ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ለውጥ እና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን-(ከኤፍሬም እሸቴ)

Adebabay  (ከኤፍሬም እሸቴ)

ኢትዮጵያ የለውጥ ማዕበል ውስጥ ናት። በመላው አገሪቱ የተቀሰቀሰው እምቢተኝነት በመንግሥት በኩል የገጠመው ጠንካራ እጅ ብዙ ዜጎችን ለሞት፣ ለእስር፣ ለስደት እና ለንብረት ውድመት የዳረገ ሆኗል። በመሆንም ላይ ይገኛል። ይሁን እንጂ የመንግሥት የብረት ጡጫ (አይረን ፊስት) ነገሮችን ከማረጋጋት ውጪ የበለጠ ቀውሱን እያሰፋውና እያበረከተው በመሔድ ላይ ይገኛል። በመንግሥት የሚፈጸሙት መንግሥታዊ ሽብሮች ደግሞ እንደ ቀድሞው ዘመን ተደብቀው የሚቀሩ ሳይሆን በተለያዩ ዘዴዎች ለሕዝብ ዓይንና ጆሮ የሚደርሱ ሆነዋል። በአልሞ ተኳሾች የተገደሉ ወጣቶች፣ በፖሊሶች ድብደባ ሲፈፀም የሚያሳዩ አሰቃቂ ቪዲዮዎች፣ ቃለ ምልልሶች እና የተቃጠሉ ንብረቶች ዘመኑ በፈቀዳቸው ቴክኖሎጂዎች በመሰነድ ላይ ይገኛሉ። ሌላው ቀርቶ መንግሥት ራሱ በምስጢር የሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የድምጽ ቅጂዎች የአደባባይ ሲሳይ በመሆን ላይ ናቸው። በዚህ ዘመን ተወርቶና ተፈጽሞ ተደብቆ የሚቀር ምንም ምሥጢር ምንም ወንጀል አይኖርም።

የለውጡ ማዕበል አንዴም ለብ፣ አንዴም ሞቅ፣ አንዴም በረድ እያለ የከረመ ሲሆን አሁን ግን በተለይም በኮንሶ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ አያያዙን በማጠናከሩ ወደኋላ ከማይመለስበት ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስላል። በአገር ውስጥ ብቻ የሚከናወነው ተቃውሞ አድማሱን በማስፋት በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በስፋት በማጠቃለል ላይ ነው። በዚያውም መጠን የመንግሥትም ጭካኔ የተሞላበት ርምጃ በከፋ መልኩ ቀጥሏል። መንግሥት በሚያደርገው ሰፊ እንቅስቃሴ ተቃውሞው በተለይ የምዕራባውያን ድጋፍ ሳያገኝ ለመቆየት የቻለ ቢሆንም አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ተቃውሞውን ለዓለም ከገለጠ በኋላ ምዕራባውያንም የሚያውቁትን፣ ነገር ግን ጀርባቸውን የሰጡትን ቀውስ በይፋ ወደመቃወም መግባታቸው እየታየ ነው። ይህ ጽሑፍ በሚዘጋጅበት ወቅት እንኳን የአሜሪካ ኮንግረስ ጉዳዩን ወደ ሕግ ደረጃ ለማድረስ ረቂቅ መዘጋጀቱን ጉዳዩን የሚመሩት የኒውጄርሲ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ (Chris Smith) ገልጸዋል።

http://amharic.voanews.com/a/usa-congressman-chris-smith-on-ethiopian-human-right/3505870.html?nocache=1

የቀውሱ መጠን ከአገር አልፎ ዓለም አቀፍ ትኩረት ባገኘበት በአሁኑ ወቅት እኛ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የኢሕአዴግ አጋር የሆኑትን ምዕራባየውያንንም ሳይቀር የሚያሳስባቸው «ቀውሱ በምን መልክ ይጠናቀቃል?» የሚለው ጉዳይ ነው። ይህንን የሚገነዘበው ሕወሐት ዜጋውንም ፈረንጆቹንም ለማስደንበር «የሶሪያ»ን ካርድ በመሳብ ላይ ይገኛል። ተቃውሞው ከቀጠለ እንደ ሶሪያ የጦርና የውድመት አውድማ እንሆናለን በማለት ላይ ነው። ሽማግሌዎቹ መሪዎቹ ከጡረታቸው በመሰባሰብ ይህንኑ «የሶሪያ ካርድ»፣ የጀርመኖችን ሆሎኮስት እና የሩዋንዳን ፍጅት በማንሣት ላይ ናቸው። የኮሙኒኬሽን ዋና መሥሪያ ቤቱ በፎቶዎች የታጀበ የሶሪያ ውድመትን እንደ እያሰራጩ ነው። ጥያቄው ግን በአገራችን ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት እንጂ ጦርነት አይደለም። አገሪቱን ሶሪያ የሚያደርጋት አውዳሚ ጦር መሣሪያ የያዘው ሕወሐት እና ወታደሩ ነው። ስለዚህ ማስፈራሪያቸውን «እንደ ሶሪያ እናደርጋችኋለን» በሚል እንወስደው ካልሆነ ሌላ ምንም አንድምታ የለውም። የፖለቲካ ምሁራን የራሳቸውን ትንታኔ መስጠታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በበኩላችን «ቀውሱ በምን መልክ ይጠናቀቃል?» የሚለውን በተለይም ከኦርቶዶክሰ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ለመመልከት እንሞክራለን።

ሑነት  (Scenario ሴናሪዮ) አንድ፡-

ምንም ለውጥ ሳይመጣ «ዘሀሎ»ው (Status Quo) ከቀጠለ

(ማሳሰቢያ – ዘሀሎ የሚለው ስታትስኩዎ/ Status Quo የሚለውን ቃል የሚተረጉም ነው።)

ሑነት አንድ ለረዥም ጊዜ የቀጠለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በመንግሥት አሸናፊነት ቢደመደም የሚለውን መላምት የተከተለ ነው። ይህ ሑነት ድኅረ 1997 ዓ.ም ምርጫ ያለውን ሑነት ይመስላል። እምቢተኝነቱ በሕዝቡ የበላይነት የማይጠናቀቅ ከሆነ ሕወሐት መራሹ መንግሥት ከ1997 በኋላ እንዳደረገው የዚህ ሕዝባዊ እምቢተኝነት መሪ ናቸው ብሎ የጠረጠራቸው ላይ በሙሉ የማያዳግም ርምጃ ይወስዳል። ይህም በተለይ የራሱ የኢሕአዴግ ክንፎች በሆኑት በብአዴን እና በኦሕዴድ የበታች አመራሮች፣ አባላትና ካዴሬዎቹ ላይ የከረረ ይሆናል። ከዚያም አልፎ ለእምቢተኝነቱ መፈጠር ምቹ ሁኔታ ናቸው የሚባሉትን ነገሮች በሙሉ ያጸዳል። ወጣት መሆን እንደ ወንጀል የሚታይበትን ክፉ አመለካከት ያበረታዋል። ወጣቶች የችግሩ ቀዳሚ ተጠቂዎች መሆናቸው ይቀጥላል። የአገዛዙ ቀንበር ከመቼም ጊዜ በላይ የጠነከረ ይሆናል። የአገዛዙ አካሎች የበለጠ በራስ መተማመን፣ ትዕቢትና ማን አለብኝነት ያሳያሉ። ማንም አያሸንፈንም የሚለው የቆየ ዘፈን የበለጠ ይጠነክራል።

አሁን ያለው ዘሀሎ በዚሁ እንዲቀጥል ትልቅ ፍላጎት ያለው የቤተ ክህነት አመራር የተቆጣጠረው አስተዳደር ያለ እንደመሆኑ ጉዳዩ በሕወሐት/ኢሕአዴግ የበላይነት መጠናቀቁ ለቤተ ክህነቱ መሪዎች ትልቅ እፎይታ እንደሚሆን ይታወቃል። ለዚህም በአቅማቸው የለፉበት እና የሠሩበት፤ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ ሽባ በማድረግ የዚህ መንግሥት አገልጋይ ያደረጉ እንደመሆናቸው ሑነት አንድ የልፋታቸው ውጤት ተድርጎ ሊታሰብላቸው ይቻላል።

ይሁን እንጂ ቤተ ክህነቱ ለመንግሥት ባሳየው ጠንካራ ድጋፍ ምክንያት ብዙው ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወቱ ረገድ የሚኖረው ቀቢጸ ተስፋ ወትሮም ከነበረው የባሰ መሆኑ አያጠያይቅም። በካህናት እና በመነኮሳት ላይ እንዲሁም በጳጳሳት ላይ የሚኖረው አሉታዊ አመለካከት የበለጠ ስር ይሰድዳል። በምዕራቡ ዓለም በካቶሊክ ካህናት ላይ አሉታዊ አመለካከቶች በመፈጠራቸው ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ችግር እንደገጠማት ሁሉ በአገራችንም ቤተ ክርስቲያናችን የዚያ ዕጣ ሊወድቅባት ይችላል። ስለዚህም ከእምነት የሚያፈገፍጉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ቢችል የሚደንቅ አይሆንም።

በሌላም በኩል የኢሕአዴግ ማሸነፍ እና የበላይነቱን መጨበጥ በተለይም በካህናቱ አካባቢ ያለውን አድርባይነት እና ለፖለቲካው ተገዢ የመሆን «መለካዊ» ኑፋቄ የበለጠ ያሰፋዋል። ቤተ ክርስቲያን ለጣለችባቸው ሃይማኖታዊ ዓላማ ከመቆም ይልቅ በአድርባይነት እና ተመሳስሎ በመኖር አባዜ የፖለቲካውን ከበሮ በመደለቅ የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የወንጌል ዓላማ የሚዘነጉት ሰዎች ቁጥር አሁን ካለው የበለጠ አሳፋሪ ሆኖ ይቀጥላል። ሙስናው፣ ዓለማዊነቱ፣ አሰረ ክህነትን ያልጠበቁና ምንጫቸው ያልታወቀ መነኮሳት መብዛት፣ ገዳማትና አድባራት እንዲሁም አብነት ት/ቤቶችን መዘንጋቱ የበለጠ እየጨመረ ይሄዳል። ለዚህ መለካዊ ዓላማቸው እንቅፋት ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን ተቋማት፣ አገልጋዮች እና አሠራሮች ወደ ማጥፋት ይሄዳሉ።

ሑነት  (Scenario) ቁጥር ሁለት

ጥገናዊ ለውጥ

ሁለተኛውና ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አንዱ ሑነት መንግሥት «ጥገናዊ ለውጥ በማድረግ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ያቀዘቅዘዋል» የሚለው መላ ምት ነው። ጥገናዊ ለውጥ መሠረታዊ ለውጥ አይደለም። መንግሥት የያዘውን መሠረታዊ ማንነት ሳይለውጥ አንዳንድ ለውጦችን በማድረግ ከምዕራባውያን አጋሮቹ እና ፖለቲካዊ ብስለት ከጎደላቸው ወገኖች ያጣውን መተማመኛ ማግኘት ነው። የኦሮሞን ጥያቄ ለመመለስ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ሰርዣለኹ እንዳለውና ጥቂት የሙስሊም መሪዎችን እንደፈታው ያለ የታይታ ምልክቶችን ማድረግ ነው። ነገር ግን እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ርምጃዎች ከማንም አንጀት ጠብ የማይሉ በመሆናቸው ጥገናዊ ለውጥ ውስጥ ሊገቡ የሚችሉ አይደሉም።

ስለዚህ ፈረንጆቹንም፣ አንዳንድ የሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ተሳታፊዎችን ቀልብ ሊስብ የሚችለው ጋዜጠኞችን እና የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፣ ቢያንስ ከ1997 ዓ.ም በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ሊሆን ይችላል። ይህ ማለት ሕወሐት በኢህአዴግ ውስጥ ያለውን ድርሻ ሳያስነካ፣ በኢኮኖሚው፣ በውትድርናውና በደኅንነቱ እንዲሁም በሌሎች መንግሥታዊ እርከኖች ላይ ያለውን የአንበሳ ድርሻ ሳያስወስድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የጣለውን የብረት መጋረጃ በጥቂቱ ገለጥ ማድረግ፣ የግል ቴሌቪዥንና ሬዲዮኖችን እንዲሁም ጋዜጣና መጽሔቶችን መፍቀድ፣ ኢሕአዴግ ያልሆኑ ሰዎችን በሥልጣን ላይ ማስቀመጥ የመሳሰሉትን ሊያደርግ ይችላል። በሃይማኖቱ በኩልም አሁን በሥልጣን ላይ ያሉትን ፓትርያርክ ማትያስና አጋዦቻቸው የሆኑ የዘሀሎው ተጠቃሚዎችን ሳያነሣ ውጪ አገር በስደት የሚገኙት አባቶች እንዲገቡ፣ በቤተ ክህነቱ ያለው የአንድ ብሔረሰብ የበላይነት በመጠኑ ጋብ እንዲል የጥገና ለውጥ ሊያደርግባቸው ይችላል።

ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ በሽምግልና ስም «አንተም ተው አንተም» በሚል የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መንግሥት የተቀሰቀሰበትን እምቢተኝነት ሊያረግቡ የሚችሉ የተለያዩ አካላትን ሚና ሊቀበል ይችላል። ተሸምግሎ ለሌሎች ሐሳብ እንደተገዛ በማስመሰል የጥገናውን ለውጥ ሊያካሒድ ይችላል። የአሸማጋይነቱን ሚና የሚጫወቱት ሰዎች በቅን ኢትዮጵያዊ መንፈስ የሚንቀሳቀሱ ያሉበትን ያህል ልባዊ ድጋፍ ለሚሰጡት የሕወሐት/ኢሕአዴግ ቡድን በምንም በምን ብለው የሕዝቡን ቁጣ በማብረድ ነገ ነጣጥሎ ለሚመታቸው አካል የሚያመቻቹም አሉበት።

በርግጥ ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች የታየ እንደመሆኑ ሽምግልና እና ሕወሐት አብረው ይሄዳሉ ተብሎ አይጠበቅም። በሽምግልና የሚመጣ ጥገናዊ ለውጥ ከፍ ብለን በቁጥር አንድ ካየነው ሑነት ብዙም የተለየ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። የቀለም ቅብ የመሠረት ችግር ያለበትን ቤት ከመፍረስ አይታደገውም፤ ምስጥ የበላውን ምሶሶ ቀለሙን በመቀያየር ለውድቀት ማትረፍ አይቻልም። በጥገናዊ ለውጥ የሚታለሉ ሰዎች በጥቂት ነገር የሚደለሉና ከመጀመሪያውም የነገሮችን ጥልቀት ያልተረዱ ብቻ ናቸው።

ሑነት  (Scenario) ቁጥር ሦስት

ሥር ነቀል ለውጥ

ነገሮችን በጥሙና ስንመረምራቸው አሁን የተያዘው ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ዝግመታዊ ለውጥ አንድ ነገር ሥር ነቀል ለውጥ እየመጣ መሆኑን በቅጡ ያመለክታል። ይህ ሥር ነቀል ለውጥ ፍፁማዊ የመንግሥት ለውጥን ሊያመጣ የሚችል ርምጃ ነው። መንግሥት የፈቀደውን ያህል መሣሪያ የታጠቀ ቢሆን፣ የፈቀደውን ያህል አሰቃቂ እመቃ እና አፈና በማድረጉ ቢገፋም፣ አንዱን ብሔረሰብ ከአንዱ ማጋጨቱ ምንም ያህል በመንግሥት ደረጃ ቢናፈስም ይህ የኅዳጣን (የጥቂቶች) መንግሥት መውደቁ አይቀርም። ምናልባት መቅረብ ያለበት ጥያቄ «መቼ?» የሚለው ነው።

ሥር ነቀል ለውጡ ይዞት የሚመጣቸው በጎ ውጤቶች እንዳለው ሁሉ ላለፉት 25 ዓመታት በተፈፀሙ አፍራሽ ተግባራት ምክንያት አገሪቱን የሚያስከፍላት ዋጋም መኖሩ ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ሕወሐት የተደራጀ ኃይል እንደመሆኑ በአንድ ጊዜ ብን ብሎ ሊፈርስ የሚችል አይደለም። ነገር ግን መንግሥታዊ ሥልጣንን ተቆናጥጦ ለመቆየት ሕዝቡ አልገዛም ከማለቱ የተነሣ «ቤዝ« ወደሚለው የትግራይ ግዛት ሊያፈገፍግ ይችላል። ብዙዎቹ መሪዎቹና ደጋፊዎቹም ንብረታቸውን ወደማሸሽ፣ አገር ጥለው ወደመሸሽ ሊገቡ ይችላሉ። የዚያ ምልክቶች መታየት ከጀመሩ መቆየታቸውን ልብ ይሏል።

ሕወሐት ወደ ቤዙ ማፈግፈግን ከመረጠ (ደርግ ትግራይንና ኤርትራን ለቅቆ ሲወጣ እንዳደረገው) በሰላም፣ ያለምንም ውድመት ይወጣል ብሎ መገመት የዋህነት ይሆናል። ከዚህ ቀደም በመሐል አዲስ አበባ ሳይቀር ፍንዳታዎችን በማቀነባበር «አሸባሪዎች ፈጸሙት» እንዳለውና ከጥቂት ሳምንታት በፊትም በመተማ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን የዘር ፍጅት እንደደረሰባቸው በማስመሰል በደኅንነቱ በኩል እንዳሰደዳቸው ሁሉ (http://wazemaradio.com/?p=2853)፣ አሁንም በትግራይ ሕዝብ ንብረቶች እና ሕይወት ላይ እንዲሁም በተቀረው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ንብረቶች ላይ ውድመት ሊቃጣ ይችላል የሚል ስጋት አለ። «ባልበላው ጭሬ ላፍሰው» የሚለው ተረት በተግባር ሲውል ስላየን ይህንን አለመጠበቅ የዋሕነት ይሆናል። ጥያቄው ለዚያ ጊዜ ያለን ዝግጅት ምንድነው የሚለው ብቻ ነው።

የሕወሐት የብረት አገዛዝ መላላት ብቻ ሳይሆን መሰባበር ሲጀምር ይኸው ቀውስ የንጹሐን ወገኖችን ሕይወት የሚያበላሽ እንዳይሆን በተለይም ቤተ ክርስቲያን እና ቤተ ክርስቲያንን የመሳሰሉ ተቋማት ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። ሕወሐት በደህና ጊዜ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማሽመድመዱ ምክንያት እና ማኅበረሰባዊ ሰንሰለቱ ባይበጠስም እንዲቀጥን በማድረጉ ለዚህ ዓይነቱ ክፉ ጊዜ ይጠቅም የነበረውን ማኅበራዊ ካፒታል አባክኖታል። ስለዚህም ለችግር ጊዜ መድረስ ይገባት የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ያንን ሰማያዊ ኃላፊነቷን ልትወጣ የምትችልበትን አቅም አድክሞታል። መሪዎቿ በመለካዊነት የተጠመቁ በመሆናቸው ምክንያት የአስታራቂነትን እና የአረጋጊነትን ሚና ሊጫወቱ የሚችሉበት ዕድል በእጅጉ ተመናምኗል። በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት የተጎዳ በመሆኑ ቃላቸውን ሊሰማ የሚችል ሰው ማግኘት ከባድ ይሆናል። ከሕዝብ ጋር አብሮ ችግርን መካፈል፣ ስቃዩን መሰቃየት፣ ኃዘኑን ኃዘን ማድረግ የሚጠቅመው ለዚህ ዓይነቱ ክፉ ጊዜ ነበር።

ሕወሐት ሥልጣኑን ሲለቅ አሜሪካዊው ፓትርያርካችን ዜግነት ወደተቀበሉበት አገር መመለሳቸው የማይቀር ነው። እሳቸውም በተራቸው የስደት ሲኖዶስ፣ የስደት አስተዳደር፣ የስደት ካህናት ወዘተ ወዘተ ይዘው ይቀጥላሉ። በስደት አገር በሕዝቡ ላብ የተቋቋሙት አብያተ ክርስቲያናት ሰላም እና አገልግሎት በዚህ አይታወክም ብሎ መገመት የዋሕነት ነው። የዘመናችን ክፉ ፖለቲካ በአስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በአገር ልጅነት፣ በብሔረሰብ እና በቋንቋ ላይ የቆመ እንደመሆኑ የአብያተ ክርስቲያናቱም አሰላለፍ ያንን መከተሉ የሚጠበቅ ነው። ከዚህ በፊት የተሞከረ እንጂ አዲስ ነገርም አይደለም። እውነታውን ላለመመልከት ዓይናችንን ካልጨፈንን በስተቀር።

አገሪቱ መሠረታዊ ለውጥ ስታደርግ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርም ሥር ነቀል ለውጥ ይጠብቀዋል። ፓትርያርክ ማትያስና አጋሮቻቸው ስደትን መረጡም አልመረጡም በስደት ላይ የነበሩት አባቶች በፈንታቸው በኅብረትም ይሁን በየግላቸው ወደ አገራቸው መግባታቸው የሚጠበቅ ነው። ከ25 ዓመታት በላይ ከቤተ ክህነቱ አስተዳደር ተለይተው እንደመቆየታቸው የተሰደዱት ሲመለሱ በአገር ውስጥ ካለው ጋር ያለ ምንም ችግር ተዋሕደው አገልግሎታቸውን እንዲፈጽሙ ምን ሊደረግ ይገባል? በዚህ 25 ዓመት በቤተ ክርስቲያን ላይ ወንጀል የፈፀሙ፣ ንብረቷን የዘረፉ ሰዎች አሉ። አስተዳደራዊ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወንጀሎች ተፈጽመዋል። የነበረው እንዳልነበር ሆኗል። ሥር ነቀሉ ለውጥ የበለጠ መተረማመስና ዝርፊያ የነገሠበት እንዳይሆን ዝግጅት እስካልተደረገ ድረስ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ ለሚሉ ወንጀለኞች በር መከፈቱ አይቀርም።

እንግዲህ ዞሮ ዞሮ ጥያቄው ለቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ለሊቃውንቱ፣ ለምእመናኑ እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ ነው። አገራችን ላይ እየመጣ ያለውን ሑነት አስመልክቶ ምን ያህል ተዘጋጅተናል? የዳር ተመልካቾች ሆነን እንቅር ወይንስ በአገራችን ጉዳይ ወሳኝ ሚና እንጫወት? ጥቂት ግለሰቦች ከደም አፍሳሹ መንግሥት ጋር ወግነው በሚፈጽሙት በደል የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በሙሉ በዚህ ጥቁር ነጥብ ይበላሽ ወይንስ ይህንን የሚክስ ተግባር እንፈጽም? እዚህም እዚያም በግላችን እንጩህ ወይንስ በቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ለአገራችን በአንድነት ድምጻችንን እናሰማ? ታሪካዊው ጥያቄ ቀርቦልናል። መልሳችን ይጠበቃል። ይቆየን

መረጃና ጥቅሙ

Achamyeleh Tamiru

የወያኔ ድርጅታዊና ስርዓታዊ ሞዴል ቁሳቁሳዊ ግብዓቶችን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ጉልበት ማግኘት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ ሞዴል እስከ ዛሬ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በነበሩት ስልጣኔዎች ሁሉ የሰራሞዴል ነው። የሞዴሉ ጽንስ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው። ቁሳቁሱን የተቆጣጠረ አካል ሁኔታዎች ወዴት እንደሚያመሩ መቆጣጠር ይችላል የሚል መነሻን ያደርጋል። የቁጥጥሩ ስርዓት የሚከናወነው ደግሞ የመረጃ ስርጭትን በመቆጣጠር ሲሆን ይህንን ለማድረግ በቁጥጥር ስር ያለውን አካላዊ መሳሪያ ሁሉ ይጠቀማል። ይህ የተለመደ ሁኔታ ነው።

ዛሬ ላይ ግን መሳሪያ ብቻ ይረዳል ማለት ዘመኑን የዋጀ አስተሳሰብ አይደለም። ምንም እንኳን ይቺን የአሁኗን ቅጽበት የሚቆጣጠረው ብረቱን የያዘው አካል ቢሆንም የምትቀጥለውን ደቂቃ ወይም ሰዓት ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ግን መረጃውን የሚቆጣጠረው አካል ነው።

እስከ አለፉት ሁለትና ሶስት አስርት ዓመታት ድረስ መሳሪያውን የያዘው የሚተላለፈውን መረጃ ይወስን ነበር። ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። ዛሬ መረጃን መቆጣጠር ማለት ተደማጭነት መኖር ማለት ነው። መረጃ ካለህ ሰው ሊሰማህ ይፈልጋል። መረጃ ከሌለህ የለህም። መረጃ ከሌለህ ማንም ሊሰማህ አይፈልግህም። ማንም ሊሰማህ ካልፈለገ ምንም መስራት አትችልም። ይህ ማለት እንግዲህ የአድማጭ መልካም ፈቃድ የሚገኘው በመረጃ ነው ማለት ነው። አንድ ሰው ሌላውን ለማዳመጥ መልካም ፈቃድ ከሌለው በመሳሪያ አስገድደህ ሙሉ ቀን ስብሰባ ላይ ብታውለው፤ ሙሉ ቀን በሬዲዮና በቴሎቭዥን ብትለፈልፍ ምንም የምታመጣው ለውጥ የለም። በርግጥ ሰውን ያለፍላጎቱ አግተህ ፖለቲካ በመጥመቅ ጊዜያዊ ግንዛቤ መፍጠር ይቻል ይሆናል። ይህ በሚሊዮን ብር የተገነባው ግንዛቤ ግን በአንድ የፌስቡክ መልዕክት ሊፈርስ ይቻላል።

ይህ እንዲሆን ትክክለኛ መረጃ ያስፈልጋል። ትክክለኛ መረጃ መሰብሰብ ከሁሉ አስቀድሞ ለራስ አስፈላጊ ነው። እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ ራሱን ነጻ ለማውጣት የሚያስችል ፍላጎትና አቅም አለው። ሆኖም የያንዳንዱ ሰው ፍላጎትና አቅም ብቻውን ነጻነት አያመጣም። ፍላጎትና አቅም በመረጃ ታጅለው ጣምራ መሆን አለባቸው።

መረጃ ሲጠራቀምና ጣምራ ሲሆን አቅምና ፍላጎትን አቀጣጥሎ ወደተፈለገበት የሚያደርስ ነዳጅ ነው። ትክክለኛ መረጃ ወደነጻነት ሲያደርስ የተሳሳተ መረጃ ነጻነትን ያስነጥቃል። አንድ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው ለቤተሰቡ፣ ለጎረቤቱ፣ ለማኅበረሰቡ፣ ለሃገሩ ሊያደርግ የሚችለው አነስተኛው ነገር፣ ያለውን ትክክለኛ መረጃ ለሁሉም ማካፈል ወይንም ለሁሉ ወደሚደርስበት የመረጃ ቋት መላክ ነው። በየትኛውም መንገድ መረጃ ያገኘ ሰው ለነጻነቱ የሚችለውን እንዲያደርግ የሰው ተፈጥሮ ያስገድደዋል። ባጭሩ በባርነት እየኖርን ያለነው ሁላችንም ተባብረን የጋራ የመረጃ ቋት ባለመፍጠራችን ወይንም ያወቅነውን ትክክለኛ ነገር ለሁሉም ባለማሳወቃችን ነው።

ያየውንና የሚያውቀውን ትክክለኛ መረጃ የሚደብቅ ሰው ሃላፊነት የማይሰማው ሰው ነው። እውነቱን የሚደብቅ ሰው ለሰው ጥሩ የሚያስብ ሰው አይደለም። አውቆም ሆነ ሳያውቅ የውሽት መረጃ የሚያጋራ ሰው ደግሞ የሰውን ጥፋት የሚሻ ተልኮለኛ ሰው ነው። የግራ ፖለቲካ ወደ አገራችን ከገባ ወዲህ እኛ አገር አንዱ ትልቁ ችግር የተንኮለኛና ሴረኛ ሰዎች መብዛት ነው። ያ ደዌ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ የዛሬው ትውልድ በሽታም ሆኗል። ካለፉት አርባ አመታት ወዲህ ባዳበርነው የፖለቲካ ባህል መረጃን መደበቅ ወይም ስህተት የሆነን መረጃ ማስተላለፍ እንደባህል ሆኗል። ለዚያም ነው የግራ ፖለቲካ ባህል ወደ አገራችን ከገባ ጀምሮ አለመተማመን ባህላችን የሆነው። ይሄ የፖለቲካ ባህል እውነት ቢነገርም በጥርጣሬ ለማየት እንድንገደድ አድርጎናል። በዚህም የተነሳ ዛሬ ችግራን ብዙ ሆኗል።

በሶማሌና በአፋር ባህል ውስጥ ግን የሚደነቅ የመረጃ ልውውጥ ባህል አለ። ለሶማሌና ለአፋር መረጃ የነፍስ ያህል ነው። እንደሚታወቀው የዘላን ህይወት ዛሬ እዚህ ነገ እዚያ ነው። ዘላን ከአንዱ ቦታ ተነስቶ ወደሌላው ቤተሰቡን፣ ከብቱንና ባጠቃላይ በዚህች አለም ላይ ያለውን ሁሉ ይዞ በረሃውን አቋርጦ ሲሄድ ስለሚያጋጥመው ነገር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። በመዳረሻ ቦታው ውሃው ደርቆ ከሆነ ሁለት ቀን ተጉዞ እዚያ ሲደርስ ጉድ ሊሆን ይችላል። ቤተሰቡ ሊያልቅበት ይችላል። በዚያ መንገድ ላይ ሽፍቶች ወይም ተቀናቃኝ ጎሳዎች ካሉ ካላወቀው ከነቤተሰቡ ያልቃል። ስለዚህ ምንም ሌላ የመገናኛ መሳሪያ በሌለበት አንድ አፋር ወይም ሶማሌ በአካባቢው ስላለው ሁኔታ በየቀኑ በትክክል ማወቅ አለበት። የተሳሳተ መረጃ ካለው አለቀለት። የዚህ ችግር መፍትሄ በነዚህ ጎሳዎች ባሕል ውስጥ አለ። ይኸውም መረጃን በትክክል ለጎሳቸው አባል ለሆነ ሰው በትክክል ማስተላለፍ ነው።

ሁለት አፋሮች መንገድ ላይ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ሲሄዱ ከተገናኙ ይቆሙና፣ ዱላቸውን መሬት ላይ ተክለው ተደግፈው መረጃ ይለዋወጣሉ። የመረጃ ልውውጡ ስርዓት አለው። አንዱ ሲናገር ሌላኛው እህ! እህ! እህ! እህ! እያለ ከማዳምጥ በስተቀር አያቋርጠውም። መንገድ ላይ ያለውን አደጋ፣ የማን ቤተሰብ የት ጋ እንዳለ፣ የትኛው የውሃ ምንጭ እንደደረቀ፣ ሌላም ሌላም ነገር ይነግረዋል። ተራው ሲደርስ ያኛውም እንደዚያው ያደርጋል። ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ከሰጠ በሰውዬውና ቤተሰቡ ህይወት ላይ ፈረደ ማለት ነው። ስለዚህ በዛ እልም ያለ በረሃ ውስጥ እያንዳንዱ አፋር የሚሆነውን፣ የሚያጋጥመውን፣ የቱ ጋ ምን እንዳለ በደምብ ያውቃል ማለት ነው።

ይህንን ፈረንጆቹ situational awareness ይሉታል። አሁን አሁን ግን ከባድ የነበረውን የአፋሮና የሶማሌዎች ህይወት ሞባይል ስልክ የበለጠ አቃሎታል።
ትግራይ በነበርሁ ጊዜ «ዞን ሁለት» በሚባለው የአፋሮች አካባቢ ለመስክ ጥናት ሄጀ አርባ ግመል የሚጎትት የአብር አባወራ አርባውን ግመል ሰትሮ በሞባይል ስልኩ ሌላ ቦታ ላለው የጎሳው አባል መረጃ ሲያቀብልና situational awareness ሲሰጥ በአይኔ አይቻለሁ። ይህንን ለመገንዘብ የቻልሁት አፋርኛ የሚችለው ትግሬው ሾፌራችን አርባውን ግመል ሰትሮ ለረጅም ጊዜ በሞባይሉ ያወራ የነበረው አፋር ምን እያወራ እንደሆነ ጠይቄው ሌላ ቦታ ላለው የጎሳው አባል መረጃ እየሰጠ እንደሆነ ተርግሞ ነግሮኝ ነው። ሾፌራችን አጠገባችን የቆመው አፋር ወዲያ ማዶ ላለው የጎሳው አባል… በዚያ አትሂድ፣ በዚህ አቋርጥ፣ እዚያ ብትሄድ ይህ ይገጥምሀል፣ በዚህ ብትሄድ ይህንን ታገኛለህ፣ ወዘተ እንደሚለው ተርጉሞልኛል።

እስካሁን ወያኔ በህዝባችን ላይ ተነግሮ የማያልቅ ሰቆቃ ሲታደርስ ለምንድነው የረባ ራስን ነጻ የማውጣት የተባበረ እንቅስቃሴ ያልተደረገው ለሚለው መልሱ እዛ ጋ ያለ ይመስለኛል። ዘላኖቹ አፋሮችና ሶማሎዎች እንዳላቸው አይነት ትክክለኛ የሆነ የዳበረ የጋራ የሁኔታዎች ምልከታ (situational awareness) የለንም። ካለንም የተሳሳተ፣ የተዛባ ነው። ከፍ ብዬ እንዳልሁት እውነት ቢሆንም አናምነውም፤ እንጠራጠራለን። የምንጠራጠረውን ከማረጋገጥ ይልቅ ይዘነው እንቀራለን። የማረጋገጥ ፍላጎቱ ካለ ግን ለማንጠር [refine ለማድረግ] ቀላል ነው። ቀላሉ ዘዴ ማመሳከር ነው፤ ከሌላው ጋር መለዋወጥ ነው። ሁሉም ሰው «ይህ በዛ ያ አነሰ» ሳይል ያለውን መረጃ ጠረጴዛው ላይ [ፌስቡኩ ላይ ማለቴ ነው] [ስጋት ያለበት ካለ ደግሞ በውስጥ መገናኛ መስመር ለሚያምነው ሰው ሊልክ ይችላል] ከዘረገፈው የዚህ ሁሉ ሰው አይን እውነቱን ከውሸቱ ለይቶ ያወጣል። ማመሳከር ማለት ያ ነው። አፋር ውስጥ የሰውን ስም ማጥፋት ከባድ ነው። ሲስተሙ እያመሳከረ እውነቱን ያወጣዋል። ለነፍስህ ስትል ሁሉንም ስለምታዳምጥ እውነቱ ወዲያው ይወጣል። ውሸታሙ ወዲያው ይጋለጣል። ውሸቱ ሲጋለጥ ህይወት ሊጠፋውም ይችላል።

በኛ አካባቢ እንደ አፋርና ሶማሌዎች እውነቱን እያመሳከረ የሚያወጣ ሲስተም ስለሌለ ሰው ጥይት መተኮስ አያስፈልገንም። አንዱን የማንፈልገውን ሰው ልናጠፋው ከፈክለግን ያልሆነ ወሬ አንስተን «ቱስ» ብንል የፈለገ ትልቅ ሰው፤ ደግ ፍጡር ቢሆን ደብዛውን ልናጠፋው እንችላለህ። ይህም የሚሆነው ውሸት ብናወራ ስለሚወራው ነገር ስለማናመሳክር ነው። እውነት በቀላል ይገኝ ይመስል ውሸት በቶሎ እንቀበልና ስለእውነት የሚገባውን ክብደት አንሰጥም።

ያለንበትን ጊዜ መጠቀም ከቻልን ይህንን ሁሉ ችግር ማስወገድ የምንችልበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የዘመኑ ቴክኖሎጂው ነገሮችን አቅሏቸዋል። ከኛ የሚጠበቀው ያለውን ሁሉ መረጃ በትክክል ማቅረብ ነው። ቴክኖሎጂውና የሰው ልጅ የእውቀት ደረጃ አንድን መረጃ እውነት እንኳ ባይሆን በቀላሉ ያጣራዋል። ቴክኖሎጂው የቀረበለትን መረጃ በተቻለ መጠን ማዛመድ፣ ማጣራት፣ ማመሳከር ይችላል።

ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂና እውቀት ከሌለን ግን የአፋሮችንና የሶማሌዎችን የመረጃ ልውውጥ ዘዴ ብንከተል ብዙውን ችግራችንን ማቃለል እንችላለን። ስለዚህ እንደ አፋሮች የሰማኸውን ነገር ሁሉ ሰማሁ ብለህ አቅርብ፤ ያየከውንም አጋራ። የሰማኸውን አየሁ ካልህ፤ ያላየኸውን አይቻለሁ ካልክ መረጃውን በከልከው ማለው ነው። የተበከለ መረጃ ሰው ርግጠኛ ሳይሆን እንዲፈርድ ያደርገዋል።

በሰለጠኑት ፈረጅኖች ዘንድ ዛሬ የአንድን መረጃ ትክክል መሆን አለመሆን በሂሳብ ቀመር የሚፈትን ነጻ የኮምፒዩትር ፕሮግራም አለ። ይህ ምናልባትም ላይመስል ይችላል። በርግጥ ይህ ፕሮግራም የሁሉን ተሳትፎ ይጠይቃል። ፕሮግራሙ swiftriver ይባላል። እውነቱን ከውሸቱ አበጥሮ ያወጣል።

ፕሮግራሙ ስለራሱ እንዲህ ይላል… «SwiftRiver is a platform that helps people make sense of large amounts of information in a short amount of time. It’s also a mission to democratize access to the tools used to make sense of data – to discover information that is authentic.»

አንድ አይነት ራዕይ ያለን ሰዎች የራሳችን swiftriver መፍጠር እንችላለን። ታዲያ የኛው swiftriver የኮምፒዩተር ፕሮግራም አይደለም፤ መረጃ የምንልክለት የኛ የሆነ ሁነኛ ሰው እንጂ። ይህ የኛ swiftriver የመረጃ ማእከል ይሆንና አጠቃላይ የመረጃ ፍሰቱን ይቆጣጠራል። ይህ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት የመረጃ ፍሰቱን የሚቆጣጠረው ይህን አካል ካወቅን ወይንም ያን አካል እኛ ከፈጠርነው ወደፊት በማን ራዕይ እንደምንመራ ማወቅ እንችላለን ማለት ነው።

ስለዚህ በተለይ አገር ቤት ያላችሁ የመረጃ ትንሽ የለውምና በእጃችሁ ያለውን ስልክ ሳይቀር በመጠቀም መረጃ ሰብስቡ። የሰበሰባችሁትን መረጃ ደግሞ የኛ swiftriver ነው ብላችሁ ለምታስቡት ሰው ላኩ። ይህ ሰው የላካችሁትን መረጃ አደራጅቶ ፤ ትርጉም ሰጥቶ፤ሁኔታ አበጅቶ፤ መልክ አስቀምጦና ተንትኖ የዳበረ የጋራ የሁኔታዎች ምልከታ ይፈጠራል። ይህ የነጻነታችን ሞተር ነዳጅ ነው። ያየነውን፤ ያወቅነውን ወደ አንድ swiftriver የሆነ ሰው በመላክ ያለብንን ሃላፊነት በመወጣታችን ነጻ እንወጣለን።

ሁላችንም በኃላፊነት ስሜት ያለንን፣ ያየነውን፤ ያወቅነውን ሁሉ ወደ መረጃ ቋታችን ማለትም ወደኛው swiftriver መላክ ከቻልን በቀላሉ መጻኢ እድላችንን መቅረጽ እንችላለን፤ መረጃ ፍሰቱን የሚቆጣጠረው አካል የወደፊቱን ሁሉ ይቆጣጠራልና!

አክባሪያችሁ!

አቻምየለህ ነኝ!

‘Medical torture’ being reported out of prison camps in Ethiopia

By Ass’n of Amhara Physicians

Image result for 'Medical torture' being reported out of prison camps in Ethiopia

There are reports of medical torture in NAZI TPLF concentration camps to Amhara people. Birsheleko Victims are reportedly being enforced to take drugs without any professional medical expertise for corporal punishment.

Please those Amhara physicians, pharmacists, health officers ,nurses and related professionals working especially in Finoteselam , Motta, Burea,Enjibara hospitals and health centers be informed that any person in amhara region with fainting ,collapse, dizziness, bizzariness, death or others brought to these centers with accompany TPLF assistants is highly suspicious victim of medical torture with out medical expertise.
This fundamentally violates medical ethics of Hippocratic Oath and international laws.

We all amhara physicians are expected to adhere to laws and stand against deliberate and explicit harm. Nazi TPLF cadres without ability are prescribing and giving drugs for ‘bad will’ to deliberately harm amhara people, a criminal act against humanity in its concentration camps. The Declarations of Geneva, Tokyo and World Medical Association Medical Ethics require us to have utmost respect for human life even under threat. As of World Medical Association Declaration of Tokyo and UN Principles of Medical Ethics, Health Personnel, particularly Physicians, should stand for Protection of Prisoners and Detainees.

The doctor shall not countenance , condone or participate in the practice of torture in whatsoever circumstances.

We amhara physicians strongly ask if any Cadre medical professionals in Camps are using their medical knowledge contrary to the laws of humanity.

We Amhara physicians are profesionaly responsible for knowing torture drugs more likely TPLF sponsored which might have lots of short or long term bad effects on the victims, their families, communities, future generation genetic alterations and Amhara people in general.

We are currently not sure whether Federal Drug Control Authority of Ethiopia has a regulation relating to medical torture in Ethiopia.

We are highly requesting all to:

1. evaluate all victims and even deaths for any drug use
2. identify brand or generic name, manufacturing country or company of drug
3. examine drug’s biochemistry
4. identify individuals/ professionals involving in the situation
5. know ways how such drugs are imported to our country
6. inform means for use of such community and generation risky drugs with out approval of Federal Drug Authority

 

የኦነግ ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መግሇጫ-በኣማራ ክሌሌ (ጎንድር፣ ጎጃምና ወሌቃይት) ኣካባቢ ያለዉን አንቅስቃሴ በተመለከተ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ቋሚ ስብሰባውን ከመስከረም 1 እስከ 11 ቀን 2016ዓም በማካሄዴ የዴርጅቱ የስራ ዗ርፎች ሪፖርት በማዲመጥ እንዱሁም፡ የኦሮሞ ህዝብ ነጻነትና የኦሮሚያ ለዓሊዊነትን ሇማረጋገጥ እየተካሄዯ ስሊሇው ትግሌ ሁኔታ፣ ስሇፋሽስቱ ወያኔ መንግስት፣ የጸረ-ፋሽስቱን ወያኔ እንቅስቃሴዎች፥ በኣማራ ክሌሌ(ጎንዯር፣ ጎጃምና ወሌቃይት) ውስጥ እየተካሄዯ ስሊሇው የህዝብ ኣመጽ፣ ስሇኮንሶና መዠንግር፣ ስሇጋምቤሊ፣ ሲዲማ፣ ቤኒሻንጉሌ፣ ኦጋዳን፣ ስሇኣፍሪካ ቀንዴና ስሇኣፍሪካ ኣህጉር እንዱሁም ስሇኣሇም ሁኔታ በቀጥታ ዯግሞ ከኦሮሞ ህዝብ ነጻነትና የኦሮሚያ ለዓሊዊነት ጋር ተያይዞ የኦሮሞን የዱፕልማሲ እንቅስቃሴ ኣስመሌክቶ በጥሌቀት በመገምገም ከዚህ በታች ያለትን ወሳኔዎች በማሳሇፍ ስብሰባውን በስኬት ኣጠናቋሌ።

ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ

የኢትዮጵያ ኢምፓዬር ከተፈጠረችበት ጊዜ ኣንስቶ እስከ ዛሬ ዴረስ የኦሮሞ ህዝብ በጅምሊ መገዯሌ(የ዗ር-ማጥፋት)፣ ማንነቱን መነፈግ፣ መታሰር፣ መሰቃየት፣ መ዗ረፍና ከሃገሩ በሃይሌ ከመባረር በተረፈ በሃይሌ በተመሰረተችው የኢምፓየርነት ኣገዛዝ ውስጥ ያገኘው ይህ ነው የሚባሌ ኣንዲችም ፋይዲ የሇም። ይህንን የጨሇመ የታሪክ ጉዞ ሇመቀየር በሚሉዮኖች የሚቆጠሩ ውዴ የኦሮሞ ሌጆች ሇዚህ ጀግና ህዝብ ነጻነትና ለዓሊዊነት መተኪያ የላሊትን ህይወታቸውን ኣሳሌፈው ሰጥተዋሌ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይህንን የጀግንነት ታሪክ በወረሱ የኦሮሞ ሌጆች የተመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ከኣንዴ ምዕተ-ዓመት ተኩሌ በሊይ ሇሚሆን ጊዜ እየከፈሇ ሊሇው ከባዴ መስዋዕትነት ፍሬ ሇማስገኘት ነው። ኦነግ ባካሄዯው ከባዴ መስዋዕትነት ያስከፈሇ መራር ትግሌ ዛሬ የኦነግ የፖሇቲካ ፕሮግራም በኦሮሞ ህዝብ ዴጋፍ ተቀባይነቱ እየጎሊ መጥቶ በኢትዮጵያ ኢምፓዬር ውስጥ ሊሇው የፖሇቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ችግሮችና የባህሌ ጭቆና እንዱሁም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዗ሊቂ መፍትሄ ሇማስገኘት እየተቃረበ ይገኛሌ። ይህንን ሇማዴረግም የኦሮሞ ህዝብ ከሰሜን እስከ ዯቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብና ከማዕከሊዊ ኦሮሚያ ውስጥ በኣንዴ ዴምጽና የፖሇቲካ ኣመሇካከት ፋሽስታዊነቱ ካሁን በፊት ታይቶ የማይታወቀውን ጠሊት ተጋፍጦ የጸረ-ጭቆና ኣመጽን ወዯ የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ ትግሌ ኣሸጋግሮታሌ። ይህም ፍርሃትን በማሸነፍ ከኣባቶቹ በወረሰው ጀግንነት ጠሊትን በመጋፈጡ ትግለን ከመከሊከሌ ወዯ ማጥቃት ኣሸጋግሯሌ። ኦነግ ባስቀመጠው እቅዴና ፕሮግራም ሊይ በመመርኮዝ የኦሮሞ ህዝብ ባድ እጆቹን ሇ11 ወራት በቀጣይነት እያፋፋመ ባሇው የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ ያሳየውን ጀግንነትና ኣንዴነት ያዯንቃሌ። በዚህ ኣመጽ የኦሮሞን ህዝብ ነጻነትና የኦሮሚያን ለዓሊዊነት ሇማረጋገጥ፣ የኢምፓዬሪቷ ጠባቂ የሆነውን የወያኔ ፋሽስት መንግስትንና በኢምፓዬሪቷ ሊይ የተመሰረተውን ስርዓት ከመሰረቱ መንቀሌ እጅግ ወሳኝ ነው። ይህም ነጻነቱን ባረጋገጠ ህዝብ፣ ነጻና ገሇሌተኛ በሆነ ህዝበ-ውሳኔ(ሬፈረንዯም) ሊይ የኦሮሞን ህዝብ የራስን እዴሌ በራስ የመወሰን መብቱን በማረጋገጥ እውን ይሆናሌ። ስሇሆነም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ከዚህ ውጪ ላሊ መፍትሄ እንዯላሇ ተገንዝቦና ተግባብቶ ይህን የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ በትጥቅና ትጥቅ ኣሌባ የትግሌ ስሌቶች በመጠቀም ይበሌጥ እንዱፋፋም ኣስቸኳይ ጥሪ ያቀርባሌ። ይህ ፋሽስቱ የወያኔ መንግስት ወዴቆ የኦሮሞ ህዝብ መብት እንዱረጋገጥ እስካሁን የሰጠውን ኣመራር በይበሌጥ ኣጠናክሮ እንዯሚቀጥሌ ኦነግ በዴጋሚ ቃለን ያዴሳሌ።

ሇመሊው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ የኦነግ ኣመራሮች፣ ኣባሊትና ዯጋፊዎች

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኣባሊት፣ የኦነግ ኣመራሮች፣ ኣባሊትና ዯጋፊዎች ሇኦሮሞ ህዝብና ሇኦሮሚያ ለዓሊዊነት እየተካሄዯ ባሇው ትግሌ ውስጥ ግንባር-ቀዯም በመሆን እጅግ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ውዴ መስዋዕትነት እየከፈለ ዛሬን መዴረሳቸው የሚታወቅ ነው። ትግለ ዛሬ የዯረሰበት ዯረጃና ህዝባችን ያሇበት ሁኔታ በቆራጥነትና በቁርጠኝነት ትግለ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁለ በመክፈሌ ትግለን ከግቡ ሇማዴረስና የኦሮሞ ህዝብን የፖሇቲካ ስሌጣን ባሇቤትነት ሇማረጋገጥ ባያሇንበት ፋሽስቱን የወያኔ መንግስት በማጥቃት ሊይ እንዱሰማራ መሌዕክታችንን እናስተሊሌፋሇን።

ፋሽስቱን የወያኔ መንግስትና የስርዓቱን ተሊሊኪዎች በተመሇከተ

ፋሽስቱ የወያኔ መንግስትና የወያኔ ተሊሊኪዎች የሆኑት በፌዳራሌ ዯረጃና በኦሮሚያ ክሌሌ ሊይ ያለት የኦፒዱኦ ኣመራር ኣባሊት ኣብዛኛዎቹ ኣፋን ኦሮሞን የፊንፌኔ የስራ ቋንቋ ማዴረግ፣ ከፊንፊኔ ኣካባቢ በሃይሌ ሇተፈናቀለ የኦሮሞ ዜጎች ቤት በመስጠት እንዱሁም መሰሌ እርምጃዎችን በማወጅ በትናንሽ የማስመሰያ ሇውጦች ህዝቡን በማስገዯዴ ሇስርዓቱ ዴጋፍ እንዱወጣ ሇማዴረግ ኣቅዯዋሌ። ይህ ሇኦሮሞ ህዝብ ነጻነትና ሇኦሮሚያ የለዓሊዊነት ጥያቄ ፈጽሞ ምሊሽ ሉሆን የማይችሌ፡ የኦሮሞን ህዝብ ኣዯናግረው የጭቆና ፍጻሜ ኣመጹን በማኮሊሸት ጨቋኙን የወያኔ ስርዓት በኦሮሞ ህዝብ ጫንቃ ሊይ ሇማሰንበትና ሇስርዓቱ ያሊቸውን ታማኝነት ሇማረጋገጥ የወጠኑት ጠሊትዊ ሴራ መሆኑን እናስገነዝባሇን። ኦነግ በህዝባቸው ሊይ የሚፈጸመው የ዗ር-ማጥፋት ወንጀሌ ተሰምቷቸው ወገናቸው እንዲይጎዲ ሲሰሩ የነበሩና ኣሁንም በመስራት ሊይ ያለትን የኦፒዱኦ ኣባሊት ያዯንቃሌ። የኦሮሞ ህዝብ ከሊይ እንዯተገሇጸው የኦፒዱኦ ኣመራሮችና ጌቶቻቸው እየፈጸሙት ባሇው ዴብቅ ሴራ እንዲይታሇለ እያሳሰበ፥ የሕወሃት ፋሽስት መንግስት ያወጣውን ይህን እቅዴ በማክሸፍ ሇኦሮሞ ህዝብ ነጻነትና ኦሮሚያ ለዓሊዊነት እተካሄዯ ያሇውን ትግሌ በቆራጥነት በማጠናከር ሇስርዓቱ ፍጻሜ እንዴናበጅሇት ኦነግ ኣጥብቆ ያሳስባሌ። ከዚሁ ጋር ከስህተታቸው ባሇመማር በወገናቸው ሊይ ወንጀሌ እየፈጸሙ ያለ የኦሮሞ ዜጎችም ከዴርጊታቸው እንዱታቀቡ ያስጠነቅቃሌ።

በወያኔ መንግስት የጦር ሃይሌ ውስጥ ሇሚገኙና በተሇያዩ ዯረጃዎች ባለ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሇሚሰሩ የኦሮሞ ዜጎች በሙለ

ሁለም የኦሮሞ ዜጋ እንዯሚያውቀውና እንዯሚገነ዗በው የ዗ር-ማጥፋት ወንጀሌ በኦሮሞ ህዝብ ሊይ ከታወጀ ቆይቷሌ። ዛሬ የኦሮሞ ዜጎች ህይወት የወያኔ መሳሪያ ኢሊማ መሇማመጃ ሆናሇች። ይህ ዗ግናኝ እርምጃ ዯግሞ ሁለንም የኦሮሞ ዜጋ እንቅሌፍና ኑሮ የሚነሳ መሆን ይገባዋሌ። ስሇሆነም በወያኔ የጦር ሃይሌ ውስጥ የምትገኙና በፌዳራሌ ዯረጃና በኦሮሚያ ክሌሌ ውስጥ በተሇያዩ የመንግስት መዋቅሮች ውስጥ የምትሰሩ የኦሮሞ ተወሊጆች እራሳችሁን በማዯራጀት በምትችለት ሁለ ህዝባችሁ ሇነጻነት እያካሄዯ ካሇው ትግሌ ጎን እንዴትሰሇፉ ኦነግ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባሌ። ይህንን ሃሊፊነት ኣሇመወጣት በኦሮሞ ህዝብና ከታሪክ ተጠያቂነት እንዯማታመሌጡ መገን዗ብ ግዳታ ነው። ዛሬ ከኦሮሞ ነጻነትና ከኦሮሚያ ለዓሊዊነት ትግሌ ጎን የማንሰሇፍ ከሆነ ከወገናችን ጋር የምንቆምበት ጊዜ መቸ ይሆን? የሚሇውን ጥይቄ መምሇስም ግዳታችሁ እንዯሆነ ኦነግ ኣስረግጦ ያሳስባሌ።

የኢትዮጵያን የፖሇቲካ ዴርጅቶች በተመሇከተ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጸረ-ፋሽስት ወያኔ የሆኑ የኢትዮጵያ ኢምፓዬር የፖሇቲካ ሃይልች ሁለ እያካሄደት ያሇውን ትግሌ ያከብራሌ። በኢትዮጵያ ኢምፓዬር ውስጥ ሇሚገኙ ህዝቦች የራስን እዴሌ በራስ የመወሰን መብት መከበር ዓሊማ የሚታገለ ዴርጅቶችን ዯግሞ ኦነግ በተሇየ ይመሇከታሌ። የህዝቦች ትብብር ሇነጻነትና ሇዱሞክራሲ(PAFD) የተመሰረተውም ሇዚሁ ነው። በዚሁ ሁኔታ ሊይ በመመርኮዝ በሃገሪቱ ውስጥ በተጨባጭ መሌኩ መሬት ሊይ በሚታይ ስራ የሚታወቁ ዴርጅቶች የየዴርጅቶችን የፖሇቲካ ዓሊማ በማክበር፣ የጋራ ጠሊት በሆነው ፋሽስት ወያኔ ሊይ በማትኮር በጋራ ትግሌ እንዴናስወግዯው ኦነግ በዴጋሚ ጥሪውን ያቀርባሌ።

ተሇያዩ ምክንያቶች ከዴርጅታችን መዋቅር ውጪ ሊሊችሁ ኣባሊትና ዯጋፊዎች

የኦሮሞን ነጻነትና የኦሮሚያን ለዓሊዊነት ሇማረጋገጥ እየተካሄዯ ባሇው ትግሌ የቀረው የስርዓቱ መውዯቅ ኣይቀሬ መሆኑ እውን ቢሆንም ትግለን ሇማጠናቀቅ የሚጠበቅብን ኣስተዋጽዖ የሊቀ ነው። ኣሁን ባሇው ሁኔታ ከፊታችን ያሇውን ግዳታ በዴሌ ሇመቋጨት ኦነግ የሚሻውን ዴጋፍ ከማዴረግ የሚቆጥበን ማናቸውን ምክንያት መኖር የሇበትም። ያሇንበት ሁኔታ በመኖርና ኣሇመኖር መካከሌ ኣንደን እንዴንመርጥ ያስገዴዯናሌ። ህዝባችንን ከመጥፋት ሇመታዯግ ያሇንን የግሌ ችግር መፍታት ብሌህነት መሆኑን በመረዲት ካሁን በፊት በተሇያዩ ምክንያቶች ከኦነግ የወጣችሁ ኣባሊትና ዯጋፊዎች በኣፋጣኝ ወዯ ዴርጅቱ እንዴትመሇሱ ኦነግ ወገናዊና ሃገራዊ ጥሪውን ያቀርብሊችኋሌ።

ነጻ የሆኑ የኦሮሞ የፖሇቲካ ዴርጅቶችን በተመሇከተ

ጨቋኑ የወያኔ ፋሽስት መንግስትን ከኦሮሚያ በመንቀሌ የኦሮሞን ህዝብ ነጻነትና ዗ሊቂ ሰሊም ሇማስገኘት የኦሮሞን ህዝብ የሰው ሃይሌና ሃብት በኣንዴነት ማቀናጀት ወሳኝ መሆኑን በማመን ነጻ በሆኑ የኦሮሞ የፖሇቲካ ዴርጅቶች መካከሌ ከስምምነትና ከመግባባት መዯረሱ ይታወሳሌ። ይህ መግባባትና ስምምነት በስራ እንዱተረጎም ከነዚህ ዴርጅቶች ተወካዮች ተውጣጥቶ የተቋቋመው የኦሮሚያ ነጻነትና የኦሮሚያ ለዓሊዊነት ሃይልች ኣስተባባሪ ኮሚቴ ይህንን ስምምነት ስራ ሊይ ሇማዋሌና በመተግበሩ ስኬታማ እንዱሆን ኦነግ የሚጠበቅበትን እንዯሚያበረክት ያረጋግጣሌ።

በኣማራ ክሌሌ (ጎንዯር፣ ጎጃምና ወሌቃይት) ኣካባቢ ያሇውን እንቅስቃሴ በተመሇከተ

የኣማራ ህዝብ በጎንዯርና በጎጃም ኣካባቢ እያካሄዯ ያሇው ጸረ-ወያኔ እንቅስቃሴ የመብት እንቅስቃሴ መሆኑን ኦነግ ያምናሌ። ይሁን እንጂ የወያኔ መንግስት ካሌተወገዯ በስተቀር ይህ ጥያቄ ምሊሽ ያገኛሌ ብል ኣያምንም። ስሇሆነም በሁለም ኣቅጣጫ የወያኔን መንግስት ሇማንበርከክ መስራት ኣስፈሊጊ መሆኑን ኦነግ እያስታወሰ፥ በፋሽስቱ ወያኔ መንግስት በኣማራ ክሌሌ ህዝብ ሊይ እየተፈጸመ ያሇውን ግዴያ፣ እስራትና ሰቆቃ በጥብቅ ያወግዛሌ። በወያኔ መንግስት የሚፈጸመውን ዝርፊያና ማንነታቸውን የማጥፋት እርምጃ በመቃወም የኮንሶና የመጀንግር ህዝቦች እያካሄደት ያሇውን ትግሌ የኦሮሞ ህዝብና መሪ ዴርጅቱ ኦነግ እያዯነቀ፡ ከጎኑም እንዯሚቆም ያረጋግጣሌ። የኮንሶና የመጀንግር ህዝቦች እያካሄደት ያሇው ትግሌ ፍትሃዊ ትግሌ ነው ብልም ያምናሌ። በተጨማሪም በኮንሶና መጀንግር ህዝቦች ሊይ እየዯረሰ ያሇውን የጅምሊ ግዴያ፣ እስራትና ወከባ ኦነግ በጥብቅ ያወግዛሌ።

በውጪ ሃገራት የሚገኘውን የኦሮሞ ማህበረሰብን በተመሇከተ

የሃገር ባሇቤትነት መብቱን በመነፈግ፣ በሰሊም መኖር ባሇመቻለ በተሇያዩ ሃገራት የሚኖረው የኦሮሞ ማህበረሰብ ሇስዯተኝነት የዲረገውን ምክንያት በሚገባ ተረዴቶ ሃገሩን ማስመሇስ ወሳኝ መሆኑን ኣምኖ ሇኦሮሞ ነጻነትና ሇኦሮሚያ ለዓሊዊነት ትግሌ ዴጋፍ ሲያዯርግ ከዛሬ ዯርሷሌ። ኦነግ ይህንን ኣስተዋዕዖ እያዯነቀ ትግለን በዴሌ ሇመቋጨት ኣሁን ያሇው ሁኔታ የሚጠይቀውን ሌዩ ግዳታ ሇመወጣት በውጪ ሃገራት ያሇው ማህበረሰባችን ሇትግለ የሚያዯርገውን ዴጋፍ በእጥፍ-ዴርብ እንዱያሳዴግ የኦነግ ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባሌ።

የወያኔ መንግስት እያካሄዯ ያሇውን የ዗ር-ማጥፋት(Genocide) በተመሇከተ

ፋሽስቱ የወያኔ ሕወሃት መንግስት በኢምፓዬሪቷ ውስጥ ከታዩት መንግስታት ሁለ በሊቀ ሁኔታ በጭካኔ የተሞሊ መሆኑን ዴርጊቱ እንዯሚያረጋግጥ ሇሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚታገለ ዴርጅቶች ሁለ እየመሰከሩ ነው። የ዗ር-ማጥፋት ወንጀለ በቀጥታ በኦሮሞ ህዝብ ሊይ ያነጣጠረ መሆኑም ፋሽስቱ ወያኔ ሊሇፉት 11 ወራት የፈጸመውን ተግባር መመሌከትና የወሰዯውን እርምጃ ማጤን በቂ ነው። ይህ የ዗ር-ማጥፋት በጋምቤሊ፣ በቤኒሻንጉሌ፣ በሲዲማ፣ በኦጋዳንና በኮንሶና በመጀንግር ህዝቦች ሊይም በስፋት ሲፈጸም የነበረና ኣሁንም እያተፈጸመ ያሇ ወንጀሌ ነው። በቅርቡ ዯግሞ በኣማራ ህዝብ ሊይ ያነጣጠረውን ግዴያ ማስተዋለ ተጨማሪ ማስረጃ ነው ብሇን እናምናሇን። ስሇሆነም ይህንን እየተፈጸመ ያሇውን ዗ግናኝ ግዴያ ነጻና ገሇሌተኛ የሆነ ቡዴን መርምሮ በማጣራት ሇተባበሩት መንግስታትና ሇኣሇምኣቀፉ የወንጀሇኞች ችልት(ICC) እንዱያቀርብ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይጠይቃሌ። ከዚሁ ጋር በኦሮሞ ህዝብና በላልች ህዝቦች ሊይ እየተፈጸመ ያሇው የ዗ር-ማጥፋት ወንጀሌ መሆኑን ተገንዝበው ኣቤቱታችውን በማቅረብ ሊይ ሊለ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ኦነግ ያሇውን ኣዴናቆትና ምስጋና እየገሇጸ ይህንን የተቀዯሰ ስራቸውን ኣጠናክረው እንዱቀጥለ ይጠይቃሌ።

ዴሌ ሇኦሮሞ ህዝብ !!!

የኦነግ ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ

መስከረም 12, 2016ዓም

Journalist Tesfaye Tesemma vs. Jawar Mohammed on Ethiopians in Oromia

Journalist Tesfaye Tesemma challenges Jawar Mohammed on an event set to discuss social media activism in Washington DC and Jawar responds. Tesfaye asks whether there is real common agenda of Oromo protest and Amhara resistance and emphasizes on the necessity of genuine national dialogue. Tesfaye also asks about how the Oromo protesters and its activists view and understand the basic human and democratic rights of none/Oromo citizens residing in Oromia region.

 

 

ሽፈራው ሽጉጤ በዓማራ ህዝብ ላይ የሰራው ወንጀል!

“የትግራይ ወሰን ተከዜ ነው” ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም

ትዝታ በላቸው መለስካቸው አምሃ, VOA


በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ ክፍሎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣ ይመስላል።

በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ ክፍሎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣ ይመስላል።

የማንነት ጥያቄ ደግሞ ከአሰፋፈርና ከመሬት ይዞታ ጋር በጥብቅ የተሣሰረ ነው። ይህ ጉዳይ በክልሎች ቅርፅና ይዘት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። ይህ ምናልባት የማንነት ጥያቄ በሚነሣሳባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚያጋጥም ላይሆን ይችላል።

ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አቅንተን የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በየጊዜው ስንዘግብ ቆይተናል።

በወልቃይት አማርኛ ተናጋሪው ሕዝብ፤ አስተዳደሩ ከፍላጎታችን ውጭ ወደ ትግራይ ጠቅልሎናል ሲል ተቃውሞ ካቀረበ ሰነባብቷል።

ቅሬታውንም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርብ ኮሚቴ አቋቁሞ አባላቱ አዲስ አበባ ከመድረሳቸው በፊትና ከደረሱም በኋላ እየተዋከቡ መሆናቸውን አስታውቋል።

አሁንም ከፍተኛ የባህልና የሥነ-ልቦና ተፅዕኖ እያደረሱብን ነው ሲሉ ያካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በቀዳማዊ ኃይለሥሌ ዘመነ-መንግሥት ለብዙ ዓመታት የጠቅላይ ግዛቱ ገዥ የነበሩትን ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምንም ይዘናል።

ትዝታ በላቸው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሁለት የወልቃይት አዛውንት አነጋግራለች። የመጀመሪያው አቶ ላቀው አንዳርጌ ይባላሉ።

የኢትዮጵያ ካርታ

የኢትዮጵያ ካርታ

 

ትዝታ ያነጋገረቻቸው ሌላኛው የወልቃይት አካባቢ ተወላጅ ደግሞ የሰማንያ አምስት ዓመቱ አዛውንት አቶ ብርሃኑ አስረስ ይባላሉ።

እንደተጠቀሰው ወልቃይት ዛሬ የተካለለው በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ አስተዳደር ሥር ነው። ለመሆኑ ወልቃይትና ትግራይ በነበረ ታሪካቸው ምንና ምን ናቸው?

ከ1966 ዓ.ም. በፊት የትግራይ ጠቅላይ ገዥ የነበሩትን ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምን መለስካቸው አምሃ አነጋግሯቸዋል። ሙሉውን ዝርዝር ለማዳመጥ፣ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

 

ተጠናቀቀ ኢትዮጵያዊነት

By Abiyot Kasanesh

ተጠናቀቀ
ተው በለው ተው በለው
ቴሬ ጠረፍ ሽፈራው
ከልብ አስደስተሽኛል እህቴ ይሄ ነው የኢትዮጵያዊነት

እንዴት ባሳደገዉ ባጎረሰው ወገን
ህሊናስ ይፈቅዳል ብረት ለመደገን
ያበቀለህ ምድር ህዝቧም ጨዋ ናቸዉ
እጆችህ ጭካኔን ማን አስተማራቸዉ

ከወንድሜ ፊት ላይ አይቼዉ እግርህን
እንዳላምን አረከኝ ከሰው መፈጠርህን
የዛሬን ተዉእና በል የነገን አልም
ታዝዤ ነዉ ማለት ከፍርድ አያድንም

ለህሊናህ ታዘዝ ባክህ እወቅበት
ያንተም ቀኑ ሲመሽ መልስ እንዳታጣበት
መንገድ ላይ የጣልካት ልጄን ብላ ወታ
እስኪ እናቴ ብትሆን ብለህ አስብ ላፍታ

ጠላት ብታደርግኝ በልተን በአንድ ሞሰብ
ከብዶኛል ስራህን ለደቂቃ ማሰብ

ቸር አውለኝ ብለህ የምትማፀነው
ጌታ አይቆጣም ወይ ወንድምክን ስትገድለው
የማትፈቅደዉን እንዲደርስ አንተ ላይ
በሰው አታድርገው ይቆጣሃል ከላይ

ምትለምንልህን እንዲሰጥህ እድሜ
እህትክን ገደልካት ምን ነካህ ወንድሜ
በወገኖችህ ደም ታጥበከዉ እጅህን
እንዴት ነዉ ሚሰማዉ ፈጣሪስ ፀሎትህን
ጨክነህ ከሳብከዉ የብረትክን ላንቃ
ከሰዉ መፈጠርክን ዘንግተሃል በቃ

ከ ሄኖክ ነጋሽ

የዐማራ ብሔርተኝነት ለምን?

በዐማራ ብሔርተኝነት ላይ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚጽፉ ጎልማሳ ወጣቶች ውስጥ አቶ አያሌው መንበር እና አቶ ሙሉቀን ተስፋው ጋር በፎረም 65 ላይ “የዐማራ ብሔርተኝነት ለምን?” በሚል አጭር ቆይታ አድርገናል።