የግብጽ ተላላኪዋ ህወሀት ና አባይ ላይ የሰራችው ደባ

By Ze Addis የግብጽ ተላላኪዋ ህወሀት ና አባይ ላይ የሰራችው ደባ

******************************************************
ህወሀት አልሳካ አላት እንጂ ታሪክን ለማጥፋት ያልጣረችው ጥረት : ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም:: በተለይ ያለፈ ነውረኛ ታሪኳን ለመሸፈን : ሐዲስና እንግዳ ልቦለድ በመጻፍ ብዙ ትደክማለች:: እውነት ግን እውነት ስለሆነች አትሞትም እንጂ::

ሰሞኑን ግብጽ አባይን በተመለከተ ስምምነትን አሁን አልፈርምም ማለቷ ተሰምቷል::

የህወሀት ካድሬዎች ደግሞ

“ግብጽ አልፈርምም ያለችው ህወሀት ከወደቀ በኋላ ስልጣን ላይ የሚቀመጠው ኢትዮጵያዊ – አባይን በተመለከተ የሀገሩን ጥቅም የማያስከብር ስለሆነ እሱን አውቃ ነው” የሚል አዲስ ትረካ ጀምረዋል:: what an amazing analysis lol

አባቱን አያውቅ ይሏል ይህ ነው:: እውነት እንደሚነገረን ግን የአባይን ግድብ በማፍረስና ኢትዮጵያ አባይ ላይ ያላትን ጥቅም አሳልፎ የሰጠው የህወሀቱ መሪ መለስ ዜናዊ እና ድርጅቱ ህወሀት ናቸው:: የህወሀትንና የመለስን ያህል አባይ ላይ ክህደት የፈጸመ የለም::
ዝርዝሩ እንዲህ ይቀጥላል

የጣና በለስ የአባይ ግድብና 1800 ኪሎሜትር የመስኖ ልማት ፕሮጀክት
***************************************************
የአባይ ግድብ የተጠናውና የተግባር ዝግጅት የተጀመረው በ1930ዎቹ ነው:: የኮሎኔል መንግስቱ መንግስት ስልጣን ይዞ ጥቂት እንደቆየ( በ1970ዎቹ) -ተግባራዊ ለማድረግ ከተነሳባቸው አንዱ ፕሮጀክትም የአባይ ግድብንና የመስኖ ልማትን ነበር:: ከነዚሁ ግድቦች ውስጥም ጣና በለስ ፕሮጀክት ተመረጠ:: የዚሁ ግድብ ኢንጂነር የነበረው
Giordano Sivini(ጆርዳኖ ሲቪኒ) – Resistance to Modernization in Africa Translated by Joan Krakover Hall , 2007, New Jersy
በሚለው መጽሓፉ የጣና በለስ ግድብን መስኖ ልማትን እንዲህ ሲል ይተርከዋል( page 123-125)

The Beles Valley lies at an altitude between 1000 and 1300 meters; it is 60 killometers long and 30 kms wide.
The plan of Tana Beles project was to irrigate the Beles valley with water brought down through a tunnel from Lake Tana ( Nile intersection) , the source of the Blue Nile, that is why the project is called Tana- Beles. The idea of this project goes back to the thirties; it was revived in the sixties and now by Mengistu and the Italian agency. Using the water brought through the tunnel, a hydro- electric power station was planned to be constructed to supply energy for the WHOLE COUNTRY and Beles valley below would become a sort of gaint irrigated farm( 60 km by 30 Km) that could produce very significant surplus. An Italian consultancy firm , engaged to implement the project , quickly developed an amazing master plan to settle not 100,000 but 300,000 people in 118 villages with road and services including network of hundreds of killometer.

በአጭሩ ወደ አማርና ስንመልሰው ጣና በለስ የግድብና የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመን በ1930ዎቹ በአሜሪካኖች ተጠንቶ ; በ1950ዎቹም ሊሰራ ተሞክሮ በመጨረሻ በዘመነ መንግስቱ በ1970ዎቹ የተጀመረ ግድብ ነበር::

የዚሁ ግድብ ዓላማም የመጀመርያው ክፍል- የመላ ሀገሪቱን የመብራት ፍላጎት የሚያሟላ ግድብና የኃይል ማመንጫ መስራትና 60 ኪሎ ሜትር በ30 ኪሎሜትር የሚሆነውን የበለስን ሸለቆ የአባይ ውሃን በመጠቀም በመስኖ ማልማትና ሀገሪቱን በምግብ እህል በማትረፍረፍ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ነበር::

አሜሪካ : ግብጽና ሱዳን ክፉኛ ቢቃወሙም ኮሎኔል መንግስቱ ግን ስራውን አላቋረጡም:: ከጣልያን መንግስት በተገኘው የ200 ቢሊዮን ሊሬ ብድርና እርዳታ ፓኬጅ ስራው ተጀመረ:: በአጭር ጊዜ ውስጥም የጣልያኑ ኮንትራከተር ሥራውን ተረክቦ ግድቡ : የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግንባታውና የመስኖ ልማቱ ሥራ ተጀመረ:: የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ ተማሪዎች: የባህር ዳር ፖሊ ቴክኒንክ ተማሪዎች: የአለማያ ኮሌጅ ተማሪዎች በተደጋጋሚ በመዝመት የበለስ ልማት ላይ ተሳትፈዋል:: ይሄን ግዙፍ የመብራት ኃይል እና እርሻ ልማት ግንባታ ረጅም ርቀት ከሄደ በኋላ ህወሀት አዲስ አበባን ያዘች::

ህወሀት የጣና በለስ ግድብና የመስኖ ልማት ማወደሟ
*********************************************
ህወሀት አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረች የመጀርያ ስራዋ ጣና በለስ ፕሮጀክትን ድምጥማጡን ማጥፋት ነበር:: አዲስ አበባ በገባች በሳምንቱ ጣና በለስን እንደ ጠላት ጦር ዘመተችበት:: በመቶዎች የሚቆጠሩ ግሬደሮች: ኤክስካቬተሮች ትራክተሮችን የቻለችውን ዘርፋ የተረፉትን ድምጥማጡን አጠፋቸው::

ሲልቪያኖ የተባለው የግድቡ መሃንዲስ አግራሞቱን ” Unforgivable mistakes ” በሚለው ጽሁፉ እንዲህ ገልጾታል

” ሱዳንና ግብጽ እንኳን እንዲህ ያፈራርሱታል ብዬ አልጠብቅም:: እነዚህ ሰዎች የኮሎኔል መንግስቱ ተቃዋሚ ቢሆኑም : የሀገራቸው ተቃዋሚ ግን መሆን አልነበረባቸውም:: እንዴት ይህን የሚያህል ሀገሪቱን ወደ ታላቅ እመርታ ከፍ የሚያደርጋትን ፕሮጀት እንዲህ ለማውደም ፈለጉ:: እንደ ሰው ግራ ገብቶኛል:: ይህን 60 ኪሎ ሜትር በሰላሳ ኪሎ ሜትር የሆነ መስኖ ልማት የሚያመርተው በሚሊዮኖች ኩንታል የሚቆጠር ምርት እኮ ለሀገሪቷ ኢኮኖሚ ከባድ እና ታላቅ አስተዋጾ ነበር:: እጅግ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው:: እንዴት ሰው ሀብቱንና ንብረቱን እንዲህ ያወድማል ” በማለት በቁጭት ገልጾታል::

ህወሀት ይሄን ያወደመችው የግብጽንና የሱዳንን ውለታ ለመመለስ ነበር:: ዛሬ ግዜ ተገልብጦ ደግሞ –
“ሌላው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያን ጥቅም በአባይ ላይ ስለማያስጠብቅ ነው አሁን ግብጽ አልፈርምም ያለችው ” የሚለውን ስላቅ መስማት ይገርማል:: ጅብ በማያቁበት ሀገር..የሚለውን ተረት ያስተርታል::

ጣና በለስ ያባድ ግድብና መስልኖ ልማት እና ያሁኑ ያባይ ግድብ
*****************************************
ያሁኑ የአባይ ግድብ ላይ ኢትዮጵያ ውሃውን ኤሌክትሪክ ከማመንጨት ውጭ ለምንም መጠቀም አትችልም:: ያሁኑ ያባይ ግድብ ትልቁ ጥቅሙ ሊያመነጭ የሚችለው ኤሌክትሪክና የተገደበው ውሃ ላይ ሊረቡ የሚችሉ አሳዎች ናቸው::

ጣና በለስ ግን የአባይን ውሃ ከአባይና ጣና መገናኛ በግዙፍ ቱቦ በማመላለስ 30 ኪሎ በስልሳ ኪሎ ሜትር የሆነው ( 1800 ስኩዌር ኪሎሜትር) እርሻን በአባይ ውሃ የሚያለማ ነበር:: ከአዲስ አበባ ሞጆ ድረስ በግምት ወደ 60 ኪሎ ሜትር ነው) ያንን የሚያህል እርሻ በዓመት ሁለቴ በአባይ ውሃ በማልማት ሀገሪቱን የእህል ጎተራ የሚያደርግ ነበር:: የጣና በለስ ኤሌክሪክ ማመንጫም በወቅቱ የሀገሪቱን ኤሌክትሪክ ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ የሚያሟላ ነበር:: የሱዳንንና የግብጽን ወለታ ለመመለስ ህወሀት አፈራረሰችው እንጂ::

በነገራችን ላይ አሁን ጣና በለስ ላይ የተገነባው የርሻ ላማት ቀድሞ የፈረሰውን አንድ መቶኛ እንኳን አይሆንም::

የአባይ ግድብን የደፈረ የሚባልለት መለስ ዜናዊ እውነተኛ ታሪኩ ግን የአባይን ግድብ ያፈረሰና የሃገሩን ጥቅም ለሱዳንና ለግብጽ የሸጠ ነበር::

ሌባ እናት ልጇን አታምንምና ዛሬም የህወሀት ግልገል ካድሬዎች – ” ወያኔ ስልጣን ቢለቅ የሚመጣ ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያን የአባይን ጥቅም አያስጠብቅም ” ሲሉ መስማት በራሱ ያስገርማል:: Really?

የሀገር ጥቅምን በማስከበር ከህወሀት የሚያንስ ማንም የለም::

%d bloggers like this: