ኮሎኔል ደመቀን በተመለከተ አሁን ያለው ዕውነታ

Image result for Demeke ZewduMuluken Tesfaw

Update: ኮሎኔል ደመቀን በተመለከተ አሁን ያለው ዕውነታ

 የዞኑ ፍርድ ቤት ፋይሉን ዘግቷል፤ የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አዲስ መዝገብ ሊከፍት ይችላል

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጉዳይ ሲመለከት የከረመው የሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮሎኔሉ ላይ የተመሠረቱት ሁለት ክሶች ዘግቷል፡፡ በሰው መግደል ወንጀል የነበረው የመጀመሪያው ክስ ከሳሽ ባለመቅረቡና ክሱ ላይ ማስረጃ ባለመቅረቡ ምክንያት መስከረም 03 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ ክሱን መዝጋቱ ይታወቃል፡፡
የፌደራል አቃቢ ሕግ በመስከረም 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በሽብር ወንጀል አዲስ ክስ ከፍቶ ጉዳዩን ይኸው ፍርድ ቤት ሲከታተል ቆይቶ ነበር፡፡ ዛሬ በዋለው ችሎት በፌደራል አቃቢ ሕግ የቀረበው የሽብር ወንጀል የተሟላ ማስረጃ ያልቀረበ ሲሆን የዋስትና መብት ሊያስነፍገው አይችልም፡፡
ችሎቱ የቀረበውን ክስ በዝርዝር ሲመለከት ከዋለ ካረፈደ በኋላ ጉዳዩን ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ነው ማየት የሚችለው በማለት መዝገቡን ዛሬ ዘግቷል፡፡
የኮሎኔል ደመቀን ጠበቃ በስልክ ባነጋገርናቸው መሠረት ጉዳዩን ሊያየው የሚችለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መሆኑን እና የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትን ወክሎ የሚሠራው የዐማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሜን ጎንደር ምድብ ችሎት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
የቀረበባቸው ክስ ዋስትና ሊያስከለክል የማይችል እንደሆነ የሚገልጹት ጠበቃው ዛሬ ከሰዐት በኋላ በዋስ መውጣት አለመውጣታቸው እንደሚታወቅ ተናግረዋል፡፡

%d bloggers like this: