ #የአማራ_መንግስት!
ይህ አሀዝ በአማራ ልጆችና ወዳጆች ወጥና የጸና ይሆናል። ከጠላት ግን ምንም አንጠብቅም!
—————————————-————
እንግዲህ ይህ ቁጥር የሚያመለክተው በጠላቶችችን ተጨፍጭፈው ያለቁትን 3 ሚሊዮን አማሮች አይጨምርም።
ስብጥሩ እንደሚያመለክተ ዐማራ ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ያለውን ትሥስርና ተከባብሮ የመኖር ጸጋውን ነው።
አማራ ባላጸደቀውና ባልተወከለበት ህገ መንግስት፣ በበታችነት ስሜት ጥላቻ በቁማቸው በነቀዙ ፍጡራን የመቃብር ድንጋይ ተጭኖበት ሲሶ ክፍለ ዘመን ሊደፍን ነው።

የዐማራ ህዝብ በያለበት ከወገኑና ከራሱ ጋር ይመካከር። ሁሌም ነቅቶ ማንነቱን ያስከብር።
ራሱ ሳይኖር አገሩን ያስከበረ ማነም የለምና፣ ሁሉም ዐማራ ህልውናውን ያስቀድም።

#ዐማራ_የነጻነት ትርጉም!
ለራስህ የሚበጅህን መንግስት መስርት።

አናንያ ሶሪ ‘ና ፋና

የአማራ ወጣቶችን የሚያስገደሉ 72 ባለሥልጣናትና ደኅንነቶች ተለይተው ታወቁ

የአማራ ወጣቶችን የሚያስገደሉ 72 ባለሥልጣናትና ደኅንነቶች ተለይተው ታወቁ

ከሕወሓት መልዕክት እየተቀበሉ ወጣቱን በማሳፈስ እና ጊዚያዊ የፌድራል ፖሊስ እና መከላከያ ኃይል ጊዚያዊ ማዘዥያ እዝ ከመንግሥት በጀት በመመደብ፤ መኪና በማቅረብ እና በማቀናጀት በቀጥታ እየመሩት ያሉ አማራ ነን የሚሉ ባለስልጣናት ተቃወቁ፡፡ የአማራውን ተጋድሎ በሚመሩ የጎበዝ አለቆች ከተባባሪ የአማራ ተወላጅ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የፖሊስ ኃላፊዎች ጋር በመተባበር 72 ሕወሓትና የሕወሓት ቅጥረኛ ባለሥልጣናትና ደኅንነት አባላት በስም ተለይተዋል፡፡
ጥናቱን ያካሔደው የጎበዝ አለቆች ቡድን ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሔር የተባለችውን የትግራይ ተወላጅና የክልሉ የኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊዋን በቀዳሚ ጠላትነት አስቀምጧል፡፡
ሁለተኛው አቶ ብናልፍ አንዷለም ሲሆን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ም/ርዕስ መስተዳድር ሲሆን በየቦታው የታሰሩ እና የታጎሩ የአማራ ልጆችን ጉዳይ ይዞ በመምራት እና አስካሁን የታሰሩት ያለምንም መፍትሔ ብርሸለቆና ሰባታሚት ብሎም በየጣቢያው ለሚሰቃዩ ወገኖች ዋናውን ኃላፊነት ድርሻ ወስዷል፡፡
በተጨማሪም አቶ ደሴ አሰሜ፤ የአማራ ክልል አሰተዳደር እና ፀጥታ ጉዳየች ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አየለ አናውጤ የክልሉ የመረጃ እና ደህንነት ጉዳይ ዋና የስራ ሂደት መሪ፣ አቶ ደሴ ደጀን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር፣ አቶ የማነ ነገሽ የአማራ ክልል አሰተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዩች ቢሮ የመረጃ እና ስምሪት ኮሚቴ አባል ናቸው፡፡
በተለይም በአሁኑ ስዓት በመላው የአማራ ክልል እየተቀጣጠለ ያለውን አመፅ እና ከግብ እንዳይደረስ ሕወሓት አዋቅሮ እያሰራቸው የሚገኙ የክልሉ 72 ባለስልጣናት እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡
1. ከማነደር ኢሳያስ ገ/ ኪዳን ከብሄራዊ ደህንነት መረጃ
2. አቶ ይርሳው ታምሬ
3. አቶ ብናልፍ አንዷለም
4. አቶ አለምነው መኮንን
5. ዶ/ር ተሾመ ዋለ
6. አቶ ፍርዴ ቸሩ
7. አቶ አወቀ እንየው
8. አቶ አየልኝ ሙሉዓለም
9. አቶ አየነው በላይ
10. አቶ ደሴ አሰሜ
11. አቶ ዘመነ ፀሃይ
12. አቶ ንጉሱ ጥላሁን
13. አቶ ተስፋየ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ገበያልማት ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ፈንታ ደጀን
15. አቶ ደሳለኝ ወዳጀ
16. አቶ በላይ በጤና ቢሮ የወባ መከላከል የስራ ሂደት መሪ
17. አቶ ሃብቴ በትምህርት ቢሮ የአይሲቲ ክፍል ኃላፊ
18. አቶ ማማሩ ጽድቁ
19. ም/ኮሚሽነር ደስየ ደጀን
20. አቶ መኮንን የለውምወሰን የአብቁተ ዋና ዳይሬክተር
21. አቶ መላኩ አለበል የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ
22. አቶ ምስራቅ ተፈራ የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ
23. አቶ ምትኩ የጥረት ኮርፖሬት ምክትል ስራ አስፈፃሚ
24. አቶ ስዩም አዳሙ
25. አቶ ሙሉጌታ ደባሱ
26. አቶ ስዩም አድማሱ
27. አቶ ተፈራ ፈይሳ
28. አቶ ሺፈራው ግብርና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ
29. አቶ ተስፋየ የልህቀት ማዕከል ኃላፊ
30. አቶ ቴዎድሮስ የቀድሞ ጣና ሃይቅ ትራንስፖርት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረ አሁን መቅደላ ኮንስትራክሽን
31. አቶ ዘላለም ህብስቱ
32. አቶ የማነ ነጋሽ
33. አቶ ጌትነት የገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
34. አቶ ስለሺ ተመስገን
35. አቶ ዘላለም የግብይት ልማት የስራ ሂደት መሪ
36. አቶ ዳንኤል የሆቴሎች ማህበር ፕሬዚደንት
37. አቶ ኃ/ኢየሱስ ፍላቴ
38. አቶ ብርሃኑ የባህል፣ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ
39. አቶ ላቀ ጥላየ
40. አቶ ሙሃመድ አልማ ምክ/ስራ አስፈፃሚ
41. አቶ አለማየሁ ሞገስ
42. አቶ አጉማስ የከተሞች ልማትና ግንባታ አክስዮን ማህበር ኃላፊ
43. አቶ ደመቀ የከተሞች ልማትና ግንባታ አክስዮን ማህበር ባለሙያ
44. አቶ አሻግሬ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የህፃናት የስራ ሂደት መሪ
45. ዶ/ር ፋንታሁን መንግስቱ
46. አቶ አየለ አናውጤ
47. አቶ ሃብታሙ የርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮቶኮል
48. ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሄር
49. ወ/ሮ አበራሽ በክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረች ነባር ታጋይ
50. አቶ ፈለቀ ተሰማ
51. አቶ ጌታ ኪዳነ ማርያም
52. አቶ ገሰሰው ግብርና ሜካናይዜሽን ተመራማሪ
53. አቶ ዳኜ በጤና ቢሮ የሃይጅንና ሳኒቴሽን ባለሙያ
54. አቶ ፈንታው አዋየው
55. ወ/ሮ ዝማም አሰፋ
56. ዶ/ር አምላኩ አስረስ
57. አቶ ደጀኔ ምንልኩ
58. ወ/ሮ ትልቅ ሰው ይታያል
59. አቶ ላቀ አያሌው
60. አቶ ባይህ ጥሩነህ
61. አቶ ጥላሁን የክልል ም/ቤት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ
62. አቶ ፍስሃ ወ/ሰንበት
63. አቶ ጌታቸው በት/ት ቢሮ የፈተና ኤክስፐርት
64. ዶ/ር ይበልጣል ቢያድጌ
65. አቶ አቃኔ አድማሱ
66. አቶ የኔነህ ስመኝ
67. ኮማንደር ሰይድ የፖሊስ ኮሚሽን
68. አቶ አስናቀ በኢት. ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ኃላፊ
69. አቶ ሙሉጌታ ከግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት
70. አቶ ባየ ከልህቀት ማዕከል ኃላፊ
71. አቶ አምባው አስረስ
72. ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ
የወይዘሮ ገነት ገ/እግዚአብሔርንና የሌሎች የሕወሓት አባላት ዝርዝር መረጃዎችም አብረው ተልከዋል፡፡

#AmharaResistance 

ታላቁ የ TPLF ሴራ በ አማራ ህዝብ ላይ

ታላቁ የ TPLF ሴራ በ አማራ ህዝብ ላይ ባጭሩ ይህን ይመስላል!

የአማሮች ደም ይመለሳል!
(ሳምሶን ኃይሌ)
ነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን በሚቆጣጠረው የፌደራል መንግሥት በኩልና በተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስትር አማካይነት በሕዝባችን ላይ ጦርነት አውጇል፡፡ አጋዚ የተባለው የዚህ ግፈኛ ቡድን ነብሰ ገዳይ ጦር መብታቸውን በሚጠይቁ አማሮች ላይ እያነጣጠረ በመተኮስ ሕፃናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ገድሏል፡፡ አሁንም በዚኸው ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት እርምጃው ቀጥሎበታል፡፡ ወያኔዎች የዘረፉትን የኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሀብትና የሚመሩትን ታይቶ የማይታወቅ የቅንጦት ኑሮ እንዲሁ እንደዘበት አሳልፈው ይሰጣሉ አይባልም፡፡ እንዳበደ ውሻ እየተቅበዘበዙ መናከሳቸው አይቀርም፡፡ መግድላቸውም የሚጠበቅ ነው፡፡
የወሮበላው ቡድን ጭቆና ያንገፈገፈውና የአባቶቹን መሬት ለማስመለስ የቆረጠው የአማራ ሕዝብ ግን አሁንም ከጥይት ጋር በጽናት እየተፋለመ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የቱንም ያህል ቢገድሉት ሕዝባችን ከዚህ ግፈኛ ወሮበላ ቡድን አገዛዝ ነጻ ለመውጣትና የወልቃይት ጠገዴን መሬት ለማስመለስ ቆርጧልና፣ ሺሕዎችን ገብረንም ቢሆን ነጻ እንወጣለን እንጂ ባርነት ምርጫችን አይሆንም፡፡ ይልቁንም፣ የአርበኛ አባቶቹንና አያቶቹን አልበገር ባይነትና ጽናት የወረሰ ደም መላሽ ትውልድ ስለተፈጠረ፣ እስካሁን በነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን የተገደሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደምም እንዲሁ እንደዋዛ ፈሶ የሚቀር አይሆንም፡፡ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይመለሳል!!!
ሕዝባችን ከየትኛውም ሕዝብ ጋር በሰላም የሚኖር ደግ ሕዝብ ነው፡፡ ከየትኛውም ሕዝብ ጋርም ጠብ የለንም፡፡ የእኛ ግንባር ቀደም ጠላት፣ ከትናንት እስከዛሬ ድረስ በሕዝባችን ላይ የዘመተው ወሮበላው ወያኔ ነው፡፡ ስለሆነም በምንችለው ሁሉ እነዚህን ነብሰ ገዳዮች እንፋለማቸዋለን፡፡ እነሱ ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ እስካልወረዱ ድረስ ሰላም አናገኝም፡፡ እነዚህ የባንዳ ልጆች ገዳዮቻችን ናቸውና ከእነሱ ጋር ምንም ዓይነት ኅብረት የለንም፡፡
ወሮበላው ቡድን በለየለት ቂም በቀል ተነሳስቶ በሕዝባችን ላይ የጥይት ናዳ ማዝነቡንና ብዙዎችን መግደሉን ቀጥሎበታል፡፡ በሳሞራ የኑስ የበላይ መሪነት የሚንቀሳቀሰው ነብሰ ገዳዩ የአጋዚ ጦር በሕዝባችን ላይ የለየለት የዘር ፍጅት እየፈጸመ ነው፡፡ ሆኖም ወሮበላው የወያኔ ቡድን የትኛውንም ያህል ጦር ቢያዘምት፣ የአርበኛ አያቶቹን መንፈስ የወረሰ ደም መላሽ ትውልድ ተፈጥሯልና ከዚህ በኋላ የአማራን ሕዝብ ማንበርከክ ጨርሶ አይቻልም፡፡
ውለታ ቢሶች ስለሆኑ ሙታቸውን አልቅሶ እየቀበረ፣ ቁስለኛቸውን እየተንከባከበና ሠራዊታቸውን እያበላ አሳልፎ ለሥልጣን እንዲበቁ ያደረጋቸውን ሕዝብ ውለታ ክደው በአማራ ሕዝብ ላይ ያልፈጸሙት በደል የለም፡፡ በእንቡጥ ሕፃናትን ላይ ጥይት አርከፍክፈው በርካቶችን ፈጅተዋል፤ የአማራ እናቶችን አስለቅሰዋል፡፡ ለዚህ ነው ኅብረት የለንም፤ አንፈልጋቸውም፤ ሌላው ቀርቶ ከለቅሷችን አይድረሱ፣ እኛም ከእነሱ ለቅሶ አንሔድም የምንለው፡፡ መቼም ቢሆን ከገዳዮቻችን ጋር ኅብረት አይኖረንም፡፡ ይልቁንም፣ ለእኛ ፍትሐዊም ተገቢም የሚሆነው የተገደሉብን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደም መመለስ በመሆኑ፣ ተቀዳሚ ተግባራችን ይህንን ተልዕኮ መወጣት ብቻ ነው፡፡
ጦርነቱ የወሮበላው ወያኔና የአማራ ሕዝብ ጦርነት ነው፡፡ በዚህ በአማራ ሕዝብ ላይ በታወጀ ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት ጦርነት ላይ የሌሎች ብሔረሰቦች ልጆች የወያኔ መሣሪያ ሆነው በሕዝባችን ላይ እንዳይተኩሱ አጥብቀን እንመክራለን፡፡

ዝቋላ ሀገሩ የት ነው?

በ ዳንኤል ክብረት

የዚህች ሀገር ባለቤቶች ሁላችንም ካልሆንን በቀር በተናጠል ማንም ባለ ግዛት ሊሆን አይችልም፡፡ ሉሲ አማራ ትሁን ኦሮሞ፣ አፋር ትሁን ሶማሌ፣ ጉሙዝ ትሆን ትግሬ፣ ወላይታ ትሁን ጋሞ የሚያውቅ የለም፡፡ በአኩስምና አካባቢው በተገኙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ነገሥታቱ የሚገዙትን ሀገር ሕዝቦች ስም ይዘረዝራሉ፡፡ እጅግ የሚገርመው ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካና የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የምንሻኮተው ብዙዎቹ ጎሳዎች/ነገዶች ስማችን የለም፡፡ ሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ከተለያየ ቦታ መጥተን የሠፈርንበት ላይ ረግተን ነው ዛሬ የምንገኘው፡፡ የሕዝብ የሥፍራ ንቅናቄ የታሪኳ አንዱ መገለጫ በሆነቺው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ሌላውን ሀገርህ አይደለም፣ ክልልህ አይደለም፣ መሬትህ አይደለም እንደማለት ያለ ታሪካዊ ኃጢአት የለም፡፡ ትንሽ በታሪክ ወደኋላ ስንጓዝ ዛሬ ክልልና መንደር በመሠረትንበት ቦታ ሌሎች ሲኖሩበት እናገኛለን፡፡ አሁን የያዝነው ቦታ ከምእተ ዓመታት በፊት የሁላችንም አልነበረም፡፡ ሁሉም ሠፋሪ ነው፡፡ ነባር መሬቱ ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የምታዋጣን የሁላችን እንድትሆን አድርገን ከሠራናት ነው፡፡ እንደ አጥር ሠሪ እንስሳት(territorial animals)  ከዚህ በመለስ ማንም አይገባብኝም፡፡ እኔን ያልመሰለውን በዚህ አካባቢ ላየው አልፈልግም የሚለው ሂደት መጨረሻው መበጣጠስ ነው፡፡ የልዩነትን ያህል ተመሳሳይነት ሰፊ አይደለም፡፡ ተመሳሳይነት እጅግ ጠባብ ነው፡፡ አንድ ነኝ ብሎ በሚያስብ ‹ብሔርም ሆነ ብሔረሰብ› ውስጥ አያሌ ልዩነቶች አሉ፡፡ የጎሳ፣ የቤተሰብ፣ የአካባቢ፣ የእምነት፣ የፍላጎት፣ የርእዮተ ዓለም፣ የጾታ፣ የሀብት ደረጃ፣ የሥልጣን፣ ምኑ ቅጡ፡፡ ሁሉም ተመሳሳዩን ፍለጋ ከሄደ መጨረሻው ግለሰብ ነው፡፡ በሰውነት ክፍላችን እንኳን ተመሳሳያቸውን ከሚያገኙት ይልቅ የማያገኙት ይበልጣሉ፡፡ ሰው እንኳን በግለ ሰብእነት ሕልው የሆነው ልዩነትን በአንድ ኑባሬ ውስጥ በማስተናገድ ችሎታ ነው፡፡ አንድን አካባቢ ‹በተመሳሳይነት ሚዛን› አንድነቱን ጠብቆ ማቆየት አይቻልም፡፡

ያማ ቢሆን ኖሮ ሶማልያን የመሰለ ጠንካራና የማይናወጥ መንግሥት አይኖርም ነበር፡፡በእምነትና በቋንቋ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ይሄ ተመሳሳይነታቸው ግን አንድነታቸውን ሊጠብቅላቸው አልቻለም፡፡ ትኩረታቸው ‹ተመሳሳዩን ብቻ ፍለጋ› በሚለው ላይ ስለነበር ወደ ነገድ፣ ወደ ጎሳ፣ ወደ ጎጥ፣ ወደ ቤተሰብ እየወረዱ ነው በጦርነት ሲታመሱ የኖሩት፡፡ ለሶማልያ ችግር መፍትሔው ተመሳሳይን መፈለግ አይደለም ልዩነትን ለማስተናገድ መቻል ነው፡፡ ተመሳሳይነት ጠባብ ነውና፡፡ ጠባብነት ከሚመነጭባቸው ምንጮች አንዱም ‹ተመሳሳይን ብቻ ፍለጋ› ነው፡፡

የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬ በሚታወቅበት ቦታ ላይ ከተገደመ ከ700 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ በዚያ አካባቢ አያሌ መንግሥታትና ሕዝቦች ተፈራርቀዋል፡፡ ገዳሙ ግን መከራ ሲገጥመው እየቀዘቀዘ፣ መከራውን አሸንፎ ደግሞ እንደ ፍግ እሳት እንደገና እየጋመ ከእኛ ዘመን ደርሷል፡፡ ወደዚያ ገዳም የሚገቡ መነኮሳት ሰማያዊቷን ሀገር የሚናፍቁ፣ ጾምና ጸሎትን ገንዘባቸው ያደረጉ፣ የጻድቁን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ ናቸው፡፡ የመነኩሴ ሀገር የለውም፡፡ መነኮሳት እንኳን ከእናትና አባታቸው በተወለዱበት ሀገር ቀርቶ ስማቸውና ታሪካቸው በማይታወቅበት ሀገርም ‹ሀገርህ የት ነው?› አይባሉም፡፡

ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ግብጽ ውስጥ ኖረዋል፣ ሊባኖስ ውስጥ ኖረዋል፣ ሶርያ ውስጥ ኖረዋል፤ ግሪክ ውስጥ ኖረዋል፣ ሮም ውስጥ ኖረዋል፡፡ አርመን ውስጥ ኖረዋል፡፡ ‹ሙሳ አል ሐበሽ› ሶርያ ውስጥ የታወቀ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ነው፡፡ የሶርያ ድርሳናት እንደሚነግሩን ሙሳ (ሙሴ) የዐፄ ገብረ መስቀል ልጅ ነው፡፡ ዛሬ ከኢትዮጵያ በላይ ሀገሩ ሶርያ ናት፡፡ በቅርብ ዓመታት የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ገዳም በሊባኖስ ውስጥ በቁፋሮ ተገኝቷል፡፡ ቫቲካን ውስጥ የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ማረፊያ ለታሪክ ቆሞ ይታያል፡፡ አርመን ውስጥ ኤቺሚዚን የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ገዳም ዛሬም አለ፡፡

እንዲያውም ዛሬ የዝቋላ መነኮሳት እንደገጠማቸው ያለ ‹ሀገርህ አይደለም› የሚል ሰውነት ያልገባው ፈተና ሲገጥማቸው ራሱ ፈጣሪ ነበር ይገሥጽላቸው የነበረው፡፡ በተአምረ ማርያም ላይ የተጻፈውና ኢየሩሳሌም በጦርነት ምክንያት በተዘጋች ጊዜ በ13ኛው መክዘ አካባቢ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘው ኢትዮጵያዊ ታሪክ ለዚህ ማሳያ ሆኖ ይኖራል፡፡ ይህ በኢየሩሳሌም ተሳላሚዎች ሁሉ የታወቀውና ዛሬም ድረስ በጎልጎታ መግቢያ በር ላይ ምልክቱን ትቶ ያረፈው ታሪክ እንዲህ ነበር የተፈጸመው፡፡

ከዛሬ 700 ዓመታት በፊት አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛል፡፡ ከአፍሪካ ምድር የሄደ ብቸኛ ሰው ነበር፡፡ የትንሣኤ በዓል ሲከበር የትንሣኤውን መብራት ከመቃብሩ የሚያወጡት ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ያን ጊዜ ግን ብቻውን ስለነበር ማንም ከቁም ነገር አልቆጠረውም፡፡ እንዲያውም  በመልኩ ምክንያት ተንቆ ‹ያለ ሀገርህ ለምን መጣህ፣ ውጣ› ተባለ፡፡ እርሱም ወጥቶ መግቢያው በር ላይ ሲያለቅስ በላዩ ላይ የብርሃን ዓምድ ተተክሎ ታየ፡፡ ተሳላሚው ሁሉ እምነቱንና ታላቅነቱን አደነቀ፡፡ ብርሃኑ የወረደበት ቦታም ተሰንጥቆ እስከ ዛሬ ድረስ ይታያል፡፡ ወደ ጎልጎታ የሚገባም ሁሉ ይሳለመዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በሌሎች ሀገሮች ሄደው በኪደተ እግራቸው የባረኩት ሁሉ ሀገራቸው ሆኖ መኖራቸው ብቻ አይደለም የሚገርመው፡፡ ከመላው ዓለም የመጡ መነኮሳትም በዚህች ሀገር ውስጥ ‹ከየት መጣችሁ? የማንስ ወገን ናችሁ?›› ተብለው ሳይጠየቁ እንደ ሀገሬው ዜጋ ኖረዋል፡፡ አባ መጣዕ(ሊባኖስ)፣ ተሰዓቱ ቅዱሳን፣ አርባ ሐራ፣ አምስቱ የመንዝ ቅዱሳን፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እጨጌ ዕንባቆም፣ ማኅበረ ጻድቃን፣ እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ መጥተው ኖሩ፡፡ እዚህችም ሀገር ዐረፉ፡፡ ገዳማቸው ገዳማችን፣ ታሪካቸው ታሪካችን ሆነ፡፡

 

ዛሬ ያ ሁሉ ተረስቶ ነው የዝቋላ ገዳም መነኮሳት ዝቋላ ‹ሀገራችሁ አይደለም›› የተባሉት፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያውያን አይደሉምን? እዚህ ቦታኮ ከ700 ዓመታት በላይ ኖረዋል፡፡ እዚህ አካባቢ ከ700 ዓመታት በፊት የነበሩ ዜጎች አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲመጡ ‹ኦቦ› ብለው ተቀበሏቸው እንጂ ‹ሀገርዎ አይደለም ይውጡ› አላሏቸውም፡፡ ዛሬ በሥልጣን ላይ ካሉትና ገዳሙን በኢሬቻ መተካት ከሚፈልጉት ሰዎች ይልቅ ያኔ የነበሩት ሰዎች ልበ ሰፊዎች፣ አስተዋዮች፣ የሰውነት ክብር የገባቸው፣ የሀገርን ትርጉም የተረዱ፣ ከዘር ይልቅ ለሰውነት ታላቅ ቦታ የሚሰጡ፣ ሰውን በምግባሩ እንጂ በቋንቋውና በቀለሙ፣ በዘሩና በአጥንቱ የማይለኩ ነበሩ፡፡

የአንድ ክልል የቱሪዝም ቢሮ አንድን ገዳም ነጥቆ በገዳሙ ሥርዓት የማይፈቀድ ሌላ እምነትን ለመተካት ማነው ሥልጣን የሰጠው? በዚያ ገዳም ክልል ውስጥ ሊከበሩ የሚገባቸው ሃይማኖታዊ በዓላትንስ በምን ቀኖናዊ ሥልጣኑ ነው የሚወስነው? ለምንስ ነው እነዚህን መነኮሳት እየጠራ የሚያስፈራራው? ይኼ ገዳምኮ ዘመናትን ሁሉ ተሻግሮ እዚህ እንዲደርስ ያደረገው በእምነቱ ጽኑ የሆነው የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጅ ነው፡፡ ሕዝቡ እዚያ ገዳም ለጸሎት የተጉ መነኮሳት እንደሚገኙ፣ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቃል ኪዳን ቦታ እንደሆነ የሚያምን ነው፡፡ በየዓመቱ በጥቅምትና በመጋቢት 5 ወደ ቦታው በመሄድ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ከሚያከብረው ሕዝብ አብዛኛው የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጅ ነው፡፡ ታድያ እነዚህ አካላት ይህንን አስተሳሰብ ከየት አመጡት?

ይኼ ተልዕኮ ሃይማኖታዊ ተልዕኮ አይደለም፡፡ የጠብ ጫሪነት ተልዕኮ ነው፡፡ በሰላም የኖረውን ሕዝብ የማበጣበጥ ተልዕኮ ነው፡፡ መጋቢት 5 ቀን በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ‹ኢሬቻን በጠበሉ ቦታ እናከብራለን፣ ሐውልት እናቆማለን› ብሎ በሕዝብ መገናኛ ማወጅ ጠብ ያለሽ በዳቦ እንደማለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ያጸድቀኛል ብሎ ያሰበው እምነት ሊከተል ይችላል፡፡ ሁለት እምነቶች ግን በአንድ ቤተ መቅደስ ሊመለኩ አይችሉም፡፡ ሁሉም የየራሱን ነው መከተል ያለበት፡፡ ‹ከባልሽ ባሌ ይበልጣልና አልጋሽን ልቀቂለት› የሚለው ብሂል ግን ዛሬ የሚያዋጣ አይመስልም፡፡ የሃያ አንደኛው መክዘ ኢትዮጵያንም በጤና አውሎ አያሳድራትም፡፡ በዝቋላ ገዳም ላይ የተጀመረው ርስትን የመንጠቅ ሥራም በዝቋላ የሚያበቃ አይሆንም፡፡ ‹መንግሥታዊ ሃይማኖት የለም› ከተባለ መንግሥታዊ መዋቅሮች አንድን እምነት ደግፈው ሌላውን እምነት ለመጫን እንዴት ቻሉ?

ስለዚህም

  1. ቅዱስ ፓትርያርኩ ሁኔታውን በተመለከተ ለሚመለከታቸው ድብዳቤ መጻፋቸው የሚገባ ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶስ ግን ይህንን ነገር በዕንቁላሉ ለመቅጨት መወሰንና መሥራት ያለበት ጊዜ ዛሬ ነው፡፡ መነኮሳቱና ሀገረ ስብከቱ የጻፏቸው ደብዳቤዎች በገዳሙ ስለደረሰው መከራ ብዙ የሚናገሩት ነገር አለ፡፡ በስብሰባዎች የደረሰባቸው ጫና፣ በየጊዜውም የሚደርስባቸውን እንግልት ገልጠውታል፡፡ ሲኖዶሱ ገዳማትን ከመጠበቅ የሚቀድም ሌላ ኃላፊነት የለውም፡፡
  1. ምእመናንም ገዳሙን በንቃት መከታተልና በተለይም በመጋቢት 5 ቀን በክብረ በዓሉ በመገኘትና በዓሉን በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት በማክበር ለቅዱሱ ሥፍራ ያለንን ፍቅር፣ ለመነኮሳቱ ያለንን የዓላማ አንድነት፣ ሁላችንንንም ለሚያቅፈው ኢትዮጵያዊነት ያለንንም ክቡር ሥፍራ ማሳየት አለብን

 

  1. መንግሥትም በጥባጭ ካለ ጥሩ ለመጠጣት አይቻልምና በሚዲያ የተሳተው በሚዲያ፣ በአሠራር የተበላሸውም በአሠራር እንዲታረም ማድረግ ይገባዋል፡፡

የ‹አማራ›ና ‹ቅማንት› ጉዳይ

በ ሙሉቀን ተሰፋው

የ‹አማራ›ና ‹ቅማንት› ጉዳይ
=====================

ይህን ጉዳይ ስሸሸዉ የቆየሁት ነገር ነዉ፡፡ እርግጥ አንድ ጊዜ ፋክት መጽሄት ላይ ነካክቸዉ ነበር (ያኔ ኤዲት ሲደረግ የኔን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ይዞ ባይወጣም) ግን እስከ መቼ እየሸሸሁትስ እዘልቃለሁ? የማያስኬድ ነገር ሲሆንብኝ ይህን ሀሳብ ለመሞነጫጨር ተገደድኩ፡፡ ያለዉን ነበራዊ ሁኔታ በዚህ መልኩ ማስቀመጡ ጠቀሜታም ጉዳትም ይኖረዋል፡፡
ጉዳቱ አንዳንድ የአስተሳሰብ ስንኩላን ከእሳቱ ላይ ቤንዚን ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ በሌላ መልኩ ጠቀሜታዉ ደግሞ የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና በመጨመር እየተፈጠረ ላለዉ ሁናቴ መፍትሄ ሊያፈላልጉ የሚችሉ ግለሰቦችና ምሁራን አይጠፉም፡፡ ጥቅሙንም ጉዳቱንም በመመዘን ለአንባቢያን ማሳወቁ ይጠቅማል ብየ ስላሰብኩ በሚከተለዉ መልኩ አስቀምጨዋለሁ፡፡
የዛሬ ወር አካባቢ መሆኑ ነዉ፡፡ ከአዘዞ አጼ ቴዎድሮስ አዉሮፕላን ማረፊያ ወደ ፒያሳ አንዲት ቢጫ ታክሲ ኮንትራት ይዣለሁ፡፡ የታክሲዉ አሽከርካሪ ደስተኛ አለመሆኑ ፊቱ ቢመሰክርም ምን እንደሆነ መጠየቅ አልፈለግኩም፡፡ ግን በራሱ ጊዜ የሆነዉን ነገረኝ፡፡
እድሜዎ በአርባዎቹ መካከል የሚገኘዉ የታክሲ አሽከርካሪ ያስከፋዉ ነገር ሚስቱንና የልጆቹን እናት ያጣበት ምክንያት ነዉ፡፡ ‹‹አስራ ሰባት (17) አመታት ከሚስቴ ጋር አብረን ስንኖር ስለ እርሷ ዜግነት(?) የማዉቀው ነገር አልነበረኝም፡፡ ሰዉነቷ ብቻ በቂዬ ነበር፡፡ እዉነቴን ነዉ የምልህ የጎንደር ልጅ ከመሆኗ ዉጭ የማዉቀው አልነበረኝም፡፡ በጋብቻችን ለአቻዎቻችን አርኣያ የምንሆን ነበርን፡፡ በትዳራችን 3 ልጆችን አፍርተናል፡፡ የመጀመሪያዋ 16 አመቷ ነዉ፡፡ ባለፈዉ የጥቅምት መድሀኒዓለም እናቷ ደወለችልኝና ለመድሀኒዓልም ዝክር ዝግጅት ታግዘኝ ላካት አለችኝ፡፡ እኔም በደስታ እናቷን እንድታግዝ መሄዷን በደስታ ተቀበልኩ፡፡ የጥቅምት መድሀኒዓለም አልፎ ግን ከነገ ዛሬ ትመጣለች እያልኩ ከልጆቼ ጋር ብናያት የዉሃ ሽታ ሆነች፡፡ ስልክ ስንደዉል ስልኳን ዘግታለች፡፡ መጨረሻ ቤተሰቦቿ ካሉበት ቦታ ትክል ድንጋይ ሰዉ ተላከ፡፡
‹‹ልጃችን ‹አማራ› አግብታ አትኖርም! የሚል መልስ ከእናቷ ሰሙ የተላኩት ሰዎች፡፡ ሶሰት አመት ያልሞላዉን ህጻን ልጅ እና ሌሎቹንም ልጆቿን ትታ ለመቅረት እንደወሰነች ሰማሁ፡፡ በቄስ በሽማግሌ አስጠየቅኳት፡፡ ወይ ፍንክች የአባ ቢለዋ ልጅ! ልጆቼ ሲያድጉ ሰራተኛ አላያቸዉም፡፡ ሙሉ በሙሉ የሚያስፈልጋቸዉን ሁሉ እርሷ እና እኔ ነን የምናሟላቸዉ፡፡ ሰራተኛ አሁን አስገብቼ ለትምህርት ቤት ምሳ እንድትቋጥር ሳደርግ ልጆቹ ሳይበሉት እየተመለሱ እርሃብ ሊገድላቸዉ ሆነ፡፡ አሁን የቤቱንም የዉጩንም ስራ ብቻየን ይዠዋለሁ›› በማለት ልብን የሚሰብረዉን ግለ ታሪክ አጫወተኝ፡፡
ሌላዉ አጋጣሚ ደግሞ እንደዚህ ነዉ፡፡ በህዝብ ትራንስፖርት ወገራ አዉራጫ ዉስጥ ኮሶዬ ከሚባል ቦታ ደርሼ ለመምጣት ተሳፈርኩ፡፡ መኪና ውስጥ ከፖለቲካ ዉጭ የሚወራ ወሬ መጥፋቱን አስተዋልኩ፡፡ በቃ ግማሹ መንግስትን ተቃዉሞ ከፊሉ ደግሞ መነታረክ ነዉ፡፡ ስሄድ ምንም ሳልናገር ደረስኩ፡፡ ስመለስም ሌላ የፖለቲካ ንትርክ ካለባት ሚኒባስ ውስጥ ገባሁ፡፡ እርግጠኛ ነኝ- የፓርላማ ሰዎች ያን ያክል ውይይት አያደርጉም፡፡ ወደ ጎንደር ከተማ ስንቃረብ ግን ፖለቲካዉ ‹ቅማንት- አማራ› ሆነ፡፡ አንድ መሀል ሰፋሪ ወጣት ነገሩን አቀጣጠለዉ፡፡
ከአምባ ጊዎርጊስ የተሳፈረ ግለሰብ ሸምበቂት ከምትባል አነስተኛ መንደር ሲወርድ ‹አቀጣጣዩን› ልጅ ‹ቅማንት ስለሆንክ እወድሀለሁ!› ብሎት ወረደ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ይህ ጎጠኝነት ገበሬዉ ድረስ ስር መስደዱ አሳዘነኝም አንገበገበኝም፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ከጀርባየ ካለዉ ወንበር የተቀመጡት ሁለት ሰዎች ሊደባደቡ ሲታገሉ ዞርኩ፡፡ መኪናው ቆሞ ሰዎቹን መገላገል ያዝን፡፡
ከአፍታ በፊት በወዳችነት ሲያወሩ የነበሩት ግለሰቦች ለምን እንደተጣሉ አጣራንና የበለጠ አዘንን፡፡ ሊደባደብ የሚገለገለዉ ሰዉዬ ‹እኔ በአባቴ ቅማንት ነኝ፡፡ እርሱም ቅማንት ነዉ፡፡ የሚኖረዉ ጎንደር ዙሪያ ሆኖ ሳለ እባክህ በእናንተ አካባቢ ‹ኮሶየ› ምሽት ፈልግልኝ አለኝ፡፡ ጎንደር ዙሩያ ጠፍቶ ነዉ ኮሶየ ድረስ ምሽት ፍለጋ የምትመጣዉ? ስለዉ ከዚህማ ሁሉም አማራ ሆነብኝ፡፡ ቅማንት ከእናንተ አካባቢ ብዙ አለ ብየ እኮ ነዉ ይለኛል፡፡ አማራ ቢሆኑ ምን ችግር አለዉ? ብየ ስመልስለት ‹ደሞ ከነዚህ ‹እንትኖች› ጋር ነዉ የምጋባዉ? ሲለኝ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ!›› በማለት ሲያብራራ እኔ የምናገረዉ ስላልነበረኝ ዝም አልኩ፡፡ አብረዉ የነበሩ ሊደባደቡም የከጀሉ፣ የተጨቃጨቁም፣ ብዙ ያወሩም አሉ፡፡
የተሳደበዉ ግለሰብ ዝምታን መርጧል፡፡ ጥፋተኛነቱን ያመነ ይመስል ነበር፡፡
ግን ከዚህ ሁሉ ምን እንመለከታለን? ዘረኝነትና ጎጠኝነት ገጠር ካልተማረው ማህበረሰብ ድረስ ገብቷል፡፡ በአርማጭሆ፣ ወገራና መተማ በዚህ አመት ብቻ በርካታ ጥንዶች ትዳራቸዉን አፍርሰዋል፡፡ ልጆቻቸዉን በትነዋል፡፡ በሰሜን ጎንደር ዞን ያሉ ፍርድ ቤቶች በዚህ አመት ያስተናገዱት የፍች ጥያቄ ከዚህ በፊት ካለዉ ዘመን ጋር የሚነጻጸር አይደለም፡፡
ለእኔ እስከሚገባኝ ቅማንትና አማራ መካከል ምንም ልዩነት አላየሁም፡፡ የሚኖረበት ቦታ፣ የሚናገሩት ቋንቋ፣ የሚያመልኩት ሀይማኖት፣ የሚመገቡት…. ሁሉ ተመሳስሎ ሳለ ለምን ግን መለያየት አስፈለገ? የ‹ቅማንት ብሄረሰብ› አለባቸዉ በተባሉ ቦታዎች ሁሉ ዞሬ ለመታዘብ እንደቻልኩት ከ‹አማራዉ› የተለየ ቋንቋና ባህል አልገጠመኝም፡፡ ይህ መሬት ላይ ያለ እዉነታ ነዉ፡፡ ቅማንት የሚባል ቋንቋ ነበር፡፡ አሁንም በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች እንችላለን ያሉኝ አሉ፡፡ አባ ወንበሩ መርሻ (የቅማንት መሪ) ከመሞታዉ በፊት ይህን ጉዳይ አረጋግጠዉልኛል፡፡
በእኔ እምነት ይህ ቋንቋ ፈጽሞ ከመጥፋቱ በፊት ዩንቨርሲቲዎቻችን (በተለይም የጎንደር ዩንቨርሲቲ) መዝገበ ቃላትና ሰዋሰዉን ማስቀረት አለባቸዉ፡፡ ፈቃደኛ የሖኑ ሰዎችም ሊማሩበት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ መሰረታዊ እዉነታ መሬት ላይ ባለበት መልኩ እርስ በራስ ቅራኔ ውስጥ መግባቱ እጅግ አስቀያሚና ኋላ ቀር የሆነ አስተሳሰብ ነዉ፡