ወያኔ የአማራውን ህዝብ ማጥፋቱ አልበቃ ብሎት ሀይቃችንንም ሊያደርቀው ተዘጋጅቱዋል

በአማን አበባው

image

በጣና ሀይቅ ላይ 40 ሺህ ሄክታር ላይ የተከሰተው የእንቦጭ አረም የሀይቁን ብዝሃ ህይወት ለከፋ ጉዳት ማጋለጡ ተገለጸ ።

አረሙ የውሀን የመትነን መጠን በሦስት እጥፍ በመጨመር በአጭር ጊዜ ሊመለስ የማይችል ጉዳት የማድረስ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑ ተግልጿል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት አረሙን በሰው ሃይል ለማስወገድ ሰፊ ጥርት ቢደረግም አረሙ ካለው ፈጣን የማደግና የመራባት ስነ ህይወታዊ ባህሪ ጋር ተያይዞ መልሶ ሀይቁን በመውረር ውጤታማ ስራ ማከናወን እንዳልተቻለ ተግልጿል።
በዓሣ ሀብት፣ በቱሪዝም እንቅስቃሴ፣የእንስሳት ግጦሽ መሬትን በመውረር፣ በሃይቁ ዙሪያ የሚገኘውን የእርሻ መሬት ከሰምርት ውጭ በማድረግ ጉዳት እያደረስ ነው።
የሀይቁንና የሌሎች የውሀ አካላትን ደህንነት በዘላቂነት ለመጠበቅ የተጀመረው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ገዱ አስታውቀዋል።
የአማራ ክልል የአካባቢ ጥበቃ፣ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ አቶ ባይህ ጥሩነህ አረሙ በ19 ቀበሌ ከ40 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ በሀይቁ ዙሪያ ውሀ አዘል መሬት፣የእንስሳት ግጦሽ ቦታ፣የእርሻ ማሳና ሃይቁን ሸፍኖ ይገኛል ብለዋል።
ባለፈው አንድ ወር በህዝቡ ተሳትፎ በተደረገ ጥረት ከስድስት ሺህ 800 ሄክታር የሚበልጥ በአረሙ የተጠቃ ቦታን ማፅዳት የተቻለ ቢሆንም በሞገድ እየተገፋ መልሶ በመሸፈን የመከላከሉን ስራ ከአቅም በላይ እንዳደረገው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመጤና ተዛማጅ አረሞች ብሔራዊ አስተባባሪ አቶ ረዘነ ፍሰሃ በበኩላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተለዩ 45 አደገኛ አረሞች 38ቱ በአማራ ክልል ይገኛሉ ብለዋል።
ከእነዚህም ደግሞ እምቦጭ ወይም በሳይንስዊ ስሙ (ዋተር ሃያሲስ) የተባለው አረም በውሀ ላይ በመንሳፈፍ በፍጥነት በመራባት ብዝሃ ህይወትን በማውደም የሚስተካከለው እንደሌለ ገልፀዋል።
ከፍተኛ ውሀ በመሸከም በተፈጥሮ የሚተነውን የውሀ መጠን በሦስት እጥፍ በማሳደግ በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሀ በማትነን የውሃ መጠኑን እንደሚቀንስ በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል።
በጣና ሃይቅ ላይ መከሰቱ በሃይቁ ዙሪያ ያለው ውሀ አዘል መሬትን ለችግር ከማጋለጡ ሌላ በአካባቢው የሚያርፉ ስደተኛ ወፎችን መጠለያ በመንሳት እያጠፋቸው መሆኑን አስታውቀዋል።
በሀይቁ የሚገኙ የዓሣ ዝርያዎችን የእርባታ ሂደት በማስተጓጎል ሀብቱ ላይ ጉዳት በማድረስ በዘላቂነት ሊያጠፋቸው እንደሚችል አስረድተዋል።
ሀይቁ ለአካባቢው ህዝብ የሚሰጠውን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጠቀሜታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአጭር፣የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ተይዞ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል።
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ለምባ አርባየቱ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አዱኛ መኮንን በሰጡት አስተያየት የእምቦጭ አረም የእንስሳት ግጦሽ መሬትን በመሸፈን መኖውን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን ተናግረዋል።
በአካባቢያቸው ዓሣ በማስገር ቀደም ሲል በቀን ከ20 እስከ 30 ኪሎ ግራም ምርት ያገኙ እንደነበር አስታውቀው አረሙ ከተከሰተ ወዲህ ግን የሚያገኙት ምርት ከ10 ኪሎ ግራም በታች መቀነሱን ገልፀዋል።
የሚያምርቱት ዓሳ ጣዕም በመቀየሩ ገበያ ላይ ተፈላጊነቱ እየቀነሰ መምጣቱን ጠቁመው ወደባቸውም በአረም በመወረሩም ረጅም ርቀት በመጓዝ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል።
በሃይቁ ዙሪያ የነበራቸው የእርሻ መሬት በአረሙ በመጠቃቱ በበጋው ወራት ሽንኩርት፣ቲማቲም፣ድንች፣በቆሎና መሰል ሰብሎችን አምርቶ በመሸጥ ያገኙት የነበረው ገቢ ሙሉ በሙሉ መቆሙን ተናግረዋል።
አረሙ እያደረሰ ያለውን ችግር ለመከላከል ህዝቡ በሳምንት ሁለት ቀን እየወጣ የማፅዳት ስራ ቢያከናውንም በፍጥነት ተመልሶ ስለሚወረው የመከላከሉ ስራ ከአካባቢው ህዝብ አቅም በላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

%d bloggers like this: