“የትግራይ ወሰን ተከዜ ነው” ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም

ትዝታ በላቸው መለስካቸው አምሃ, VOA


በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ ክፍሎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣ ይመስላል።

በኢትዮጵያ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱ ክፍሎች ቁጥር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጨመረ የመጣ ይመስላል።

የማንነት ጥያቄ ደግሞ ከአሰፋፈርና ከመሬት ይዞታ ጋር በጥብቅ የተሣሰረ ነው። ይህ ጉዳይ በክልሎች ቅርፅና ይዘት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። ይህ ምናልባት የማንነት ጥያቄ በሚነሣሳባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚያጋጥም ላይሆን ይችላል።

ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ አቅንተን የወልቃይትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በየጊዜው ስንዘግብ ቆይተናል።

በወልቃይት አማርኛ ተናጋሪው ሕዝብ፤ አስተዳደሩ ከፍላጎታችን ውጭ ወደ ትግራይ ጠቅልሎናል ሲል ተቃውሞ ካቀረበ ሰነባብቷል።

ቅሬታውንም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርብ ኮሚቴ አቋቁሞ አባላቱ አዲስ አበባ ከመድረሳቸው በፊትና ከደረሱም በኋላ እየተዋከቡ መሆናቸውን አስታውቋል።

አሁንም ከፍተኛ የባህልና የሥነ-ልቦና ተፅዕኖ እያደረሱብን ነው ሲሉ ያካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በቀዳማዊ ኃይለሥሌ ዘመነ-መንግሥት ለብዙ ዓመታት የጠቅላይ ግዛቱ ገዥ የነበሩትን ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምንም ይዘናል።

ትዝታ በላቸው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሁለት የወልቃይት አዛውንት አነጋግራለች። የመጀመሪያው አቶ ላቀው አንዳርጌ ይባላሉ።

የኢትዮጵያ ካርታ

የኢትዮጵያ ካርታ

 

ትዝታ ያነጋገረቻቸው ሌላኛው የወልቃይት አካባቢ ተወላጅ ደግሞ የሰማንያ አምስት ዓመቱ አዛውንት አቶ ብርሃኑ አስረስ ይባላሉ።

እንደተጠቀሰው ወልቃይት ዛሬ የተካለለው በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ አስተዳደር ሥር ነው። ለመሆኑ ወልቃይትና ትግራይ በነበረ ታሪካቸው ምንና ምን ናቸው?

ከ1966 ዓ.ም. በፊት የትግራይ ጠቅላይ ገዥ የነበሩትን ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምን መለስካቸው አምሃ አነጋግሯቸዋል። ሙሉውን ዝርዝር ለማዳመጥ፣ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

 

%d bloggers like this: