‹‹ይድረስ ላንቺ›› ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ – በዘላለም ክብረት

By Zone9 ‹‹ይድረስ ላንቺ›› ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ በዘላለም ክብረት    ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡ ‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣ እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››   የደላው! ቢያሻው

The post ‹‹ይድረስ ላንቺ›› ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ – በዘላለም ክብረት appeared first on 6KILO.com.

ይታይሽ የኔ አለም

ይታይሽ የኔ አለም…
በድሀ አንደበቴ አፈቅርሻለሁ ስል
ይታይሽ አለሜ….
በድሀ ትክሻ
ፍቅርን ያህል ነገር ተሸክሜ ስዉል
ልብ አርጊዉ እንግዲህ…
የድሀ አንደበቱ ጉልድፍ ተብታባ ነዉ
አፈቀርኩኝ ሲል ነዉ የተባዉ የሰላዉ
ልብ አርጊዉ እንግዲህ…
የድሀ ትክሻ ቀጭን ጎባጣ ነዉ
ፍቅርን ሲሸከም ነዉ ወፍሮ የቀናዉ
ተመልከች እንግዲህ…
የድህነት ባህር ጥልቀት ባይለካም
ልብ አርጊዉ እንግዲህ ይታይሽ የኔ አለም
ከፍቅር ጋር ሲኮን…
መስመጥ አያሰጋም መሞት አያስፈራም
አይገርምሽም ታድያ…
ይሄ ከንቱ ሁላ…
የፍቅርን ሚዛን የማያዉቅ ነሁላላ
ያለልኩ ሂዶ…
ያላቅሙ አፈቀረ እያለ እሚያወራ
ያዉም ፍቅርን ሳያዉቅ ያዉም ሳይጠራ
የልቡን ዉብ መሻት የህይወቱን ዜማ
ከድህነት በርኖስ ከችግር አዉድማ
በመንፈስ ተነጥቆ በነብሱ ሳይሰማ
እያያት መሻቱን ፊት ለፊቱ ቁማ
መደብ ይሉት ግድብ ብሄር ይሉት ባህር
የፍቅር እርግቡን እንዳትበር የሚያስር
ታካች በበዛበት
ሰነፍ በሞላበት እንቅልፍ በወረሰዉ
በዚህ ሁሉ ድብርት በዚህ ቅዠት ማሀል
ይሰማሽ የኔ አለም…
በድሀ አንደበቴ አፈቅርሻለሁ ስል
የመደብ ግድቡን በፍቅርሽ አልፌ
የብሄር ባህሩን በሳቅሽ ቀዝፌ
ፍቅርን ብቻ ብየ ፍቅርሽን አግዝፌ
ከኔ ልመሳሰል ካንች ልቀላቀል
ይሰማሽ የኔ አለም…
በድሀ አንደበቴ አፈቅርሻለሁ ስል


(በሰለሞን ሳህሌ)

«አይደለም።የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም አሳማ ስለማይበላ ነው።» አለኝ

Dawit Temesgen ዶር መረራ ባንድ ወቅት«የተራበ ሕዝብ መሪዎቹን ይበላል» ብለው ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተርቦ ስለማያውቅ ነው ወይ መሪዎቹን የማይበላው? ብዬ አንዱን ብጠይቀው፤ «አይደለም።የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም አሳማ ስለማይበላ ነው።» አለኝ።

The post «አይደለም።የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም አሳማ ስለማይበላ ነው።» አለኝ appeared first on 6KILO.com.

ፈሪ ነኝ! ሞዴል ፈርቶ አደር! -Agegnehu Asegid

Agegnehu Asegid ፈሪ ነኝ!ፈሪ ነኝ! ሞዴል ፈርቶ አደር! ውሃ ውስጥ ሆኜ የሚያልበኝ። በርግጥ ውሃው “ፍል ውሃ” ከሆነ ማንም ሊያልበው ይችላል። እኔ ግን አጥንት በሚቆረጥም ውሃ ውስጥም ያልበኛል። መፅሀፉ፣ “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው” ይላል። እኔ ግን “የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ፣ መጨረሻውም ሁሉንም መፍራት ነው” ብያለሁ። ፈርቻለሁም። እግዜር ሰይፍ የያዙ መላዕክት አሉት። መንግስት ዱላ እና ጠመንጃ

The post ፈሪ ነኝ! ሞዴል ፈርቶ አደር! -Agegnehu Asegid appeared first on 6KILO.com.

መሣፍንት ባዘዘው: ጎንደሬ አድምጥ!

ጎንደሬ አድምጥ!
(መሣፍንት ባዘዘው)ዛሬ ልወርድብህ ነው! ከዛ መሃል ፒያሳ ላይ ከቆመው የመይሳው ሃውልት ላይ ተለጥፈህ ፎቶ መነሳትህን ተው!! ለጊዜው የቴዲ ልጅ ነኝ እያልክ መዝፈኑንም ያዝ አድርገው።ጀግና ሳንሆን የጀግና ልጅ ነኝ እያሉ መኮፈስ ይብቃን!! የቴዎዽሮስ ሃሞት እንጥፍጣፊዋ እንኳ ከኛ ዘንድ ሳትኖር እንዴት የጀገናውን ስም በከንቱ እንጠራዋለን?

ወልቃይት ሲቆረስ ዝም! ጠገዴ ሲቆረስ ዝም! ዋልድባ ሲታረስ ዝም! አርማጭሆ ሲሸጥ ዝም! የቴዎድሮስ ሃገር ቋራ ሲሸጥ ዝም! ትውልድ በጫት ሱስ እዬደነዘዘ ፣ የትምህርት ፖሊሲው ጥራት እያሽቆለቆለ… እያዬህ “እምቢ!” ማለት ካቃተህ የቴዎድሮስ ልጅ ነኝ አትበለኝ። አሁንስ በዛ ብለህ መነሳት ከቃተህ …እንኳን ከመይሣው ሃውልት ላይ ፎቶ ልትነሳ ነው እና በአጠገቡ ማለፍ የለብህም። እውነት እኔ እዛ ሃውልት ላይ ተደግፌ ፎቶ መነሳት አፍራለሁ። ሌላውን ሁሉ ተወው! እስኪ የወያኔን ሃሳብ ከመደገፍ ተቆጠብ።እስኪ መጀመሪያ በሃሳብ ደረጃ “እምቢ!” በል!

እስኪ ግራ እና ቀኝህን ተመልከት! ያቺ የተቀደሰች ከተማ በጫት ቤቶች ስትሞላ እየታዬህ አይደለም?ትንንሾችህ በአንተ እግር እዬተተኩ ወደ ሱስ እዬገቡ እንደሆን አስተውለሃል? ከ20 አመት በፊት የነበሩት ቸቸላ ሆስፒታል እና ፖሊ ክሊኒክ ስንት ሆስፒታል እና ክሊኒክ ተጨመረላቸው? ወገንህን እሲኪ ቸቸላ ላይ ሄደህ እየው…ሜዳ ላይ እንደ ምናምንቴ ወዳድቆልሃል!ፋሲለደስ ስንት ሃይድኩል ወለደ? ምንም!! ስንት ፋብሪካ ተተከለ? …… የወያኔን ሴራ ከአንተ የበለጠ ማን ያውቀዋል? እና ምነው ተኛህ? ኧረ ንቃ!!!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እዬተቧደንክ ከመነታረክ እስኪ ስለ ቴዎድሮስ መንፈስ ተወያይ። እውነት የቴዎድሮስ ልጅ መሆናችንን በተግባር እናሳይ!! ዘፈን ብቻ ሰለቸኝ!! የኛም ትውልድ ቴዲን አምጦ ይውለድ እና መጭው ትውልድ ይዝፈንልን!! በየመጠጥ ቤቱ የአራዳ ልጅ፣ የፒያሳ ልጅ እያልክ በቢራ ጠርሙስ ስትፈነካከት ለም መሬትህ ለሱዳን ተቸብችቦ አለቀልህ…እስኪ በየቀበሌ መቧደንክን ትተህ አንድ ሁን እና በጠላትህ በወያኔ ላይ ተነስ!!

የተዋበች የምንተዋብ ፣የጥሃይቱ ሴት ልጆች በየሺሻ ቤቱ ሲውሉ እያዬህ እንዴት አስቻለህ? ከትንንሽ እህቶችህ ጋር የሺሻ ገመድ እዬተቀባበልክ ስታጨስ ምንም አይሰማህም?? ኧረ እንደተኛን ነግቶ ተመልሶ መሸ………

ምስጋና ለአያሌው ጎበዜ – አክባሪዎ አቢሲኒያዊ

እርስዎ ብዐዴን/ህወሀትን ወክለው የአማራን ህዝብ ሲመሩ መቆየትዎ ይታወቃል በዚህም የክልሉ ህዝብ ኤያሌው ጎበዜ ለዘላለም ይኑር እያለ እንዲኖር ማድረግዎትን የሚያስታውሱት ነው እርስዎ በጣም ያሳዘኑኝ ያ ወዳጅዎ ደመቀ መሬቱን ድንጋይ ያድርግለት እና በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ይገባሻል ብሎ መለስም ብራቮ

The post ምስጋና ለአያሌው ጎበዜ – አክባሪዎ አቢሲኒያዊ appeared first on 6KILO.com.